Page 1 of 3
ቆምጬ
Posted: 04 Mar 2026, 10:01
by Selam/
ገራገሩ ቆምጬ እንደምን ከርመሃል
ስትፀልይ ከልብህ ወፎች ይሰሙሃል
ፎጣም ልበስ ቁምጣ ሁሉም ያምርብሃል
ግርማና እርጋታህ መንፈስን ያረካል
የምቀኛን ቅስም ይሰብራል ይገድላል
ጮማም ብላ ጥሬ ፈገግታህ ያስቀናል
ለአናሳ ጎጠኞች ደም ፍላት ይሰጣል
ሲመሽም ሲነጋም ስምህን ያነሱታል
Re: ቆምጬ
Posted: 04 Mar 2026, 18:41
by Selam/
Re: ቆምጬ
Posted: 04 Mar 2026, 19:12
by Axumezana
ቆምጬ ታታሪ ነው አገር ይቀልባል
አአ አትግባ ቢሉት በርግዶ ይገባል
አገር ነፃ አውጥቶ ፍትህን ያነግሳል
ናቂ ውዳቂ ነው ተቀምጦ ያገሳል
Re: ቆምጬ
Posted: 04 Mar 2026, 19:13
by Selam/
Re: ቆምጬ
Posted: 04 Mar 2026, 19:26
by Misraq
ቆምጬ ገራገሩ ያገር ጠባቂው
ረሃብ ቸነፈር ግፍ ያልበገረው
ቂምን የማይቋጥር መቻቻል ባህሉ
አግብቶ ተጋብቶ በሃገሩ ሁሉ
ሕዝብን አንድ አድርጎ በድንቅ ባህሉ
ይኖረው ነበረ በሃገሩ ሁሉ
Re: ቆምጬ
Posted: 04 Mar 2026, 19:44
by Selam/
ደጉ ገራገሩ ፣ ቆምጬ ባላገሩ
ቢያጣ ቢገረጣ ፣ ፈገግታው ማማሩ
ዕኩል ሁሉን የሚያይ ፣ ስብዕናው ኩሩ
ጎጠኛ ሲንጫጫ ፣ ሲያፍር በሃገሩ
ባለ ቁምጣው ጎበዝ ፣ ጅንን ስመ ጥሩ

Re: ቆምጬ
Posted: 04 Mar 2026, 19:52
by Selam/
Re: ቆምጬ
Posted: 05 Mar 2026, 03:30
by Meleket
በምድር እያለ በሰማይ ላይ ኗሪ፡
በምድር እያለ እንደሰማይ ኗሪ፡
አምላክና ሰውን ሁሉንም አክባሪ፡
ንጹህና ቅዱስ ሃብቱ ለፈጣሪ፡
ቆምጬ እንደሆነ እኛ ነን መስካሪ።
ተጻፈ በኛ በኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
Re: ቆምጬ
Posted: 05 Mar 2026, 09:55
by Selam/
ቆምጬ በቀደሰው ባርኮ በመረቀው
ሳይማር በልቡ ፈጣሪን ባመነው
ጎጠኛ ዕንቅልፍ አጣ ጨነቀው ጠበበው

