Page 1 of 1

Abere የሚያየው ጥቁር ወይም ነጭ ብቻ ነው። Axumezana ግን ጠንካራ ጎንን ያሞግሳል ስህተትን ደግሞ እንዲስተካከል ይጎተጉታል!

Posted: 01 May 2026, 03:06
by Axumezana
ወፍጮ በእንገቱ ላይ ታስሮበት
እንደ ጋሪ ፈረስ ሲጎትት በአቀበት
የዚህ አለም ሸክም እጅጉን ከብዶት
አበረ ይመን በእየሱስ ጭነት ይቅለልለት

viewtopic.php?f=2&t=343588&p=1619043#p14765

Re: Abere የሚያየው ጥቁር ወይም ነጭ ብቻ ነው። Axumezana ግን ጠንካራ ጎንን ያሞግሳል ስህተትን ደግሞ እንዲስተካከል ይጎተጉታል!

Posted: 01 May 2026, 07:37
by Selam/
ነጭም ይሁን ጥቁር ፣ ወይንም ህብረ ቀለም
ግራ ጫፍ ላይ ቆሞ ፣ ወደ ቀኝ የሚያልም
እጨጌው በፍፁም ፣ አመንክዮ አያውቅም

ማቴዎስን ገልጦ ፣ ሲያገኝ ቅድስና
ነፍስ ለነጠቀው ፣ ምህረት ይሰጥና
አፉ መርዝ ይተፋል ፣ ለጎዳው ጭቆና

Re: Abere የሚያየው ጥቁር ወይም ነጭ ብቻ ነው። Axumezana ግን ጠንካራ ጎንን ያሞግሳል ስህተትን ደግሞ እንዲስተካከል ይጎተጉታል!

Posted: 01 May 2026, 07:56
by Axumezana
ፋኑዬ እንደሆን ግራ ተጋብተዋል
ስላም ይሻለዋል ከእናት አባት መዋል
የሰላም ትርጉሙ አልገባ ብሏቸው
የወለንጭቷ ትንታግ እርሷ ትንገራቸው
ፋኑዬ ፈሪ ነው ጦር ሲያይ ይሸሻል
እርቅ አድርጎ ይግባ ምጣድኑን ያሟሻል!
ተራው የደረሰ ቀን አራት ኪሎ ይነግሳል
ፒፒ ከወይን እርቅ የገቡ እለት
ኢሱና ፏኑዬ አቤት ጌቶች ወዴት
አበረ ወንድማችን ደከመ ጉልበቱ
ያቀልጠው ጀመረ ሰላም ድረሽ እቱ
ያ Axumezana አይቻል ሙጉቱ

Re: Abere የሚያየው ጥቁር ወይም ነጭ ብቻ ነው። Axumezana ግን ጠንካራ ጎንን ያሞግሳል ስህተትን ደግሞ እንዲስተካከል ይጎተጉታል!

Posted: 01 May 2026, 08:47
by Selam/
አንቺው ታመጪው ፣ አንቺው ታሮጪው
ተብሎ በአያቶች ፣ እንደ ተተረተው
አንዱን ክፍተት ደፍነህ ፣ ሌላውን በተንከው

ሰላም የሚመጣው ፣ በፈቃደኝነት ነው
በግልፅ ስምምነት ፣ ሁሉም ተማምለው
የውሸቱንማ ፣ በእናንተ አየነው
በድብቅ ተቀርፆ ፣ ሳይቆይ የፈረሰው

Re: Abere የሚያየው ጥቁር ወይም ነጭ ብቻ ነው። Axumezana ግን ጠንካራ ጎንን ያሞግሳል ስህተትን ደግሞ እንዲስተካከል ይጎተጉታል!

Posted: 01 May 2026, 12:59
by Abere
ሰላም ይስጥህ ብሎ ሰላም ሲያስተምርህ፤
ስንት አምና አለፈ ምክር ሳያርስህ- እንደ ድንጋይ ደርቀህ፤
የሰላም ሓዋርያ የጉባዔው መህምር፤
ሰላም ጨርሶታል - እኔ ምን ልጨምር?

የበላዔሰብ እምቤት እመ ኩሉ ህዝብ ትርዳህ፤
የያዘህ ወያኔ ቡዔል እንድለቅህ፤
አዘክሪ ድንግል ብለህ ጸልይ ማልደህ፤
ይህ አለም ሳይጨልም - መያዣው ሳያጥርህ።