የምስጢረ ሥላሴ ታምራት የፖለቲካ ተሳትፎ ተምሳሌትነት ያለው ነው !
Posted: 25 Feb 2026, 11:47
የምስጢረ ሥላሴ ታምራት የፖለቲካ ተሳትፎ ተምሳሌትነት ያለው ነው !
እንደ ምስጢረ ሥላሴ ታምራት ያሉ ፖለቲከኞች አስቸጋሪ በሆነው የኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ መገኘታቸው ብቻ በብዙ መልኩ አስፈላጊና ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም፦
አንደኛ ለወጣቶችና ለሴቶች ያላት ተምሳሌትነት፦ ምስጢረ በሃያዎቹ መጨረሻ ወይም በሠላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኝ፣ ብሩህ አእምሮ ያላት ወጣት ሴት ነች። የእሷ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ከፊት መታየት ለሴቶችና ለወጣቶች ትልቅ ተምሳሌታዊ ትርጉም አለው። ለወደፊቱ ክብሯንና የቆመችለትን ዓላማ ጠብቃ ከተጓዘች፣ ለብዙዎች አርዓያ የመሆን ብቃትና አቅም አላት። ልምድና ተሞክሮ እያዳበረች ስትሄድ፣ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ እና ለሀገር መጥቀም የምትችል ባለተስፋ ወጣት መሆኗ አያጠራጥርም።
ሁለተኛ ድፍረትና ቁርጠኝነቷ ነው፦ ከፍተኛ ዋጋ በሚያስከፍለው የኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ሜዳ ውስጥ እንደ እሷ ወጣትና ሴት ሆኖ መሳተፍ፣ ትልቅ ድፍረትንና ጽናትን ይጠይቃል። በቅርቡ በሚዲያ በተላለፈው የምርጫ ክርክር መድረክ ላይ ያሳየችው ብቃት፣ የንግግርና የማሳመን ችሎታ፣ ድፍረቷ እና ቁርጠኝነቷ ከጋዜጠኝነትና ከሲቪል ማህበረሰብ ሥራ ካገኘችው ተሞክሮ ጋር ተዳምሮ ለሀገር ለማገልገል እና የወደፊት መሪ የመሆን ተስፋ አይባታለሁ።
አንዳንድ ወንድሞቻችን በምርጫው ሂደት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ወደ እሷ ማዞራቸው፣ ከዚያም አልፎ የብልጽግና ጉዳይ ፈጻሚና ተፈቅዶላት እንደምትተውን አድርገው ለማቅረብ መሞከራቸው ተገቢ አይመስለኝም፣ ልጂቱንም ያለማወቅ ነው። በምርጫው ነፃነትና ፍትሐዊነት ላይ እንደ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ቢኖረንም፣ እንደ እሷ ያሉ ብሩህ አእምሮ ያላቸው ወጣቶች በተለይም ሴቶች በዝምታ ከመታዘብ ወይም ከመተቸት ይልቅ፣ በአገራቸው ፖለቲካ በንቃት ተሳትፈው ለውጥ ለማምጣት መወሰናቸው እና የትግል ጥረታቸው ሊበረታታ እንጂ ሊነቀፍ አይገባም።
ሂደቶችን በውጤታቸው መገምገማችን እንደተጠበቀ ሆኖ፣ እንደ ምስጢረ ያሉ ወጣቶችን ግን በድፍረታቸውና በሚያነሱት ሐሳብ ልንመዝናቸው ይገባል። ለሀገር የሚቆረቆሩ እና የሚችሉትን ለማድረግ የሚሞክሩ ወጣቶችን በተለይም ሴቶችን ከመንቀፍ ይልቅ፣ ለሀገራቸው እና ለህዝባቸው የያዙትን አማራጭ ሐሳብ መስማትና ማክበር፣ ሲቻል ደግሞ ማበረታታት እንለማመድ።
በመጨረሻ ልብ ሊባል የሚገባው ወሰኙ ነጥብ ዛሬ በሥልጣን ላይ ባለው የብልጽግና ፓርቲ ውስጥ ካሉት አመራሮችና ሚኒስትሮች መካከል፣ ፓርቲው ቢሸነፍና የጥቅም ምንጭነቱ ቢቆም ስንቶቹ በተቃዋሚነት ጸንተው የፓርቲው አባል ሆነው ይቀጥላሉ ብለን ብንጠይቅ አንድ ሴት እንኳን ላይገኝ ይችል ይሆናል። ጥቅም ሳይፈልጉ ይልቁንም የሚያጋጥማቸውን ሁለንተናዊ ተግዳሮቶች ተቋቁመው በገባቸው ልክ ለወገናቸውና ለሀገራቸው የሚታገሉትን እንደ ምስጢረ ሥላሴ አይነት ጀግና ሴቶችን አለማድነቅ እና አለማመስገን ንፉግነት ይመስለኛል።
እናመሠግናለን ምስጢረ ሥላሴ ታምራት፣ በርቺ! Dessalegn Chanie Dagnew