Page 1 of 1

“ይኸ አዲስ አበባ እንጂ ፓሪስ ወይንም ሲንጋፖር እንዳይመስልህ!”

Posted: 31 Mar 2026, 19:48
by Selam/
በእኔ አመለካከት “ይኸ አዲስ አበባ እንጂ ፓሪስ ወይንም ሲንጋፖር እንዳይመስልህ” ወይንም “ስታንዳርዱን የጠበቀ” የሚባለውን የካድሬዎችና የመንጋዎች የዘፈቀደ አገላለፅ፣ ከበታችነት ስሜት የመጣ ስለሆነ አልወደውም።

ምክንያቱም የእነሱን የስልጣኔ ውሃ ልክ የሚመሰክሩላቸው ከአፍሪካ ውጪ ያሉት ሰዎች ብቻ ስለሚመስላቸው ፣ ሁልጊዜ ራሳቸውን የሚያወዳድሩት አፍሪካ ካልሆኑ ሃገሮች ጋር ነው።

- ለምን ይፈራሉ ከራሷ ከአፍሪካ ስልጣኔ ጋር ለማወዳደር?

- ለምን ምስክር ከራሷ ከአፍሪካ አህጉር ለመፈለግ ይሽኮረመማሉ?