Page 1 of 1

ምክር ለኦባንግ ሜቶ፣ ሕዝብህን ከዘለዓለም ትዝብት ለማዳን ወንድምህ ዮሓንስ ለታን ወይ ምከር ወይም እሰር

Posted: 25 Mar 2026, 19:46
by Naga Tuma
ኦባንግ ሜቶ ይህን መድረክ የምታነብ ከሆነ ሕዝብህን ከዘላለም ትዝብት ለማዳን ተመከር።

በእኔ አስተያየት ይህ ዘመን የመለኮታዊ ብይን ዘመን ይመስለኛል።

ስለ መለኮታዊ ነገር ያጠናሁ ሳልሆን የዚህን ዘመን የተለያዩ ክስተቶችን እያስተዋልኩ ከሰዉ ልጅ ማብራራት ዐቅም በላይ ናቸዉ ብዬ ኣስባለሁ።

የቦረና ጎሳ እና የአኙዋ ጎሳ መገናኛ የሆነች ደምቢ ዶሎ ከተማ ዙርያ ተወላጁ ዮሓንስ ለታ የፕሮቴስታንት ክርስትያን ነኝ እያለ ሃይማኖት ሜንታል ድስኦርደር ነዉ እና ሃይማኖት አድቫንስድ ስሌቨሪ ነዉ የሚል ሆኗል።

ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ብቻ ተመከር።

ምክንያቱም የአኙዋ ጎሳ ስለ መለኮታዊ ነገር ግንዛቤ የማላዉቅ ብሆንም የቦረና ጎሳ ከጥንት ግዜ ጀምሮ መለኮታዊ አሰራር ስለ መኖሩ ግንዛቤዉ ባህሉ መሆኑን ኣዉቃለሁ።

ይህ ከሰሜን ኢትዮጵያ እስከ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ከምስራቅ ኢትዮጵያ እስከ ምዕራብ ኢትዮጵያ ባህላዊ ግንዛቤ ብቻ ሳይሆን የተደራጁ ሃይማኖች ግንዛቤም ነዉ።

በባህል ቃልቻ እና ቃሉ የሚባሉት ከፈጣሪ ጋር ግንኙንት ኣለን የሚሉ ናቸዉ።

ይህ ግንዛቤ የፈረዖዎች ዘመን ጀምሮ ስለ መኖሩ ታሪክ ተመራማሪዎች ደርሰዉበት ኣብራርተዋል።

በአድዋ ማግስት ኣዲስ ኪዳን ይዞ ደምቢ ዶሎ ደርሶ ስለ መለኮታዊ ነገር ላስተምራችሁ ያለዉ እንግሊዝ መሠረቱ የጥንት ኢትዮጵያ ዉስጥ ጀምሮ ስለኖረዉ መለኮታዊ ነገር ነዉ።

የዮሓንስ ኣባት በአደዋ ማግስት የፕሮቴስታንት ክርስትናን ከእንግሊዝ የተቀበለ ከሆነ ዮሓንስ ለታ ሁለተኛ ትዉልድ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ ይሆናል ማለት ነዉ።

ክርስትና የተወለደዉ የዚህ ዘመን ሁለት ሺህ ዓመታት ገደማ በፊት ነበር።

የእንግሊዝ ሞናርኪ ከተመሠረተ ወደ ኣንድ ሺህ ዓመታት ገደማ ሊሆነዉ ነዉ።

ስለዚህ ክርስትና የሁለት ሺህ ዓመታት ገደማ የመስበክ ልምድ፣ የእንግሊዝ ሞናርኪ የኣንድ ሺህ ያህል ገደማ የመግዛት ልምድ የላቸዉ ሲሆን የዮሓንስ ለታ ቤተሰብ የፕሮቴስታንት ክርስትናን መከተል የኣንድ መቶ ያህል ዓመታት ልምድ መሆኑ ነዉ።

የእኔ ግርምት ፊየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ እንደሚባለዉ በዚህ ኣጭር ግዜ ዉስጥ ሃይማኖት ሜንታል ድስኦርደር ነዉ እና አድቫንስድ ስሌቨሪ ነዉ ማለቱ ነዉ።

በአኙዋ ሕዝብ ባህል እንደ ቃልቻዎች እና ቃሉዎች ስለ መለኮታዊ ነገር እናዉቃለን የሚሉ መኖራቸዉን የማላዉቅ ብሆንም በኢትዮጵያ ታሪክ ገብረ ያሉ እና ገብረ የተባሉ ጎሳዎች መኖራቸዉን ኣዉቃለሁ።

ገብረ ማለት እና ገብረ መባል እኩልነት ኣልነበረም።

የሰዉ ልጅ ሁሉ እኩልነት ይስፈን በቅርብ ግዜ የተጀመረ እና ኣሁንም እየተካሄደ ያለ ትግል ነዉ።

የፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠስዋ ነገር ይህን የእኩልነት ትግልን የምያጨናግፍ እና ለዘላለም ትዝብት የሚዳርግ ይመስለኛል።

በእኔ አስተያየት ይህ ምክር ጥልቅ ነዉ።

ጥልቅነቱ ከተስተዋለ የእኩልነት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ለእኩልነት ኣስተዋጽኦ ማድረግ ያስፈልጋል ብዬ ኣስባለሁ።

ስለዚህ የእኔ ቀዳሚ ጥያቄ የአኙዋ ሕዝብ መለኮታዊ አሰራር ኣለ ብሎ ያምናል?

