Mereja.Forum
https://mereja.forum/content/
ADDIS ABABA IN VIVALDI'S FOUR SEASONS!
https://mereja.forum/content/viewtopic.php?f=2&t=377561
Page
1
of
1
ADDIS ABABA IN VIVALDI'S FOUR SEASONS!
Posted:
23 Mar 2026, 11:24
by
Horus
ኮሪደር የተሰራለት ያዲሳባ በልግ ዝናብ! PURE BEAUTY!
Re: ADDIS ABABA IN VIVALDI'S FOUR SEASONS!
Posted:
23 Mar 2026, 11:30
by
Horus
Re: ADDIS ABABA IN VIVALDI'S FOUR SEASONS!
Posted:
23 Mar 2026, 11:42
by
sesame
In the meantime, the country is crumbling faster than we expected. The 99.99% of Ethiopians who never heard of Vivaldi are now living like dogs, not European dogs, but ethiopian dogs
ምክትል ጠ/ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የትውልድ መንደሩ እነማይ መሄድ አይችልም። በአካባቢው ምርጫም መወዳደር አልቻለም። የእሱ የትውልድ ቦታ በፋኖ ቁጥጥር ስር ሲሆን መፍትሔ ታጥቶ ፣ ሁኔታው ከአቅሙ በላይ ሲሆን በመጨረሻም ባህርዳር ሄዶ ምርጫ ለመወዳደር ወስኗል።
https://www.facebook.com/share/p/1CXeWturTU/
https://pbs.twimg.com/media/HED5uAkWIAA ... name=large
Re: ADDIS ABABA IN VIVALDI'S FOUR SEASONS!
Posted:
23 Mar 2026, 18:34
by
sesame
HorseShit,
See how smart people evaluate the uselessness of your corridors!
Finfinne Press
7h
በተሳሳተ #የብልጽግና ፖሊሲ ምክንያት ታክሞ መዳን እና ህይወትን ማራዘም በሚቻል በሽታዎች ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸው በየወሩ እየተ ቀጠፈ ይገኛሉ
===================================
በቢሊዮን የሚቆጠር መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ በማድረግ የቅንጦት ሪዞርቶችን እና ሎጅዎችን እየገነባ የሚገኘው አገዛዙ፤ በሌላ በኩል ግን ታካሚዎች በሆስፒታል ኮሪደር፣ ለህክምና ወረፋ እየጠበቁ ባሉበት በቤታቸው ውስጥ ህክምና ሳያገኙ ህይወታቸው እያለፈ ይገኛል።
ይህ የሀብት እጥረት ብቻ አይደለም፤ ቅድሚያ የሚሰጠውን ሴክተር አለማወቅ እንጂ። የቅንጦት ሎጅ ወይስ የህዝብ መገልገያ ሆስፒታል ይቅደም የሚለውን አለመለየት ነው።
ከ120 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ባለባት አገር ውስጥ፦
⛓ አንድ የልብ ቀዶ ህክምና ማዕከል ብቻ ይገኛል፤
⛓ የካንሰር ታካሚዎች ለTACE፣ ኬሞቴራፒ እና ሬዲዮቴራፒ ረጅም ጊዜ ወረፋ ይጠብቃሉ፣
⛓ የኒዮሮሰርጀሪ (የቅንጭላት ቀዶ-ህክምና) ፤ የኩላሊት ዕጥበት (Dialysis) እና ሌሎች የህክምና አገልግሎቶችን ማግኘት ሀገራችን ውስጥ ቅንጦት ሆኖል።
⛓ እናቶችና አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ህፃናት አሁን ድረስ ማከም በሚቻል በሽታ ህይወታቸው ይቀጠፋል።
ይህ አልፎ አልፎ የሚከሰት ጉዳይ አይደለም፤ የቀን ተቀን የሀገራችን እውነታ እንጂ። ታካሚዎች የሚሰጣቸው ቀጠሮ ረጅም በመሆኑ ምክንያት ለቀጠሮ ቀናቸው ሳይደርሱ ህይወታቸው ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ የሚያልፍ ዜጎች ቁጥር እጅግ ብዙ ነው።
በዚህን ጊዜ ግን በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በቅንጦት ፕሮጀክቶች ላይ እየተረጨ ፤የራስ ዜጋን ለመጨፍጨፊያ ድሮንን እና ተተኳሽ ላይ ፈሰስ እየተደረገ ይገኛል።
እውነታውን በደንብ ግልፅ ሳደርገው፦
🕸 ሪዞርት፦ የሆስፒታል አልጋን አይተካም !
🕸 ሎጅ፦ የሕይወት አድን ቀዶ ህክምና አይሰጥም!
🕸 የውበት ፕሮጀክት፣ ኮሪደር ልማት ፦ የካንሰር ህክምናን አይተካም!
ሕዝብ እየተሰቃየ፣ እየሞተ የሚከናወን ቅንጡ ፕሮጀክት ልማት አይደለም ፤ Ignorance ነው
እኔ ልማትን እየተቃወምኩ አይደለም፤ የተሳሳተ ፖሊሲን Criticized እያደረኩ ነው! ቅድሚያ የሚሰጠውን ችላ በማለት፤ የቅንጦት ፕሮጀክቶችን ማስቀደምን ፤ የርስ በርስ ጦርነት ላይ የሙጥኝ ማለትን እየተቃወምኩ ነው።
ሕዝቡ በእየቀኑ በሚድን በሽታ ህይወቱን እያጣ ባለበት ሰዓት የቅንጦት ፕሮጀክቶችን የሚገነባ መንግስት በደንብ መጠየቅ አለበት!
Healthcare is not a privilege. It is a right !
ህይወትን የሚያድኑ አገልግሎቶች በሰፊው እስኪሰራጩ ፣ Subspecialist & Specialist ሐኪሞች ቁጥራቸው በደንብ እስኪጨምር እና Brain drainage እስኪቀንስ፣ በቀጠሮ ዝርዝር ውስጥ ያሉ ታካሚዎች ቤታቸው መሞታቸው እስኪቆም ድረስ የሚገነቡ ቅንጡ ፕሮጀክቶች በየትኛውም መመዘኛ ምክንያታዊ ሊሆኑ አይችሉም !
Dr. Henok Abraham @highlight
.