Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Horus
Senior Member+
Posts: 43042
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ETHIOPIA'S CULTURAL CONTRIBUTION TO THE WORLD: TEDDY AFRO - NO.1 PROMOTOR OF GLOBAL ETHIOPIA!

Post by Horus » 06 May 2026, 12:04

በኢትዮጵያ በየዘመኑ የተነሱ ባንዳዎች፣ መሃይሞችና ኢትዮጵያ ጠሎች ይህቺን አገር በድንቁርና ፣ በድህነት ፣ በጎሰኘት ፣ በዘረኝነት ፣ በረሃብ ፣ በስደት፣ በጦርነት ፣ በአላማ ቢስነት በአለም ላይ ስሟ ተደጋግሞ ተደጋግሞ እንዲነሳና መለያችንም ጦርነትና ድህነት እንዲሆን አድርገዋል ።

ይሄው ዛሬ እድሜ ለሙዚቃው ሊቅና ገጣሚ ሎሬት ቴዲ አፍሮ ይሁንና በየቀኑ በሚሊዮኖች በመላ አለም ስማችን በተዋበው የዜማ ባህላችን ይነሳል! ያለም ወጣት በያገሩ ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያ ሙዚቃ እየተባልን ስማችን ይነሳል! የወሎ ረሃብን አሳይቶ ስንቱን አሳፋሪ ዘመን አሻግሮ ለዚች ቀን ላደርሰን የኢትዮጵያ አምላክ ገለት ምስጋና ከማለት ሌላ ምን ቃል አለን !!!! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!


Abere
Senior Member
Posts: 15545
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ETHIOPIA'S CULTURAL CONTRIBUTION TO THE WORLD: TEDDY AFRO - NO.1 PROMOTOR OF GLOBAL ETHIOPIA!

Post by Abere » 06 May 2026, 12:16

ቴዲ አፍሮ መዝፈኑ አይደለም። በቴዲ አፍሮ እንጉርጉሮ በእውነት ለኢትዮጵያ ግንባሩን የሚሰጥ ስንት ወጣት ተገኜ ነው። በቀኝ ጆሮው አዳምጦ በግራው እያፈሰሰ ዩቲዩብ ተመልካች 10 ቢልዮን ቢደርስ የቴዲ እንጉርጉሮ ብቻውን ኢትዮጵያን ቀና አያደርግም፤ ያለቁትን ወጣቶች ከአፈር አይቀሰቅስም፤ ወልቅጤ ከእነ ጥማቸው እንስራ ተሸክመው በኦሮሙማ ወታደር የተደፉት እህቶች ቀና አያደርጋቸውም። የቴዲ መልዕክት ለአርበኝነት እንጅ ለጫት መቃሚያ አይዋል። በፍርሃት የጀግናው ስራ አይርከስ የሚል ማሳሰብያ ቢሰነዘር መልካም ነው።



ethiopianunity
Senior Member
Posts: 11004
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: ETHIOPIA'S CULTURAL CONTRIBUTION TO THE WORLD: TEDDY AFRO - NO.1 PROMOTOR OF GLOBAL ETHIOPIA!

Post by ethiopianunity » 06 May 2026, 18:29

We don’t believe in Al manufactured ad for Teddy! Teddy’s is organic and true ad naturally will come! Live in truth not in fakery

Post Reply