"መንግስት ከሜዳው ውጭ እንደሚጫወት ቡድን ሊታይ ይችላል። ጦርነት በሚያደርግበት የአማራ ፣የትግራይና የኤርትራ ቀጠናዎች የህዝብ ደጀን አይኖረውም ፤ በራቀ መጠን የሎጀስቲክ ችግር ያጋጥመዋል"
Posted: 14 Feb 2026, 15:10
ንጉስ በሰራዊቱ ብዛት አይድንም!
By Haileyesus Adamu
ሰሞኑን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደርና ከባድ መሳሪያ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ እየተጓጓዘ ነው። በጎጃም በጎንደርና እና ወሎ መስመር ወደ ሰሜን እየሄደ ያለውን የወታደር ስምሪት በአካባቢው ያሉት የፋኖ ሀይሎች ለማደናቀፍ አልሞከሩም። ይህን ያደረጉት እኛን አይመለከትም በሚል ወይስ አቅም ስላነሳቸው አልያም ሌላ የተነደፈ ስትራቴጂ ስላለ የሚለው ወደፊት የሚታይ ይሆናል። መንግስት አብዛኛውን የሀገሪቱን መከላከያ ወደ ሰሜን እያስገባ ያለውስ ጦርነት ለመጀመር ወይስ ጦርነት ለማስቀረት ( ለ deterrence ) የሚለውንም በቅርቡ የምናውቀው ይሆናል።
ጦርነቱ በአማራ በትግራይ በአፋር እና ኤርትራ የሚደረግ ከሆነ ምን ሊፈጠር ይችላል ?
1. የጦርነት ሜዳው እና ደጀን ህዝብ ፦
የሀገሪቱ ከፍተኛ መሳሪያዎች እና አብዛኛው ወታደር ወደ ሰሜን እየገቡ መሆናቸውን ተከትሎ አንድ ነገር በርግጠኝነት መናገር ይቻላል ። ይህን ጦርነት ማንኛውም ወገን ያሸንፍ ጦርነቱ ግን የሚያልቀው ሰሜን ላይ ነው። ገዥው መንግስት ከሜዳው ውጭ እንደሚጫወት ቡድን ሊታይ ይችላል ። ጦርነት በሚያደርግበት የአማራ ፣ የትግራይ እና የኤርትራ ቀጠናዎች የህዝብ ደጀን አይኖረውም ፤ ከማእከሉ በራቀ እና ጦርነቱ በተራዘመ መጠን ከፍተኛ የሎጀስቲክ ችግር ያጋጥመዋል ፤ በቀላሉም በየቦታው የመቆረጥ እድሉ ከፍተኛ ነው። በአንፃሩ በዛኛው ወገን ያሉት በራሳቸው ሜዳ ነው የሚጫወቱት ። ይህ እንወክለዋለን ለሚሉት ማህበረሰብ ከፍተኛ የሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት የሚያመጣ ቢሆንም የማሸነፍ እድላቸውን ግን ይጨምረዋል። ህዝባቸው እና የሚያውቁት መልከዓ ምድር ትልቅ አቅም ይሆናቸዋል።
2. ወታደራዊ ቁመና
2.1 እግረኛ ወታደር ፦ በእግረኛ ወታደር በኩል በቁጥር ደረጃ የብልጽግና መንግስት ብልጫ ይኖረዋል። በአንፃሩ በዛኛው ወገን ያሉት በአጭር ግዜ ስልጠና በብዛት ከተመለመለው የመንግስት ወታደር የተሻለ የጦርነት ልምድ ያላቸው ( battle-hardened) ሀይሎች አሏቸው።
2.2 የጦር መሳሪያ ፦ የብልጽግና መንግስት የተሻለ ከባድና የቡድን መሳሪያዎች አሉት።
2.3 የአየር ሀይል ፦ የብልጽግና መንግስት ድሮንን ጨምሮ ከፍተኛ የአየር ሀይል ብልጫ ይኖረዋል።
2.4 የወታደሩ የመዋጋት ፍላጎት ፦ የአማራ ፋኖ ፣ የትግራይ ቲዲፍና የኤርትራ ሀይሎች ጦርነቱ የህልውናችን ነው ብለው ስለሚያስቡ እስከ መጨረሻው ለመፋለም የተዘጋጀ ሀይል ይኖራቸዋል። በአንፃሩ በብልፅግና በኩል ያለው ሰራዊት ለደሞዝ ስራ ሲያጣ የገባ በመሆኑ የውጊያ ሞራሉ ዝቅተኛ ነው።
በወታደራዊ ቁመና ረገድ ብልፅግና የወታደር ቁጥርና መሳሪያ ብልጫ ቢኖረውም ወታደሩ የጦር ልምድ የሌለውና የመዋጋት ፍላጎቱ ዝቅተኛ ስለሆነ እግረኛ ወታደሩና መሳሪያዎቹ በቀላሉ የመማረክ እድል ይኖራቸዋል ።
3. የሀይል አሰላለፍ ፦
ከብልፅግና ጎን በዋናነት UAE እና የሱዳኑ RSF ይሰለፋሉ።
የአማራ ፋኖ ፣ የትግራይ ቲዲፍ እና የኤርትራ ጦር ጎን የሱዳኑ የአልቡህራን SAF እንዲሁም ግብፅ እገዛ ይሰጣሉ። የጉምዝ እና ጋምቤላ ሀይሎች እንዲሁም የኦጋዴን እና የ ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እንደሁኔታው ከዚህኛው ወገን በቀጥታም በተዘዋዋሪም ሊሰለፉ ይችላሉ ።
እንደ ሳውዲ አረቢያ እና እስራኤል ያሉ ሀገራት የጎላ ጣልቃ ገብነት ሳያሳዩ ይቆያሉ።
ራሽያ ፣ ቻይና ፣ አሜሪካና የአውሮፓ ሀገራት ለግዜው ገለልተኛ የሆነ አቋም ይኖራቸዋል።
በአጠቃላይ ከታዬ በሁሉም ጎራ ያሉት የየራሳቸው ጠንካራና ደጋማ ጎን ያላቸው ሲሆን የውጭ ሀይሎች ጣልቃገብነት ጋር ሲደመር ጦርነቱ ከተጀመረ ሱዳን ላይ እንደምናዬው የተራዘመ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው። በርግጥ የሶርያው አላሳድ ጦር ያጋጠመው አይነት ያልተጠበቀ የሰራዊት መፍረስ ብልፅግና ሊያጋጥመው ይችላል ። በአንፃሩ ግን በየትኛውም አይነት የቢሆን መላምት ውስጥ የሰሜን ሀይሎች ሙሉ በሙሉ የሚሸነፉበት ሁኔታ አይኖርም ። ከላይ ያየናቸውን ነጥቦች ከግምት ውስጥ ካስገባን በአንፃራዊነት የሰሜን ሀይሎች የማሸነፍ እድላቸው የተሻለ ነው።
የመውጫ መንገዱ ምን ይሁን
ብልፅግና እንደሚያስበው ይህ ጦርነት በአጭሩ አይቋጭም። በዛኛው ወገን ያሉትም እንደሚያስቡት በቀላሉ አራት ኪሎ አይደርሱም ። ከፍተኛ ጉዳት የሚያመጣ የተራዘመ ደም አፋሳሽ ጦርነት የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው። በመሆኑም ብልፅግና ከሚሊተሪ አድቬንቸር ወጥቶ ከሀገር ውስጥ ሀይሎች ጋር የፖለቲካ መፍትሔ መፈለግ አለበት ።

Please wait, video is loading...