Page 1 of 1
የተፈፀመ የሙሴ ትንቢት ኣለ ከተባለ ፈረዖ አክናተን ትንቢት የነበረዉ ሊሆን ይችላል?
Posted: 07 Mar 2026, 17:27
by Naga Tuma
እዚህ መድረክ ላይ መላልሼ እንደጻፍኩኝ እኔ ስለመለኮታዊ ነገሮች ያጠና እና ዕዉቀት ያለዉ ሰዉ ኣይዴለሁም።
ከብዙ ዓመታት በፊት ሰምቻቸዉ የሰዉ ግምት እና የተሳሳቱ አስተሳሰቦች ናቸዉ ብዬ ያለፍኩዋቸዉ ኣሉ።
ሁለቱ የማልረሳቸዉ ኣንዱ በወቅቱ የድፕሎማ ትምህርት ደረጃ የነበረዉ እስልምና ተከታይ የሐረርጌ ሰዉ ነበር። ከኣሁን በፊት ነብዮች እንደተወለዱት ለወደፊትም ነብይ ይወለዳል ወይም ሊወለድ ይችላል የሚል ነበር።
ሌላዉ ኣንድ ቀን ብቻ በስልክ ያናገረኝ እስልምና ተከታይ የባሌ ሰዉ ነበር። ኣንድ ኣዲስ ድርጅት ዉስጥ ተሳትፎ ስለኣቆምኩ በዛ ምክንያት ስንወያይ የሰዉ ልጅ መንገድ በመለኮታዊ አሰራር የሚመራ ነዉ የሚል ነበር። እንደዛ ዐይነት አስተሳሰብ ከዛ በፊት ሆነ ከዛ በኋላ ሰምቼ ኣላዉቅም።
ስለ መለኮታዊ አሰራር ያላጠናሁ ብሆንም የማነባቸዉ እና የምገነዘባቸዉ ሌሎች ሰዎች ከሚገልጹበት ጋር ተመሳሳዮች ኣሉ። ትይዩ የሆኑ ነገሮችም ኣሉ።
ያላመለኮታዊ አሰራር ማብራራት የማይቻሉ ታሪኮችን ተገንዝቤኣለሁ የሚል ሰዉ ነኝ።
ከኣሁን በፊት ኤርትራ በሚል ስም ከሚሳተፍ ሰዉ ጋር የማይረሳ ዉይይት ኣድርጌኣለሁ።
የተጻፉ ትንቢቶች እየተፈፀሙ ያሉበት ዘመን ላይ ነን የሚል አስተሳሰብ ኣለዉ።
አስተሳሰቡን ሳልቃወም እሱ ይታየኛል የሚለዉ መንገድ እና የእኔ ግንዛቤ መንገድ የተለያዩ ይመስላሉ ብዬዉ ነበር።
ተጨማሪ በሆኑ ነገሮች ምክንያት ከስደት በኋላ ፕሮፌት ሙሴ የተባለዉ ከስደት በፊት ታላቅ ፈረዖ አከናተን ከሆነ፣ የተፈፀመ የሙሴ ትንቢት የተባለዉ ያልተፈፀመ እና የሚፈፀም የፈረዖ አክናተን ትንቢት ሊሆን ይችላል ወይ እያልኩ ነዉ።
ይህ አስተሳሰብ የምያሳምነዉ ሌላ ሰዉ ኣለ ወይ?
Re: የተፈፀመ የሙሴ ትንቢት ኣለ ከተባለ ፈረዖ አክናተን ትንቢት የነበረዉ ሊሆን ይችላል?
Posted: 08 Mar 2026, 19:46
by Naga Tuma
Re: የተፈፀመ የሙሴ ትንቢት ኣለ ከተባለ ፈረዖ አክናተን ትንቢት የነበረዉ ሊሆን ይችላል?
Posted: 08 Mar 2026, 19:59
by Naga Tuma
ነምን ህን ሶበ፣ ኡርጂን ህን ሶቡ ኣለ የቦረና ሰዉ ደበሳ ጉዮ።
የክርስትና ታሪክ ከፈረዖዎች ታሪክ የተሰረቀ ነዉ ከተባለ የፈረዖዎች ታሪክ ሆነ ኣሁንም ያልተገነዘበ ያታላቁ ፈረዖ ትንቢት ያለ ከሆነ ታሪኩ የሚጻፈዉ እና ትንቢቱ የሚገለጠዉ ወደ ፊት ነዉ ማለት ኣይቻልም?
Re: የተፈፀመ የሙሴ ትንቢት ኣለ ከተባለ ፈረዖ አክናተን ትንቢት የነበረዉ ሊሆን ይችላል?
