Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7313
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ኣንድ የሚደነቅ የሂሳብ ቀመር

Post by Naga Tuma » 11 Mar 2026, 01:48

ሂሳብ ከባድ ትምህርት ነዉ ይባላል።

በወጣትነቴ ከሁሉም ትምህርት በላይ የምወደዉ ነበር።

ኢትዮጵያ ሂሳብ የወደድኩኝ አሜሪካ ደርሼ ኦፕሬሽንስ ሪሰርች ወይም እንደስትርያል እንጂነርንግን ጨምሬ ተማርኩኝ።

ለሃገር ይጠቅማል ብዬ ተሯሩጬ ለማስተርስ ድግሪ የምያበቃ ያህል ኮርሶችን ከሙያዬ ዉጪ ተማርኩኝ።

እቅዴ ትምህርቴን እንደዋስትና ይዤ በዕድሜ የገፉ ወላጆቼ ቅርብ እና ወደ አካዳሚ ስራዬ መመለስ ነበር።

ኦፕሬሽንስ ሪሰርች ወይም እንደስትርያል እንጂነሪንግ ስለ ሊኒየር ፕሮግራምንግ፣ ነን ሊኒየር ፕሮግራምንግ፣ እንቲጀር ፕሮግራሚንግ፣ ስቶካስትክ ስሙሌሽንስ ያስተምራል።

እነዚህ ከባድ የትምህርት መስኮች የወሬ ተማሪ እና በወሬ ወራሪ እሺሩሩ የሚሉት ሳይሆኑ ኣዕምሮ ያላቸዉ ብቻ ደፍረዉ የሚወስዷቸዉ እና የምያልፏቸዉ ናቸዉ።

በርካታ የኦፕሬሽንስ ሪሰርች ኮርሶችን ከወሰድኩ በኋላ ባስታወስኩት ቁጥር የሚደንቀኝን ሂሰብ ቀምሬ ፈታሁት ወይም ፎርሙሌት ኣድርጌ ሶልቭ ማድረግ ቻልኩኝ ማለት ነዉ።

ነን ሊኒየር ፕሮግራሚምግ እና እንቲጀር ፕሮግራሚንግን ጎን ለጎን ኣድርጌ ሚክስድ እንቲጀር ነን ሊኒየር ፕሮግራሚንግ ቀመርኩኝ።

ቀመሩን ተራ በተራ ለመፍታት ብረት ሲቀልጥ ጠንካራ ብረት እንዲሆን የማድረግ ሲሙሌትድ አኒልንግ የሚባል ዘዴ ተጠቀምኩኝ።

ቀመሩን ሰርቼ ከፈታሁኝ በኋላ ኣንድ ቀን ኣማካሪዬ ቢሮዬ መጥቶ ሲጠይቀኝ እንደተሳካልኝ ነገርኩት።

ከሰማ በኋላ እንዴት ኣተኩሮ እንዳየኝ ከፊቴ ኣይጠፋም። እንደዛ ኣተኩሮ ያየኝን ሌላ ሰዉ ኣላስታዉስም።

ለምን እንደዛ ኣተኩሮ እንዳየኝም ይህ ነዉ ማለት ያስቸግረኛል። የእኔ ግምት ይህን ያህል ድንቅ ሂሳብ ቀምረህ የፈታህ ኣንተ ማን ነህ የሚል ዐይነት ነበር።

እሱ በምህንድስና ሙያ በጣም የታወቀ እና በጣም የማከብረዉ ቢሆንም ድንቁን የሂሳብ ቀመር ቀምሬ የፈታሁኝ የእንደስትርያል እንጂነሪግ ትምህርት ስወስድ ነበር።

ስለዚህ ድንቅ ቀመሩ እና መፍታቱ ዉስጥ ሚና እንዳልነበረዉ ኣዉቃለሁ።

ድንቅ ቀመሩን እና አፈታቱን ለመጀመርያ ግዜ ያቀረብኩኝ የስታምፎርድ ዩኒቨርዚቲ ምሩቅ የእንደስትሪያል እንጂነሪግ ትምህርት ኣስተማሪ እንድንሰራ ለጠየቀዉ የየግል ፕሮጀክት ነበር።

ቀመሩ ከሁሉም በላይ ገብቶት ያደነቀዉ ያ ፕሮፌሰር ነበር።

ነን ሊኒየር ፕሮግራሚንግ ቀልድ ኣይዴለም። እንቲጀር ፕሮግራሚንግ ቀልድ ኣይዴለም። ሲሙሌትድ አኒልንግ ቀልድ ኣይዴለም።

ሶስቱንም ያጣመረ ሂሳብ ቀምሮ መፍታትን ማድነቅ እራሴን ማድነቅ ይሆንብኛል።

ለወደፊት ይህን ያህል ድንቅ የሂሳብ ቀመር ቀምረዉ መፍታት የሚችሉ ቢወለዱ ምኞት ይሆንልኛል።