ያምናል ከሆነ ከአኙዋ ጎሳም የሚወለድ ዮሓንስ ለታ ሃይማኖት ሜንታል ድስኦርደር ነዉ እና አድቫንስድ ስሌቨሪ ነዉ ማለትን የሚገነዘበዉ እንዴት ነዉ?

የአኙዋ ሕዝብ ስለ መለኮታዊ አሰራር ግንዛቤ የሌለዉ ከሆነ ወይም ዬለም ብሎ የምያስብ ከሆነ የእኩልነት ትግሉን በጣም ዉስብስብ የምያደርግ ይሆናል።

ምክንያቱም መለኮታዊ አሰራር ኣለ ብሎ ማማን እና ዬለም ብሎ መኖር ሁለት ዓለማት ዉስጥ እንደ መኖር ነዉ።

ይህ ግለሰብ ስለ መለኮታዊ አሰራር ታሪክ እና ኣስተዉሎዎች ለዓመታት ሲመከር የኖረ ቢሆንም ቆም ብሎ የማስተዋል ዐቅም የተሳነዉ ይመስላል።

በቦረና ቋንቋ ገብረ ማለት፣ እልሞ ነማ ማለት፣ እልመ ነማ ልሚ እልሞ ነማ ህን ቀብኔ ማለት በጣም ጥልቅ አባባሎች ናቸዉ።

እልመ ነማ ልሚ እልሞ ነማ ህን ቀብኔ ማለት ቀጥታ ትርጉሙ እንደ ሰዉ ልጅ ያልለማ የሰዉ ልጅ ማለት ነዉ።

ይህ ሂስ ስለ ሰዉ ልጅ የህሊና ግንዛቤ ነዉ። ስለ ትህትና፣ ጩቡ፣ ግፍ ወዘተ ማወቅ እና ለህሊና መገዛት ነዉ። የጨዋነት ባህል ምንጭ ነዉ።

ይህ ግለሰብ የቅርብ ግዜ የኢትዮጵያ ፖለትካ ዉስጥ ቀዳሚ ተሳታፊዎች ኣንዱ ሲሆን ስለ ፖለትካዉ በርካታ ሂሶችን በአደባባይ ተጽፈዉ እንደኣነበባቸዉ መገመት ይቻላል።

ሁሌ ኣዉቃላሁ ማለት እንጂ ግልጽ የሆኑ ስህተቶቹን ስህተቶች ናቸዉ ማለት የማችል መሆኑ መካሪ ወይም ኣሳሪ ዬለዉም ወይ ያስብላል።

የዚህን ሰዉ ኣዉቃለሁ ማለት ኣለማወቅን ለመጀመርያ ግዜ ሳምቼ የታዘብኩት ኢትዮጵያ ኮሌጅ እያለሁ የሰማሁኝ ዜና ዉስጥ ነበረ። ቃል በቃል ባላስታዉም መማር እንፈልጋለን፣ ነገር ግን ከዚህ የተማርነዉ ምንም ዬለም የሚል ዐይነት ነገር ነበር።

መማር እንፈልጋለን ማለቱን ስሰማ ኣክብሬዉ ከዚህ ምንም የተማርነዉ ዬለም ማለቱን ስሰማ በቅጽበት እንድታዘበዉ ያደረገኝ ነዉ።

ይህ የሆነዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በኣብዮት ምክንያት ብዙ ኣዋቂዎች የተባሉት ረግፈዉ በደርግ ዘመን ብዙ ሳይተኩ የመንግስት ሽግግር የተደረገበት ዘመን ነበረ።

ለወደፊት የሰዉ ልጆች ይህ መለኮታዊ አሰራር መሆን ኣለበት የሚሉት ኣንድም ነገር ትሁን የምያስማማቸዉን ካገኙ ሃይማኖት ሜንታል ድስኦርደር ነዉ እና ሃይማኖት አድቫንስድ ስሌቨሪ ነዉ ያለዉ የዘላለም ትዝብት ዉስጥ ይወድቃል ማለት ነዉ።

ዱረቱ ዱረቲ ያጉረ ዱበርቲ እንደተባለዉ እንዳይሆን ወንድምህን ወይ ምከረዉ ወይም እሰረዉ።

ኣንተም እንደ እሱ ሃይማኖት ሜንታል ድስኦርደር ነዉ እና አድቫንስድ ስሌቨሪ ነዉ ብለህ የምታስብ ከሆነ የምንኖረዉ የተለያየ ዓለማት ዉስጥ ነዉ ማለት ነዉ።