Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

sarcasm
Senior Member
Posts: 11562
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: Ethiopia’s Involvement in Sudan Civil War Exposed -Analists puzzled at the logic of allowing RSF training camp near

Post by sarcasm » 10 Feb 2026, 18:41

"አብይ የኢሜሬትስን ትዕዛዝ እንጂ የሀገርን ይቅርና የእራሱን እንኳን ጥቅም ከግምት ያስገባ ውሳኔ እየወሰነ አይደለም ስንል ያለምክንያት አይደለም። እንደማሳያ ለሱዳኑ ሀገር አፍራሽ የ RSF አማጺ ቤኒሻንጉል ውስጥ የማሰልጠኛ እና ማሰማሪያ ካምፕ ሲከፍት ፤ የሀገራችንን ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ንብረት የሆነውን የህዳሴ ግድብ ደህንነት የሚያውክ የጦር ቀጠና ከፍቷል።
ባለፉት ቀናት ብቻ ከአዲሱ ማሰልጠኛ የተሰማሩ የ RSF ወታደሮች ከግድቡ በአስርታት በሚቆጠር ኪሎሜትር ርቀት ላይ ኩምሩክ አከባቢ በሱዳን ሰራዊት ላይ አዲስ የጦርነት ግንባር ከፍተዋል። በአጸፋው የሱዳን እና የግብጽ አየር ሃይል አካባቢውን እየደበደቡ ይገኛሉ።

አንድ ነገር ልብ በሉ። በህዳሴው ጉዳይ ለረጅም ጊዜ ግብፅ ስታራምደው የነበረችው ትርክት ኢትዮጲያ የግድቡን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ አትችልም የሚል ነበር። ይህንኑ ትርክት ወደ እውነታ ለመቀየር ብዙ ሙከራዎችን ስታካሄድ ነበር። ግን አልተሳካላትም።

አሁን ግን ግብጽ ያልቻለችውን አብይ አሳካላት። የህዳሴን ግድብ አካባቢ አዲስ እና የጦፈ የጦርነት አውድማ በማድረግ ፣ ግብጽ ስትለው እንደነበረው ኢትዮጲያ የግድቡን ደህነነት ማረጋግጥ አትችልም የሚለውን ትርክት ወደ እውነታነት እያቀረበው ነው።"


ጀዋር መሃመድ

Please wait, video is loading...



sarcasm
Senior Member
Posts: 11562
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: Ethiopia’s Involvement in Sudan Civil War Exposed -Analists puzzled at the logic of allowing RSF training camp near

Post by sarcasm » 12 Feb 2026, 17:21

Abiy has made foolish decisions before but now you could be thinking he is actively speeding up the demise of Ethiopia.

He's involving himself in Sudan, seeking conflict with Eritrea, blowing up the peace deal with the TPLF, and surrendering ground to Fano, all at the same time.


https://x.com/ThomasVLinge/status/2021193177244258787

Post Reply