In 8 years of extreme mismanagement, Poverty Party stole $25 billion from Ethiopians
Posted: 08 May 2026, 17:45
Highway robbery!
Finfinne Press
ከ 2013 እስከ 2022 በ 9 አመት ውስጥ ብቻ ኢትዮጵያ በሙስና 25 ቢሊዮን ዶላር አጥታለች። ይሄ የሀገሪቱን አጠቃላይ ኢኮኖሚ 25% ይሸፍናል። ከ 2022 በሗላ ደግሞ የሙስና ፍጥነቱ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በአመት ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር እየደረሰ መሆኑን የአፍሪካ ልማት ባንክ ያወጣው መረጃ ያሳያል።
በትንሹ 3 ቢሊዮን ዶላር ወስዳችሁ ከላይ ካለው ቁጥር ላይ ብትጨምሩበት አጠቃላይ ኢትዮጵያ ከ 2013 ጀምሮ በሙስና ያጣቺው ገንዘብ 34 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል።ይሄንን አሀዝ ወደ ብር ብትቀይሩት 5 ትሪሊዮን 440 ቢሊዮን ብር ይደርሳል።
ይሄ የተወሰደ ብር የት ነው የሄደው ካላችሁ እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ መረጃ ከሆነ አብዛኛው በባለስልጣናት አማካኝትት ከኢትዮጵያ ወጥቷል።
የአፍሪካ ልማት ባንክ መረጃ አክሎም በኢትዮጵያ የውጭ ገቢ ንግድ በትክክል ሪፖርት የሚደረገው 35% ብቻ ሲሆን 65% ሪፖርት የውሸት ሪፖርት ነው።
የኢትዮጵያ 15 ቢሊየነሮች በስዊዝ ባንክ እና በካሪቢያን ወስጥ በምትገኘው ካይማን ደሴት በሚገኝ ባንክ አካውንት ከፍተው ገንዘባቸውን ወደዚያ ያስወጣሉ- ከባለስልጣናት ጋር በመተባበር።
የኢትዮጵያ የወርቅ 30% በሱዳን በኩል ብሎ ኢማራት ይደርሳል እንጅ የኢትዮጵያ ባንኮችን ንክች አያደርግም።
ይሄ ሁሉ ሀብት ከዚህ ድሀ ህዝብ ላይ ከዚህች ድሀ ሀገር ላይ የተቀማ የተሰረቀ ነው። ይሄ እጅ ከወርች የሚያሳስር ሙስና ባለበት ተጨባጭ ሀገር በፍፁም በፍፁም አታድግም።
የደለቡት ሳይጠግቡ ሌሎች አዲስ ረሀብተኛ ሙሰኞችም እየመጡ ሀገሪቷ እንዲህ ሆና መቅረቷ ያሳዝናል። ይህ ሙስና የኢትዮጵያ ህዝብ የኑሮ ሁኔታ ያቃወሰ ፤ የዋጋ ንረቱን ባለፉት ጥቂት አመታት ከ 400% በላይ እንዳደርስ ያደረገ ፤ የብርን የመግዛት አቅም ባለፉት ስምን አመታት ብቻ በ 500% እንዲወድቅ ያደረገ አሳዛኝ ሰባሪ ክስተት ነው።
ይህን በሙስና የሚጠፋውን ገንዘብ ለማሟላት ሀገሪቱ በነ IMF የብድር ማነቆ ውስጥ ገብታለች ፤ ህዝባችን ላይ ከአቅም በላይ የሆነ ግብር ተቆልሎበታል እንዲሁም በርካታ ሀገር የሚለውጡ ፕሮጀክቶች ታጥፈዋል። በዚህ ሙስና ምክንያት ሀገሪቱ የጦር አውድማ ሆና መረጋጋት የተሳናት ሆና ቀጥላለች!
ኡኡኡኡ የሚያስብል ሁኔታ ላይ ነው ያለነው!