Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11607
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

የአማራ ህዝብ ላይ የድሮን ቦንብ ለሚያዘንቡ ወታደሮቿ ከዱባይ እና ከአቡዳቢ ደብረ ዘይት እና ባህር ዳር ድረስ በአውሮፕላን የሚመጡ ትኩስ ምግቦች በግዜው መድረስ አልቻሉም።

Post by MINILIK SALSAWI » 05 Mar 2026, 09:30

የኢራን ሚሳኢሎች ብዙ ነገር ለውጠዋል። በሚሳኢሎቹ ምክንያት ኢማራት የአየር ክልሏን በመዝጋቷ የአማራ ህዝብ ላይ የድሮን ቦንብ ለሚያዘንቡ ወታደሮቿ ከዱባይ እና ከአቡዳቢ ደብረ ዘይት እና ባህር ዳር ድረስ በአውሮፕላን የሚመጡ ትኩስ ምግቦች በግዜው መድረስ አልቻሉም። ጀነራል ሐሰንን ጨምሮ የኢማራት ድሮን ተኳሾች እና ቴክኒሻኖች ለሰሞኑ የኢትዮጵያን ምግብ መልመድ ግድ ሊሆንባቸው ነው።

ወደ ገራህ ቆፍር እንደሚባለው ወደ ቀናው የሚጓዘው የአብይ አህመድ ወራሪ ጦር ለሳምንታት ተጉዞ ከተከማቸበት የትግራይ እና የአማራ ክልል ድንበር አካባቢ በከፊል ተቀንሶ ወደ መሃል አገር ጉዞ ጀምሯል።

በነገራችን ላይ አብይ ወደ ቆቦ፣ ሰቆጣ፣ ወደ ደባርቅ ኃይል ያጠራቀመው ሰሜኖች ከበው ሊያጠፉኝ ስለሆነ መከላከል አለብኝ ብሎ እንጅ አቅዶ ያደረገው ስምሪት አይደለም። በዛው አጋጣሚም እያስፈራራ ሽምግልና ሊቀመጥ ነበር ሰሚ ጠፋ። አሁን ከምርኮ የተረፈውን ሰራዊቱን እያንከራተተው ነው። ሰውዬው ሀገር እና ኮሪደር፣ ሰራዊት እና አራዊት ተምታቶበታል።

አሰብም ወደ ሃሳብ ተለውጧል፤ የቀይ ባህር ምኞትም እንደ ጉም ተኗል። ጌታቸው ረዳ፣ ደመቀ ዘውዱ፣ ሜላት ኃይሉ እና አገኘው ተሻገር የተባሉ አገልጋዮቹን በአንድ መዝገብ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ላይ ያገናኘው አብይ አህመድን አምኖ የሚከተል ሁሉ እጣ ፋንታው መክሸፍ ብቻ ነው። አስረስ ማረ ዳምጤ