Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sesame
Member+
Posts: 8549
Joined: 28 Feb 2013, 17:55

''በፍቅር ጠርተው ከዳር እስከዳር: መሀል ገቡና አቆሙን ከዳር።'' ... ቴዲ አፍሮ

Post by sesame » 16 Apr 2026, 14:31

He nailed it!

Finfinne Press

''በፍቅር ጠርተው ከዳር እስከዳር
መሀል ገቡና አቆሙን ከዳር።'' ... ቴዲ አፍሮ

ይህ ግጥም ከዘፈንም በላይ ነው። በጥበብ ቃላት የተገለፀ ፣ #የብልፄን የአጥፍቶ ጠፊ የፖለቲካ መስመር የተናገረ ፣ ለስልጣን ተብሎ የተፈፀመውን ግፍ ያመላከተ ነው።

ይህ ግፍና በደል ከተፈፀመባቸው ግንባር ቀደሞቹ የኦሮሞ ልሂቃን ቀዳሚዎቹ ናቸው። ታግለው ፣ ፊት ለፊት ዋጋ ከፍለው ፣ በህይወታቸው ተወራርደው ፣ ህዝብ አታግለው ባመጡት ለውጥ ተገፍተው ከዳር እንዲቆሙ ተደርገዋል።

መገፋት ብቻ አይደለም ... በአሰቃቂ ሁኔታ የተ ገደሉ ፣ በእስር የሚማቅቁ ፣ ከሀገር እንዲሰደዱ የተደረጉ ብዙሃን ናቸው። በፍቅር ስም እየተማለ ፣ በመደመር ቀመር እየተገዘተ ... የተቀነሱ ፣ የታሰሩ ፣ የተገፉ ... ከዚህም አልፎ የህይወት መስዕዋትነት እንዲከፍሉ ተደርጓል።

አዎ ..."በፍቅር ጠርተው ከዳር እስከዳር
መሃል ገቡና አቆሙን ከዳር" .... በዚህ ጨካኝ አገዛዝ ግፍና በደል ለተፈፀመባቸው በሙሉ ይሁን 🙏


Naga Tuma
Member+
Posts: 7367
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ''በፍቅር ጠርተው ከዳር እስከዳር: መሀል ገቡና አቆሙን ከዳር።'' ... ቴዲ አፍሮ

Post by Naga Tuma » 16 Apr 2026, 15:17

sesame wrote:
16 Apr 2026, 14:31
የኦሮሞ ልሂቃን
ልሂቅ ከማለት በፊት ቦረና፣ ኦሮሞ፣ ጋላ የሚሉት ቃላት ምን ማለት ናቸዉ ብሎ መፍታት ችግሩን የሚፈታ ኣይዴለም?

Post Reply