Re: ቆምጬ
Posted: 06 Mar 2026, 09:15
by Selam/
ሺ ተንኮል ቢያስቡ ፣ ጎጠኞች ቢያሴሩ
ከተፈጥሮ ፀጋው ፣ ሊያወርዱት ቢጥሩ
ቆምጬው ባላገሩ ፣ በሃገሩ ኩሩ
ሁሉን ሰው አክባሪ ፣ ትህትናው ጥሩ
Re: ቆምጬ
Posted: 06 Mar 2026, 09:41
by Meleket
“ቆምጬ ቆምጬ” እያሉ ሊያጥላሉት ሞከሩ፡
እነ አውርቶ-አደር፡ እነ ስራ አይሰሩ!
ምላሳቸው ረዝሞ እነ ቆርጦ ቀጥል፡
ቆምጬን ቢያጥላሉትም ሆኖባቸው አመል፡
እሱ ግን፡ ምን ግዱ፡ ቀንበር ተሸክሞ፡
ለከተሜው ምቾት ገጠር ላይ ከትሞ፡
ደማቁን ፈገግታ ከአምላክ ተሸልሞ፡
አርሶ-አጭዶ አበላቸው አሁንም ደጋግሞ።
ተጻፈ በኛ በኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
Re: ቆምጬ
Posted: 06 Mar 2026, 10:39
by Dama
Each of you above carry lots of pain inflicted by each of you against each other. Pains engraved on loss of lands one to the other. In addition, Human remains killed by each other remain unburried and strewn across plains, valleys and mountains.
Regardless, you came together to rehabilitate a character destroyed for good reasons by Odie from Gurage.
I got your notice that despite your grave losses to each other, you would gang up against Gurage when it fights Amara oppression. That Gurage to each of you is an alien enemy clearly proving your racism and xenophobia. That you would oppress and dehumanize Gurage together.
Re: ቆምጬ
Posted: 06 Mar 2026, 10:44
by Selam/
የህዝቦቼ አንድነት ፣ ዕንቅልፍ የነሳቸው
ኢትዮጵያን ማናከስ ፣ ያረጉ ዓላማቸው
የጥላቻ ወባ ፣ ያርገፈገፋቸው
ቆምጭዬን ከማማው ፣ ሊያወርዱ አማራቸው
መቋጠሪያው ውሉ ፣ መሆኑ ጠፍቷቸው
Re: ቆምጬ
Posted: 06 Mar 2026, 10:55
by Dama
Selam/ wrote: ↑06 Mar 2026, 10:44
የህዝቦቼ አንድነት ፣ ዕንቅልፍ የነሳቸው
ኢትዮጵያን ማናከስ ፣ ያረጉ ዓላማቸው
የጥላቻ ወባ ፣ ያርገፈገፋቸው
ቆምጭዬን ከማማው ፣ ሊያወርዱ አማራቸው
መቋጠሪያው ውሉ ፣ መሆኑ ጠፍቷቸው
Zerenga $hrmuta. You can also summon your donkeys.
Re: ቆምጬ
Posted: 06 Mar 2026, 10:55
by Selam/
ቆምጭዬ ቤተኛ ፣ ትግሬ ጎረቤቴ
ጉራጌው አጎቴ ፣ ኦሮሞው አማቴ
ኤርትራ እንግዳዬ ፣ ይቀመጥ ከፎቴ
ተቃጠል ጎጠኛ ፣ ዕለቅ በሸርታቴ
Re: ቆምጬ
Posted: 06 Mar 2026, 12:21
by Dama
Selam/ wrote: ↑06 Mar 2026, 10:55
ቆምጭዬ ቤተኛ ፣ ትግሬ ጎረቤቴ
ጉራጌው አጎቴ ፣ ኦሮሞው አማቴ
ኤርትራ እንግዳዬ ፣ ይቀመጥ ከፎቴ
ተቃጠል ጎጠኛ ፣ ዕለቅ በሸርታቴ
You thugs represent no one. You are hateful. Ypu are racists. Ordinary Amara is not hateful, not racist. You do not speak the language of the people. You do not represent them. Ypu spew hate of your own making.
Std P*mps!!
Re: ቆምጬ
Posted: 06 Mar 2026, 13:22
by Selam/
ቆምጬ ገራገሩ ፣ ሁሌ ልበ ሙሉ
ቢሰድቡት ቢጎዱት ፣ ሸጋ ነው አመሉ
የሚጠሉት ጉጦች ፣ ወረዱ ቀለሉ
ለምህረት ለመኑት ፣ እየተከተሉ
Re: ቆምጬ
Posted: 06 Mar 2026, 13:45
by Selam/
Re: ቆምጬ
Posted: 06 Mar 2026, 14:05
by Selam/
ቆምጬው እረኛዬ ፣ ትንሹ ጌታዬ
ከአውሬዎች አዳነኝ ፣ ነፍሴን ጠባቂዬ

Re: ቆምጬ
Posted: 07 Mar 2026, 04:01
by Meleket
ጉራጌን ታማራ ሊያናክስ አስቦ፡
ትግራይን ታማራ ሊያቧጭቅ አስቦ፡
አገውን ታማራ ሊያቃቅር አስቦ፡
አንዱን ጎሳ ታንዱ ሊያናቁር አስቦ፡
ካድሬው ብልጥግና መጣ አላማ አንግቦ፡
የ‘ኢ-ዜማው' ካድሬ መጣ አላማ አንግቦ፡
ግርማም ወደብ አለ እንዲያው ተስገብግቦ፡
እንዲያ ታላረገ ስለማይኖር ጠግቦ!
በሁለት ቀን ልዩነት፡
አንዱ ‘ጁን’ 22፡
አንዱ ‘ጁን’ 24፡
ተከታትሎ መጥቶ መረጃን በከላት።
ህዝብ እንደማፋቀር፡
ሲሰጥህ ዓላማ ህዝብን ለማናቆር፡
ትግተለተላለህ፡ ኣዬ “የካድሬ” ነገር!
‘ታትዬና ኣብዬ’ ሁለቱ እያዩን፡
‘ክልላነ’ ልንል ይህን የሰው ብኩን፡
ቆምጬን እንዳይነካብን ልንነግረው ቁርጡን!
እንግዲህ ተባብረን ‘ጨቁነናል ስልኩን!’
ለመዝናናትም ጭምር፡ ተጻፈ በእኛ በኤርትርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና !