Page 1 of 1

ኢትዮጵያ ውስጥ ልዩነቶችን የሚያስተናግድ የፖለቲካ መሰረት አለ ብሎ የሚያስብ ሰው አጭበርባሪ ወይንም ድፍን ነው!

Posted: 21 Apr 2026, 22:41
by Selam/
አሁን ሃገራችን ውስጥ ያለው የፖለቲካ ባህል ተቸርችፎ ተከርክሞ፣ የጎጥ ማንነት መገለጫና የገንዘብ ማከማቻ፣ የሎሌዎች ማጠራቀሚያና ያፈነገጠውን የመኮርኮሚያ መሳሪያ ሆኖል እንጂ የርዕዮተ ዓለም መፎካከሪያና የሃሳብ መፋጫ አይደለም።

ባለ ጊዜዎቹ ህጉን ለስልጣናቸው እንዲመቻቸው አድርገው ይለጥጡታል፣ የቀነጭቡታል ወይንም ይደፈጥጡታል እንጂ ተፎካካሪዎችንም ይሁን ህዝቡን የሚያሳትፍና ቅራኔን ሊያጠፋ የሚችልን የህግ ማሻሻያ ለማድረግ በፍፁም ፍላጎት አያሳዩም። በዚህም ምክንያት በተለይ ወጣቱ መብቱን እንዳይረዳና ከፖለቲካ ተሳትፎ እንዲሸሽ አድርገውታል።

ህዝብ እየተሸማቀቀና ሚዛናዊ የፖለቲካ ባህል ሳይዳብር፣ ብልጭልጭ መንገድ ብቻ ዘላቂ ለውጥና ዕድገት ያስገኛል ብሎ ማሰብ ራስን ማታለል ነው።

Re: ኢትዮጵያ ውስጥ ልዩነቶችን የሚያስተናግድ የፖለቲካ መሰረት አለ ብሎ የሚያስብ ሰው አጭበርባሪ ወይንም ድፍን ነው!

Posted: 21 Apr 2026, 23:14
by Axumezana
የትግራይን ፓለቲካ እንዴት አየሽው?

Re: ኢትዮጵያ ውስጥ ልዩነቶችን የሚያስተናግድ የፖለቲካ መሰረት አለ ብሎ የሚያስብ ሰው አጭበርባሪ ወይንም ድፍን ነው!

Posted: 22 Apr 2026, 03:16
by Selam/
ምን እንድልልህ ፈልገህ ነው?

የዛሬውን የቂም በቀል ፖለትካ መሠረት የጣለችው እኮ ያንተዋ ስስታሟ TPLF ነች። ለራሳችሁ የፖለቲካ ብዝሃነትን ሳታስተናግዱና ለውጥ ሳታመጡ ባላችሁበት ቦታ ተቀርቅራችሁ ቀርታችሁ፣ ከተከዜ
አልፎ የሚሄድ የፖለቲካ ተፅዕኖ አድርጋለሁ ማለት ትርፉ ጉልበትን ማዛልና መገጣጠብ ነው።