Posted: 11 Apr 2026, 12:29
by Naga Tuma
ይህ ጥያቄዬ ጥልቅ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።
ሁለት እርስ በእርስ የማይተዋወቁ ሰዎች፣ ማለትም eritrea እና እኔ፣ የዚህን ዘመን ክስተቶችን ኣስተዉለን የመለኮታዊ አሰራር ኣመልካቾች ይመስላሉ ካልን ሁለታችንም መለኮታዊ አሰራር መኖሩን የምንገነዘብ ነን ማለት ይቻላል።
ክስተቶቹ ወደ ተለያዩ ኣቅጣጫዎች ኣመልካቾች ናቸዉ የምንል ከሆነ ያልተመለሰ ጥያቄ ኣለ ማለት ነዉ።
ኣይዴለም?
Re: የተፈፀመ የሙሴ ትንቢት ኣለ ከተባለ ፈረዖ አክናተን ትንቢት የነበረዉ ሊሆን ይችላል?
Posted: 20 Apr 2026, 21:59
by Naga Tuma
ብዙዎች ዓመታትን ወደ ኋላ እያየሁ እና የዚህን ግዜ ዉሎዎችን እያስተዋልኩ ዐለምን ሁሉ ኣሳማኝ ሊሆን የሚችል መለኮታዊ ክስተት በኢትዮጵያ በኩል እየተፈጸመ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።
ይህ የዚህ ዘመን መለኮታዊ ክስተት በጥንታዊ የኢትዮጵያ ፈረዖዎች በኩል እና በጥንታዊ የኢትዮጵያ ቦረናዎች በኩል ሆኖ ክርስትናን ጡረታ የምያወጣ እና ፈርሃ እግዝኣብሔርነትን በዐለም ላይ የምያነግስ ሊሆን ይችላል ብዬ ኣስባለሁ።
በዚህም ምክንያቶች የተገለጡልኝ የምላቸዉን ወይም የሚመስሉኝን ስመክር ሰንብቻለሁ።
ይህ ምክሬ ለብዙዎች የኣንድ ግለሰብ ምናብ እንደመሰላቸዉ እገምታለሁ።
እኔ ስመክር የሰነበትኩኝ ኣንድ ፐርሰንት እንኳን ትክክል ከሆነ እና የኣንድ ግለሰብ ምናብ ናቸዉ የሚሉት ዘጠና ዘጠኝ ፐርሰንት ትክክል ከሆኑ የሚወስዱት ርስክ እንፍኒቲ ነዉ።
ምክንያቱም ዬለም ያሉት ኣለ ከተባለ ኣንድ ፐርሰንትም ቢሆን በእንፊኒቲ ሲባዛ ዉጤቱ እንፍኒቲ ነዉ።
ስለዚህ የራሳቸዉን ሴናርዮ ብቻ ከማራመድ ሁለቱንም ሴናሪዮዎች ጎን ለጎን ማራመድ ይቻላል።
ስለ መለኮታዊ ክስተቶች ምልክቶችን ማወቅ የሚችሉት ቃሉዎች፣ ቄሶች፣ ሼሆች፣ ወዘተ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።
ስለ መለኮታዊ ክስተቶች ያላቸዉ ዕዉቀት ለሺህዎች ዘመናት ባህል ሆነዉ የኖሩ ስለሆነ ብዙዎቹ ያልተጠኑ ስህተቶች ይሆናሉ።
ቢሆንም ሳይናቁ ቢጠኑ ኣንድ ቃሉ ወይም ቄስ ወይም ሼህ ስለ መለኮታዊ ክስተት ምልክቶች መቶ ነገሮችን ቢናገር ምናልባት ኣንዱ ኣሳማኝ ሊሆን ይችላል ብዬ ኣስባለሁ።
ኣንድ ኣሳማኝ የሆነ ምልክት ከተገኘ ለሌሎች ምልክቶች ጥናት ሆነ ማለት ነዉ።
ኣንድ ከተስተዋለ የመለኮታዊ ተዓምራዊ አሰራር ስክሪፕት ተገኘ ማለት ነዉ።
Re: የተፈፀመ የሙሴ ትንቢት ኣለ ከተባለ ፈረዖ አክናተን ትንቢት የነበረዉ ሊሆን ይችላል?
