ሰሞነኛውን ጥቃት ጨምሮ እስካሁን ድረስ፣ በሽርካ ወረዳ በተፈጸሙ ተከታታይ የሆኑ ጥቃቶች ከ164 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን የምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት መረጃ አመልክቷል።
ከተገደሉት በተጨማሪ የደረሱበት ያልታወቁ በርካታ ምእመናን አሉ።
ከሰሞኑን በየካቲት 19፣ 20 እና 22 በደረሰ ጥቃት ብቻ የ31 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
ከትላንት በስቲያ በሽርካ ወረዳ ጢጆ ለቡ ቀበሌ የ70 እና 72 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሁለት ወንድማማች አረጋውያን በታጣቂዎች ግድያ ተፈጽሞባቸዋል።
የሁለቱ ወንድማማቾች ሥርዓተ ቀብርም ትላንትና ሰኞ በጋለማ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።
በአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ስር በሚገኙ ወረዳወች ነዋሪ የሆኑ የቤተ ክህነቷ ታላላቅ አባቶች፣ ካህናት እና ምዕመናን ላይ በደረሰባቸው ጭፍጨፋ ከፍተኛ ሀዘን የተሰማው መሆኑን ይገልፃል።
ከየካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተፈፀመው ጭፍጨፋ ከአርባ በላይ ንፁሃን ነፍሶች በብልፅግና አገዛዝ መር የሽብር ተግባር በጥይት ተደብድበው እና በስለት ተወግተው ህይወታቸው አልፏል። በሺወች የሚቆጠሩትም ንብረታቸው ወድሟል፤ ለዘመናት ከኖሩበት ቀያቸው ተሰደዋል።
አርሲን ጨምሮ የእምነት፣ የቋንቋ እና የማንነት ብዝሃነት ባለባቸው አካባቢወች ላይ ኢ-መደበኛ ኃይሎችን በማደራጀት በዜጎች ላይ ሽብር የሚፈፅመው የብልፅግና አገዛዝ መሰል የዘር ማጥፋት ወንጀልን በግልፅ እና በስውር ሲፈፅም ይህ የመጀመሪያዉ አይደለም። በዚህ ዓመት በምስራቅ አርሲ ዞን የሽርካ ወረዳ ብቻ ከ164 በላይ ኦርቶዶክሳውያን በተመሳሳይ መንገድ ተገድለዋል። በርካታ ምዕመናንም የደረሱበት አይታወቅም።
በመሆኑም ይህ ጉዳይ ለህዝብ ጀሮ እንዲደርስ ያደረጉ የሚዲያ አካላትን እና የተፈፀመውን የሽብር ተግባር ያወገዙ የፖለቲካ ኃይሎችን እያመሰገንን፤ ጨፍጫፊውን የብልፅግና ስርዓት ለማስወገድ እየታገላችሁ ያላችሁ የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይሎችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች መሬት የወረደ ትግል በማድረግ በኦሮሚያ ክልል የሚኖረው አማራ ህዝብ ህልውናው እንዲከበር የበኩላችሁን እንድታደርጉ ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የሀገር ውስጥ እና ዓለም ዓቀፍ ሰብዓዊ መብት ማንነትን እና ሃይማኖትን መሰረት ያደረገውን መንግስት መር ጭፍጨፋ በዝምታ ማየታችሁ ከመተባበር ተለይቶ የማይታይ በመሆኑ የአሁኑን ጨምሮ ከዚህ በፊት የተፈፀሙት የሽብር ተግባራት ተጣርተው በአገዛዙ ላይ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃ እንዲወሰድ ግፊት እንድታደርጉ እንጠይቃለን።
በመጨረሻም ይህንን ብሔር እና ኃይማኖትን መሰረት ያደረገ መንግስታዊ ግድያ አዳዲስ ገዳይ ዩኒቶችን በማቋቋም የሚፈፅመው እና የሚያስፈፅመውን የብልፅግና አገዛዝ በማስወገድ ሀገራችንን ከቀውስ እና ከሽብር አገዛዝ እንድናላቅቅ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ጥሪ እናቀርባለን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
-
MINILIK SALSAWI
- Senior Member
- Posts: 11426
- Joined: 24 Aug 2012, 12:02
- Contact: