Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Affable
Member
Posts: 784
Joined: 15 Jul 2023, 13:21

Re: አዲሱ ገናናው የኢትዮጵያ ካልቸር! የታደለ ትውልድ! በሥራ ክቡርነት ካልቸር ያደገው!

Post by Affable » 26 Mar 2026, 12:54

ይህን አዲስ ትውልድ ስራ የማይንቅ ፣ የመኪና የቤት እዳ ለመክፈል ሁለት ስራ የሚሰራ ህዝብን ነው እኛ ነን መምራት አለብን የሚሉ ፋኖ ፣ ሸኔ እና ህወአት። እኔ የምለው መምራቱን ተውት ልትኖሩበት የሚያቅታችሁ አገር እየተፈጠረ ነው ያለው ጎበዝ አረ ልብ ግዙ ነው። ኢትዪጺያኖችን እርስበርስ እያጋጩ መኖር እያከተመለት የመጣ መሰለኝ።
አቢይ ከዚህ በፊት ያለው ነገር አለ — አገራችንን በፉጥነት ስናሳድግ በ Ethiopia ላይ ጦርነት ያወጁ እየከሰሙ ይሄዳሉ የሚል። ያ ግማሽ እውነት ነው። ቆንጠጥ ማረግም at times አስፈላጊ ነው።

Abere
Senior Member
Posts: 15410
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አዲሱ ገናናው የኢትዮጵያ ካልቸር! የታደለ ትውልድ! በሥራ ክቡርነት ካልቸር ያደገው!

Post by Abere » 26 Mar 2026, 13:35

Huressa,

የባህል ትርጉም ያለ አግባቡ እና ያለ ቦታው እየተጠቀምከው ነው። አንድ ሰው ወይም አገር አውሮፕላን ገዝቶ ቢያስገባ አውሮፕላን የዚያ ግለሰብ ወይም አገር አይደለም። ዐለም አቀፍ ኮሞዲቲ (ሸቀጥ) ሽግግር ወይም ልውውጥ ነው። ኢነትርኔት ማስገባት የአንድ አገር /ግለሰብ አይደለም፤ ኮንዶምንዬም እና ተያያዥ ሸቀጦቹን ማስገባት ወይም ማስመሰል ወይም ፓርክ ቀጥሮ የገና አባት ዛፍ ተክሎ ማብለጭለጭ ባህሌ ብሎ ኬኛ ማለት ትልቅ ስህተት ነው። ዓለም ዛሬ ድንበር ዐልባ - የቴክኖሎጅ እና የባህል ሽግግር ላይ ነች። ግልሰቦች ወይም አገራት ተገደው የሚያስገቧቸው ወይም የሚሸቅጧቸው ቁሳቁስ ናቸው። በጠራራ ፀሐይ ባህሌ ብሎ መዝረፍ፤ ወይም ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ማዋል ያስቃል እንጅ አድንቆት አይቸርም።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሸቀጥ ሳይሆን የራበ እና የተጠማው ሰላም ነው። የሰላም እርቦታል፤ በደሳሳ ጎጆው ውስጥ የእግዜር ውሃ ጠጥቶ ተመሰግን ብሎ ተኝቶ ለማደር አማን አውለኝ ብሎ ማልዶ ለመነሳት አይልም - ከቱርክ እና ከኢምሬት በተገዛ የድሮን ሸቀጥ ይጋያል፤ በስንት ድካም ጥሮ ግሮ የሰራው የከተማ ቤቱ እሁድ ጠዋት ቤተ-ክርስቲያን ደርሶ ሲመለስ ፈራርሶ የሰፈሩ የጂኦግራፊ ምስል ተደምሦሶ ይጠብቀዋል - በወጣበት የጎዳና ላይ ተዳዳሪ ወይም ባልድ እና ፍራሽ ተሸክሞ ኦሮሞ ስላላይደለ እንድባረር ይደረጋል። ይች አንተ ለሾው የምትለጣጥፋት ህንጻ ህዝብ በጥንድ ዐይኖቹ እያስለቀሰ ያለ - የአማራ ህዝብን አከርካሪቱን ሰብረነዋል፡ ኦሮሞ ዝሆን ነው ትግሬ እና አማራ ጥንቸል ነው- አዲስ አበባ የኦሮሞ እንጅ የማንም ኢትዮጵያዊ አይደለም - እያለ የኢትዮጵያዊያንን ጥሪት እየዘረፈ ያለ ጸረ-ሰው፤ እና ጸረ-ኢትዮጵያ የሆነ የኦሮሙማ ዲስኩር ነው። እንደተለመደው ውራጌዎች የአድርባይነት ደዌ በክፉ የመታችሁ ስለሆነ የማጎብደድ እና ፕሮፓጋንዳ የመጫን አጋሥስነት አለባችሁ - ይህን የውርደት ምግባር ከቢራኑ ነጋ ማየት ይቻላል።
ኦሮሙማ የአዲስ አበባን የስልጣኔ ስበት የማክሰም፤ በኦሮሙማ ሸምቀቆ አፍኖ የመግደል ሴራ እንጅ የስልጣኔ አብነት ምግባር አይደለም።
አዲስ አበባ የስበት ማዕከል ሳትሆን የጭካኔ፤ የማፈናቀል፤ የዘረኝነት፤ የዝርፊያ፤ የርካሽ ጎድጅ ልማድ (አደንዛዥ ዕጽ፤ የአልኮል፤ የድሪያ፤ የዝርፊያ፤ የፈሪዎች እና የፍርሃት ቆፈን) የሰፈነባት ሙት ከተማ ነች። የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ከተደራረበ ፍርሃት እና እንግልት የተነሳ መብት የሚባለውን ሰብዐዊ እሴት የማያውቅ ኋላ ቀር፤ የፈሪዎች፤ የሆድ አደሮች በመክሰም ላይ ያለ ነው።

Tiago
Member
Posts: 3307
Joined: 30 Jul 2018, 02:09

Re: አዲሱ ገናናው የኢትዮጵያ ካልቸር! የታደለ ትውልድ! በሥራ ክቡርነት ካልቸር ያደገው!

Post by Tiago » 26 Mar 2026, 13:55

The building contractors are Chinese,the plants including the scaffolding at the site are in complete opposite to how is done by the locals.

The local contractors do not care about safety at construction sites (for both workers and community).in most cases,it is run by quasi-professionals and labourers. resulting in poor workmanship.

In most countries contractors are required to have some vocational qualification and experience in building construction.Here,you just need money ,connection and fake qualification.

I am not implying there are no qualified structural engineers,quantity surveyors,contractor admin.,soil mechanics,etc but the vast majority of personnel in the building industry in Ethiopia are of poorly trained and dodgy.

You idiotic cadres want the status quo to continue and think FANO is run by cowards,thieves and fake professionals like yourselves.

You like it or not FANO is coming to town soon.

Horus
Senior Member+
Posts: 42716
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ገናናው የኢትዮጵያ ካልቸር! የታደለ ትውልድ! በሥራ ክቡርነት ካልቸር ያደገው!

Post by Horus » 26 Mar 2026, 14:47

affable,
ይህን ሃቅ መናገር ለብዙዎች ጭካኝነትና ድሃ ጠልነት እንደ ሚመስላቸው አውቃለሁ! ሃቁ ግን ያ ነው ፤ እሱም የዛሬይቱ አዲስ አበባ ለስራ ፈት፣ ለምኖ አዳሪ፣ ቀምቶ አደርና እንዲሁም የኔ ብጤ ድሃ ምቹ መኖሪያ ከመሆን እየወጣች ነው ። ዛሬ አዲሳባ ድሃ መሆን በፍጹም አይቻልም። ይህን መሰል ባለ ሁለት ስለት የእድገት ሂደት ሁሉም ያደጉና የሰለጠኑ ሕዝቦች ያለፉበት growing pain ነው።

ድህነት እንደ ስርዓትና መደበኛ ሕይወት ሲፈርስ የሚፈናቀሉ ብዙ ብዙ ድሃዎች አሉ። የስርዓት ለወጥ ሁሉ ግዙፍ መፈናቀን ይዞ ይመጣል። ያ ደሞ የኢኮኖሚ መፈናቀል ብቻ ሳሆን ያይምሮ ፣ ያስተሳሰብ፣ የእምነት፣ የድንቁርና ፣ የስንፍናና አላማ ቢስነት መፈናቀልን ሁሉ ነው ይዞ የሚመጣው።

Disruption is the mother of transformation. And, these are disruptive times. Abiy Ahmed is a disruptive leader. That is what I like about him and that is why I decided to support him.

Even the current international order, the so called word order has become a disruptive world order.

Yes, the age old shackles that have imprisoned our people must be disrupted and transformed whatever the cost. That includes poverty and the comfort of impoverished living in Addis Ababa slums.

My slogan has been - Change the place, then the people will also change. ወጣቱ ሕዝባችን 3 ሺፍት በቀን ከሰራ ባጭር ግዜ አዲስ ኢትዮጵያን ይፈጥራሉ ! አለ ጥርጥር!

