Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11655
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

የቴዲ አፍሮ የግል ስቱዲዮ እና ቢሮ ላይ የተፈፀመ መንግስታዊ ዘረፋ

Post by MINILIK SALSAWI » 23 Apr 2026, 23:25

የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ፣ መሳሪያ የታጠቁ እና በፌዴራል ፖሊስ ተሽከርካሪ የመጡ ታጣቂዎች፣ ሲኤምሲ አካባቢ የሚገኘውን የቴዲ አፍሮ የግል ስቱዲዮ እና ቢሮ በኃይል ሰብረው መግባታቸውን ተሰምቷል። ....... ይህ ህገ-ወጥ የኃይል እርምጃ የተፈጸመው ትናንት ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ ወደ ስቱዲዮው ጥሶ ለመግባት የህንጻውን ጥበቃ (ዘበኛ) በከፍተኛ ሁኔታ መደብደባቸው ተገልጿል። ......... ከዚህ የኃይል እርምጃ ባሻገር የጉዳዩን አሳሳቢነት እጅግ ከፍ የሚያደርገው የተሰበረው ቢሮ ይዘት እና የተወሰዱት ንብረቶች ጉዳይ ነው። ይህ ስቱዲዮ ቴዲ አፍሮ እንደ ዋና ቢሮ የሚጠቀምበት፣ የፈጠራ ስራዎቹን የሚያዘጋጅበት፣ ለህዝብ ጆሮ ያልደረሱ አዳዲስ የሙዚቃ ስራዎቹ እና ግጥሞቹ የሚገኙበት፣ እንዲሁም አዳዲስ ሀሳቦቹን የሚጽፍበት እጅግ ሚስጥራዊ እና ጥብቅ የጥበብ ማህደር ነው። .......... በስፍራው በርካታ እና ውድ የሆኑ አዕምሯዊ ንብረቶች የሚገኙ ሲሆን፣ አሁን በወጡ አዳዲስ መረጃዎች መሰረት ሰብረው የገቡት የፖሊስ አባላት ከስቱዲዮው ውስጥ ሁለት ላፕቶፖችን፣ ስፒከሮችን፣ የሙዚቃ ማቀናበሪያ መሳሪያዎችን እንዲሁም የተለያዩ የስቱዲዮ እቃዎችን ወስደዋል።


Post Reply