የክፋት አውራው:-
አብይ አህመድ የትግርኛ ቋንቋን እንዴት ተማረ የሚለውን ሚልኬሳ ሚዳጋ ያጋራንን መረጃ ከማብራራታችን በፊት አብይ አህመድ በመለስ ዜናዊ አስተዳደር ጊዜ እሱ ኦህዴድ ውስጥ የሆነ ቢሮ ሀላፊ እያለ ለስልጣን ካለው ጥልቅ ፍላጎት የተነሳ የ ኢህአዴግ ባለስልጣናትን ደጅ በየቀኑ ይጠና ነበር:: ዝናሽ ታያቸውን ኮሎራዶ ልኮ ልጆቹን በዌልፌር እያሳደገ እሱ አዲስ አበባ ወንደላጤ ሆኖ በየ ባለስልጣኑ በር ሲያውደለድል ነበር::
ለምሳሌ የወቅቱ ኤታማጆር ሹም የነበረው ሳሞራ የኑስ ለልጁ ልደት ሲያከብር አብይ አህመድ በየ አመቱ ድግሱ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ሳህን ያጥብ እንደነበር ሚልኬሳ አጋልጧል:: የወቅቱ የደህንነት ዋና ሀላፊ የነበረው ጌታቸው አሰፋ ቢሮ ገብቶ ለማቃጠር በየሳምንቱ አበባ እየያዘ ጌታቸው ቢሮ ምን ልስራ ምን ላንጥፍ እያለ ይገባ ይወጣ ነበር:: አብይ አህመድ ይህንን ሁሉ የሚያደርገው አንድም የነዚህ ባለስልጣኖች የውስጥ ገበና ለማወቅና ለማጥናት እንደነበር እንዲሁም ራሱን ለሹመት ለማዘጋጀት ነበር::
ሌላው ሚልኬሳ ያካፈለን በጣም የሚገርም ታሪክ አብይ አህመድ ትግርኛ የለመደው ትግራይ በባድመ ጦርነት ጊዜ ከሄደበት ሲመለስ አንዲት የትግራይ እናትን እኔ ጋር ኑሩ ብሎ ያመጣቸዋል:: ከዛም እናቱ ቤት አስቀምጦ ከሳቸው እግር ስር ቁጭ ብሎ ትግርኛ ይማር ነበር:: ወላጅ እናቱን ወይዘሮ ትዝታን ሳይሆን እኝህ ትግርኛ እንዲያስተምሩት ያመጣቸውን ሴትዬ ትግርኛ ተናጋሪ የ ህወሃት ሰዎች በሚጠሩት ግብዣ ቤት ይዞ ይሄድና እናቴን ተዋወቁ እያለ ያስተዋውቃቸዋል:: ይህም ለሁለት ምክንያት ነው አንደኛው ሴትዬዋን እጦራለሁ በሚል ትልቅ ኢንቨስትመንት በማድረግ የትግርኛ ቋንቋን መማር እስይ ላሰበው የስልጣን ኮርቻ መቆናጠጫ ይሆነኛል ሲሆን ሁለተኛው ምክንያት ከትግራይ ሰዎች ጋር በራሳቸው ቋንቋ እነሱን መስዬ የነሱ ወዳጅ መስዬ እንዲያምኑኛ ምስጢር እንዲያካፍሉኝ ያስችለኛል ብሎ ስላመነ ነው:: ወላጅ እናቱን የትም ቦታ ሳይወስድ እኚህን የትግራይ ሴትዬ እናቴ እያለ ማስተዋወቅና በሳቸው አድቫንቴጅ ለመምታት የሚያቅድ አእምሮ ምን አይነት እኩይ አእምሮ ቢሰጥ ነው? የክፋትና የተንኮል ኤክስፐርቱ አብይ አህመድ ታሪኩ ከዚህ ይጀምራል::
ይህን መረጃ ያካፈለን ሚልኬሳና ሳናመሰግን አናልፍም::
Abyi & weyane.
Re: Abyi & weyane.
Ethiopia will soon get rid off these mercenaries and thieves.