Page 1 of 1

ሲንጋፖር - አዲስ አበባ - አስመራ

Posted: 03 May 2026, 16:37
by Selam/
ሲንጋፖር የተፈጥሮ ሃብት የሌላት ባዶ ሃገር ነች፣ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ፀጋ የተቸረች ሆኖም በክፉ አስተዳዳሪዎቿ በነበረችበት ተተክላ የቀረች ሃገር ነች። ኤርትራ በተቃራኒው ተፈጥሮም የበደላት መልካም አስተዳደርም የጎደላት ክፍለ ሃገር ነች።

ኢትዮጵያ የከተማ ልማትን ከሲንጋፖር እንዳለ የምትገለብጠው ፣ መሪዎቿ ራሳቸውን የማያውቁ አናሳዎች ስለሆኑ ነው። ኤርትራ ሲንጋፖርን መሆን ተመኝታ ሰንጋተራን እንኳን መሆን አቅቷት እየሻገተች ያለችው አቅሟንም ማንነቷንም ጠንቅቀው የማያቁ ጭንጋፎች ስለጠለፏት ነው።


Singapore:



Addis Ababa:





Asmara:


Re: ሲንጋፖር - አዲስ አበባ - አስመራ

Posted: 03 May 2026, 17:04
by Fiyameta

Re: ሲንጋፖር - አዲስ አበባ - አስመራ

Posted: 03 May 2026, 17:36
by Axumezana
አዝመሪኖን አስረጇት ሰማሁኝ
በኮሪደር ልማት አብዬ ታደገኝ

ምን ግዜ አለኝና በመደመር እሳቤ አገር አፍርሻሌሁ
አራት መደቦች መማር አሁን ጀምሬአሎሁ
PHDው ይቅርብኝ ሀሁ እቆጥራሎሁ

ወይ ነዶ ወይ ነዶ
የነሰላም ሶደሬ አየሁት ተንዶ

Re: ሲንጋፖር - አዲስ አበባ - አስመራ

Posted: 03 May 2026, 23:06
by Misraq
አስመራ ልጆዋን ትጣራለች። ምነው ዘነጋችሁኝም ትላለች። ልጆችዋ አሮጊት ቡቱቷም ብለው ጥለዋት ውደ እንጀራ እናታቸው ቤት ሄደው መሬት እየጠረጉ ፡ ሽንትቤት እያፀዱ ፡ ፓርኪንግ እየሰሩ ይኖራሉ።።አስመራ የተተወች እናት። ባሳደገች እፉኝት ልጆችዋ የከዷት ምስኪን ቆዳዋ የተጨማደደ እናት ናት።

ታሳዝናለች። አንድ ቀን እሷ ራሷ ታማኝ ልጆዋን ይዛ ወደ ኢትዬጵያ መሰደድዋ አይቀርም።