Affable
Member
Posts: 784
Joined: 15 Jul 2023, 13:21

Re: አዲሱ ገናናው የኢትዮጵያ ካልቸር! የታደለ ትውልድ! በሥራ ክቡርነት ካልቸር ያደገው!

Post by Affable » 26 Mar 2026, 15:36

Horus እኔ እህት አለችኝ አዲስ አበባ የምትኖር ስለተፈናቀሉት አምርራ ታዝን የነበረ። ባብዛኛው ሲፈናቀሉ ኮንዲሚኒየም ቤት የተሰጣቸው አሮጊቶች ጨምሮ አለጎረቤት መኖሩ እንዴት እንደከበዳቸው ትነግረኝ ነበር። አሁን እሷም ተለውጣለች። የከተማው መለወጥ አስደሳች ሆኖ አግኝታዋለች። Still she is more liberal than I am, but the reality sinks in. አዲስ አበባ አሁን ሁሉም ሊኖርባት የሚችል ባት ከተማ እንዳልሆነች ሁለታችንም አምነናል።
እንዳውም አንድ ልጅ ሆነን የምናውቀው ሰው አለ። አሁንም በህይወት አለ። ከገጠር ሲመጣ ምንም ዘመድ የለውም። የቀን ስራ ሰርቶ ፣ የድሮ የጭቃ ቤት ስራን ተምሮ ፣ በሃላ ዘበኝነት ተቀጥሮ ሚስት አግብቶ ልጆች ወልዶ የኖረ። የአሁኗ አዲስ አበባ ታደሰን — የሰውየው ስም ነው — ተቀብላ ታስተናግዳለች ብሎ ማመን ይከብዳል። ከደቡብ የሚመጡ አሁንም አሉ ግን የሚኖሩት በብዛት ሆነው አንድ ቤት ተከራይተው ነው። እንደ ታደሰ አንድ ዘኒጋባ ተከራይቶ የሚኖር አንድ አዲስ መጤ አይኖርም። አሁን ወደ አዲስ አበባ እየፈለሱ ያሉና ችግር የማይገጥማቸው የገንዘብ ችግር የሌላቸው የክፍለሀገር ሰዎች ናቸው።
ሁሉም አገር ሰዊች ሊኖሩበት እየፈለጉ ሊኖሩበት የማይችሉበት ከተማ አለ በንዋይ ችግር።
ጃፓን ቶኪዪ ሁሉም ሰው የሚኖርበት ከተማ አይደለም። የቻይናውም ፔኪንግ እንዲሁ።
እዚህ አህጉራችንም ብንመለከት ናይሮቢ ውስጥ ሁሉም ኬንያዊ መኖር አይችልም።
አዲስ አበባም ያንን ፈለግ እየተከተለች ነው። ሁሌም የድሮን የመናፈቅ አባዜ no matter how backward it is must stop.

Abere
Senior Member
Posts: 15410
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አዲሱ ገናናው የኢትዮጵያ ካልቸር! የታደለ ትውልድ! በሥራ ክቡርነት ካልቸር ያደገው!

Post by Abere » 26 Mar 2026, 16:06

አዲስ አበባ ኢትዮጵያዊያን ሊኖሩባት የማይችሉ ከተማ ከሆነች ለኢትዮጵያዊያን ጥቅም አልተቆረቆረችም፤ በዚያ ትልም አልበለጸገችም፤ ተነጥላ የተንሳፈፈች ደሴት ናት፤ ማለት ነው። ምን አይነት ተጠየቅ ነው? በሳይንሳዊ የከተማ ልማት አረዳድ አድስ አበባ ሌሎች የኢትዮጵያ ከተማዎችን እየበላች እንደ አልቀት እየመጠጠች የፋፋች ጭራቅ ከተማነች - primate city። በኢትዮጵያ ያሉ ከተማዎች ሁሉ ቢሰባሰቡ የአዲስ አበባ ያህል ግዝፈት የላቸውም ። The monster city of Addis Ababa not having even 2nd largest country is the sign of an impoverished country. This primate dependent city is also easy to flash up something to catch the attention and destruct citizens from main political agenda.

If an average Ethiopian cannot live in Addis Ababa, whose city is Addis Ababa? Obviously, it is thieves, corrupts, and hideouts for runaway criminals. These criminals stole in hundreds of millions of Birr from poor Ethiopians and are saturating criminals' den of Addis Ababa.

Those opportunists like Huressa, do not care about the plight of the average Ethiopians.

Horus
Senior Member+
Posts: 42716
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ገናናው የኢትዮጵያ ካልቸር! የታደለ ትውልድ! በሥራ ክቡርነት ካልቸር ያደገው!

