Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11601
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

የአዲስ አበባ ሆቴሎች ወደ ሆስፒታል እየተቀየሩ ነዉ

Post by MINILIK SALSAWI » 11 Mar 2026, 22:22

አዲስ አበባን በአካል ከጎበኟት ሰነባብተው ከሆነ፣ የሚወዱትና የሚያውቁት ሆቴል ዛሬ የሕክምና ማዕከል ሆኖ ሊያገኙትይችላሉ የአዲስ አበባ ሆቴሎች ከመስተንግዶ ወደ ህክምና የ"አልጋ" ተሽጋግረዋል።

በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ሆቴሎች በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ሆስፒታልነት እየተቀየሩ ይገኛሉ። ይህ ከአልጋ ወደአልጋ የሚደረግ ሽግግር በከተማዋ ገጽታና በኢኮኖሚው ላይ ምን ይዞ ሊመጣ እንደሚችል በሄደት የሚታይ ቢሆንም የአዲስ አበባ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ አዲስ ክስተት እያስተናገደ ነው። በአንድ ወቅት የቱሪስቶች መዳረሻ የነበሩ፣በድግስና በደስታ ድምፅ የታወቁ ሕንፃዎች፣ ዛሬ መልካቸውንና ቀለማቸውን ቀይረው የነጭ ጋውን የለበሱባለሙያዎችና የሕመምተኞች መጠለያ ሆነዋል። ይህ ድንገተኛ ለውጥ ግን በአጋጣሚ የመጣ አይደለም።በዚህ የንግድዘርፍ ሽግግር ውስጥ ስማቸው የገነነ ሆቴሎች ተጠቃሾች ናቸው አፋርነስ ሆቴል ዛሬ 120 አልጋዎች ያሉት ላንሴትአጠቃላይ ሆስፒታል ሆኗል።በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የነበረው ስካይጌት ሆቴል አሁን ኢትዮ ኢስታንቡልሆስፒታል ሆኖ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው

የኦፍሪካ አንድነት ድርጅት አሁን የአፍሪካ ህብረት ምስረታ ታሪክ ምስክር የሆነው ሀራምቤ ሆቴል ታሪካዊ ሕንፃ፣ በ300 ሚሊዮን ብር ወጪ ወደ ቅዱስ ዑራኤል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ እየተሸጋገረ ይገኛል። ዮርዳኖስ ሆቴል ወደመቅረዝ ሆስፒታል፣ በሻሌ ሆቴል ደግሞ በዋሽንግተን ሄልዝ ኬር በሚል የህክምና ማእከል ሆንዋል።

የኢትዮጵያ ሆቴልና ቱሪዝም አሠሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ዶክተር ፍትህ ወልደሰንበት እንደሚሉት፣ ‘’የኮቪድ-19 ወረርሽኝና የሰላም እጦት የቱሪዝሙን ዘርፍ ክፉኛ መትተውታል። ሆቴሎች ገቢ አጡ፤ የባንክ ዕዳ ግን አላቆመም።በአገሪቱ አብዛኛው ባለሀብት በባንክ ብድር የሚንቀሳቀስ በመሆኑ፣ ባለቤቶች የባንክ ወለድና የማስኬጃ ወጪዎችንመሸከም ሲያቅታቸው ፊታቸውን ወደ ይበልጥ ትርፋማውና አስተማማኙ የጤና ዘርፍ አዙረዋል”። ይላሉ


የሆቴል ሕንፃዎች ግንባታ፣ የመኝታ ክፍሎች አወቃቀርና የውኃ መስመሮች ለሕክምና ተቋምነት ምቹ በመሆናቸው፣አዲስ ሕንፃ ከመገንባት ይልቅ ነባር ሆቴልን ማደስ ወጪንና ጊዜን በእጅጉ ቆጣቢ ሆኖ ተገኝቷል። ሲሉ ለ ዶቼቪሌተናግረዋል
ሆኖም ይህ ሽግግር ሌላ ስጋት ደቅኗል። ኢትዮጵያ በቅርቡ አስተናግዳዋለሁ ለምትለው ዓለም አቀፍ የኮፕ COP ስብሰባየሚመጡ እንግዶችን ለማስተናገድ በቂ የሆነ ማረፊያ ላይኖር ይችላል የሚሉ ስጋቶች እየተደመጡ ይገኛሉ።እንደ ዶክተርፍትህ ገለጻ፣ ብዙ ሆቴሎች ጊዜው ያለፈባቸውና በብድር የተተበተቡ በመሆናቸው ወደ ሆስፒታልነት መቀየር ብቸኛውየሕልውና አማራጭ ሆኖላቸዋል። ይሁን እንጂ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቱሪዝሙ እያገገመ በመሆኑ ይህ ሁኔታ ጊዜያዊሊሆን ይችላል ብለዋል።