Posted: 20 Apr 2026, 22:33
by Naga Tuma
የተፈጸመ የሙሴ ትንቢት ያልተፈጸመ የፈረዖ አክናተን ትንቢት ሊሆን ይችላል ወይ ለማለት ምክንያቶች ዉስጥ ሁለቱ፥
ኣንዱ የዚህ ዘመን ክስተቶች በመላዉ ዐለም ኢን ሪል ታይም መሆናቸዉ ነዉ።
ሌላዉ የሃይማኖት ትምህርቱ ከክርስትና ጋር ተፎካካሪ የነበረዉ የፐርሽያዉ ፕሮፌት ማኒ ስም በዚህ ዘመን መነሳት ነዉ።
አክናተን ማለት አሙን ኢዝ ሳቲስፋይድ ማለት ነዉ።
ስለዚህ ይህ ርዕስ ሁለት የጥንት ነብዮችን ወይም ፕሮፎቶችን ይመለከታል።
የሁለቱም ፕሮፌቶች ስሞች በዚህ ዘመን መነሳት ክስተት ነዉ ወይ ያስብላል።
Re: የተፈፀመ የሙሴ ትንቢት ኣለ ከተባለ ፈረዖ አክናተን ትንቢት የነበረዉ ሊሆን ይችላል?
Posted: 10 Jun 2026, 22:29
by Naga Tuma
ምድር ላይ የአሓዱ ኣምላክ የመጀመርያዉ መሪ የጥንት ኢትዮጵያ ነብይ የነበረ ለመሆኑ የታሪክ ምስክርነት ኣለ።
መለኮታዊ ስምርት የነበረ መሆኑን ሆነ ኣለመሆኑን መናገር ያስቸግራል።
ያ የጥንት ኢትዮጵያ ነብይ አሓዱ ኣምላክ ካለ በኋላ ለስደት መዳረጉም ታሪክ እና የሃይማኖት መጽሓፍ ምስክሮች ናቸዉ።
በዛን ዘመን እግዝኣብሔር ተገልጦለት ነበር የተባለዉ ያዉ የጥንት ኢትዮጵያ ነብይ ነዉ።
አክሱማዊያን በእግዝኣብሔር ፈቃድ የተረገማችሁ ናችሁ ማለትን የሰሙት ከዛ ዘመን በኋላ ነበር።
ይህ ልያመለክት የሚችለዉ እርግማን ነበረ ከተባለ ንስሃም ነበረ ማለትን ይሆናል።
ይህ ማለት ደግሞ ኢትዮጵያ ያለባት ንስሃ ነበረ ከተባለ የአሓዱ ኣምላክ ስደት ንስሃ ይሆናል ማለት ይቻላል።
ኢትዮጵያ የስቅለት ንስሃ ዬለባትም።
ስለዚህ ለኢትዮጵያ ዓመተ ምህረት ለስደቱ እርግማን ንስሃ እንጂ ለስቅለት ንስሃ ነዉ ማለት የምያስቸግር ይመስላኛል።
አሓዱ ኣምላክ ማለት ለስደት ዳርጎ ኖሮ በዚህ ዘመን ደግሞ ይባስ ብሎ እግዝኣብሔር ኣለ ብሎ ማሰብ የኣዕምሮ መቃወስ ነዉ ባይ ተከሰተ።
በእኔ ኣሰላሰል ይህ ዘመን እግዝኣብሔር ተዓምራትን እያስቆጠረ መለኮታዊ አሰራር መኖሩ የተገለጠበት ዘመን ነዉ።
ምናልባት በእግዝኣብሔር ፈቃድ የተረገማችሁ ማለት መለኮታዊ የነበረ ከሆነ ምህረቱ በዚህ ዘመን መዉረዱ ኣሳማኝ ይሆናል።
ምልክቶቹ ይህን የማያመለክቱ ከሆነ ሌላ የምያመለክቱት ምን ሊሆን ይችላል?
Re: የተፈፀመ የሙሴ ትንቢት ኣለ ከተባለ ፈረዖ አክናተን ትንቢት የነበረዉ ሊሆን ይችላል?
Posted: 11 Jun 2026, 17:18
by Naga Tuma
ጥንታዊ ኢትዮጵያ ብርሃን ብሎ አሓዱ ኣምላክ ያለ ነብይ ነበራት እንጂ ሙሴ ተብሎ የኢትዮጵያ ነብይ የሆነ በፍጹም ዬለም።
ስለዚህ ኢትዮጵያ የአሓዱ ኣምላክ ዳግማዊ ነብይ ብላ እንደገና ብርሃን የምታይ ቢሆን እንጂ ዳግማዊ የኢትዮጵያ ሙሴ ማለት በፍጹም ኣትችልም።
ሰኔ ቀን 3፣ 2018፣ ዓም