Post by Horus » 26 Mar 2026, 16:14

ትክክል ነው፤ ለውጡን ከፊት ሆኖ የሚጎትተው መሻሻልና ሃብት እንጂ መውደቅና ድህነት ሊሆን አይችልም። ከገጠር ድህነት የማይሻል ከተማ 6 ሚሊዮን ሕዝብ ስለተሸከመ ከተማ አይሆንም። ስለዚህ አዲስ አበባ የሚፈልሰው ባላገር ሁሉ ትልቀበል አትችልም። በትክክል አዲስ አበባ ኑሮ ውድ ስለሆነ አልሄድም የሚባልበት ዘመን ገብተናል።

ያ ሲሆን ነው ገጠር ያለው ወጣት የገጠር ኮሪደር ውስጥ እየገባ ዘመናዊ ገጠር መፍጠር የሚጀምረው ። አዲሳባ የመንገድ ተዳዳሪ ማየት እየቀረ ነው ። ቁርስና ምሳ ስለሌላቸው ት/ቤት የማይሄዱ ህጻናት ማየት እየጠፋ ነው። ሌላው ቀርቶ የለማኝ ቁጥር በጣም ቀንሷል።

በሚቀትለው 5 አመት ውስጥ የጭቃ ቤት በፍጹም አዲስ አበባ ውስጥ በሕግ አይኖርም ብሏል አቢይ!

ስለዚህ የተከፈለው መስዋዕትነት ተከፍሎ ይህን የዝመና ሽግግር ማድረግ የግድ ይለናል ። ይህ ደም አይቀሬ ነው!

በኔ ጽኑ እመንት አቢይ አህመድም አዳነችም አለጥርጥር የሚቀትሉትን 5 አመታት ይመራሉ ። ይህን ማለት ደሞ ፒያሳን ፓሪስ አስመስለው መርካቶን በእስለምነት ሊያቆዩ አይችሉም ። እንዲያውም የኔ ግምት የ2027 ኖቬምበር ኮፕ32 የተመድ ኮንፈረንስ ከመደረጉ በፊት አሁን የቀሩት የጉለሌ ፣ መርካቶ ፣ ኮልፌና አየር ጤና ቆርቆሮች የሚፈርሱ ይመስለኛል።


It's all a birth pain.

Horus
Senior Member+
Posts: 42716
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ገናናው የኢትዮጵያ ካልቸር! የታደለ ትውልድ! በሥራ ክቡርነት ካልቸር ያደገው!

Post by Horus » 26 Mar 2026, 16:42

በአሁን ወቅት ከገጠር ወደ ከተማ የሚፈልሱ ወጣቶች፣ አዲሳባ መጥተው ባንድ የጭቃ ክፍል ውስጥ 4 ውይም 6 ሆነው የሚኖሩበት ሁኔታ ወደፊት አይቀጥልም ። መታወቂያ ዲጂታል እና ቢኦሜትሪክ ስለሆነ የሰው ቆጠርና ማንነት መለየት እጅግ ዘምኗል። ሲቀጥል ከተማው ነዋሪ የሚኖረው አፓርትሜንት ውስጥ እየሆነ ሲሄድ በአንድ አፓርትሜንት ውስጥ ስንት ሰው ሊኖር ይችላል በሚለው ጉዳይ ተነስቶ ሕግ ይበጅለታል ።

ለምሳሌ እጅግ በበለጸጉት አገሮ 2 + 1 rule የሚባል ሕግ አለ። አንድ አፓርትሜንት ውስጥ በ1 መኝታ ቤት 2 ሰው ሂሳብና 1 ተጨማሪ ሰው ሳሎን ውስጥ ሊተኛ ይችላል። ማለት አንድ አፓርትሜንት 2 መኝታ ቤት ካለው ልይዝ የሚችለው 5 ሰው ብቻ ነው ። ይህ የኪራይ አፓርትሜንት ሕግ ነው ።

ቤቶችም ሆኑ አፓርትሜንቶች የግል ቤቶች ከሆኑ ይህ ሕግ ላይሰራ ይችላል ፣ ሆኑም ዉሃ ፣ መብራት ፣ ስልክና ሌሎች ከመንግስት ጋር የተያያዙ አገልግሎቶች ሳቢያ እንደ ቤቱ ስፋት የነዋሪ ሰው ቁጥር የሚወስን ሕግ የሚኖር ይመስለኛል።

ዞሮ ዞሮ ግለሰቦች ሁሉ የሆነ አይነት የመግስት አገልግሎት ስለመጠቀሙ በተሰነ ቦታ መታጨቅ የሚችሉ ሰዎች ቁጥር በግድ የተወሰነ መሆኑ አይቀሬ ነው።

Post Reply