ጉልበት የቀማውን ጉልበት ይቀማዋል!
ሕግ ይወጣል ሕግ ይሻራል!
እዳ ዛሬ ካልተከፈለ ወደ ፊት መከፈሉ የግድ ነው!
የኢትዮጵያን ወደብ መልሰህ በሰላም ኑር!
ኋላ ከሁለቱም እንዳታጣ!
Meleket wrote: ↑11 May 2022, 09:25ቤነገራችን ላይ ግጥሙ፡ ለ'ጋዜጠኛው ቴድሮስ ጸጋዬ" ወልጋዳ ምልከታ የተገጠመ ነበር፡ እስቲ ኣጣጥሙ፡ በኤርትራዊ ኣማርኛ የተጣፈ ነው!
Meleket wrote: ↑11 May 2022, 04:23'በአንከላኛ'ና በከበደ ሚካኤልኛ የገጠምነውን እናጋራ፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች። "ኣንከላኛ' ደግሞ ምንኛ ነው እንዳትሉ!![]()
Meleket wrote: ↑12 Aug 2018, 08:53ርእዮት - ግርድፍ ግጥም
አንድ እናት ነበረች ልጆች የነበሯት፣
እጅግ ውብ የሆነች እንከን የማይወጣት።
ያለም ነገር ሆኖ እርጅና መጥቶ፣
ልጆች ስታሳድግ እንግልቷ በዝቶ፣
ብዙ ስቃይ አየች የማያልቅ ተወርቶ።
ግን አልሰነፈችም በማድረጓ ጥረት፣
አንድ ልጇን ዳረች መርቃ በክብረት።
ያለም ነገር ሆኖ የጤናዋ ጉዳይ፣
ለልጆቿ ስትል እሷ ስትሰቃይ፣
ከእለት ወደ እለት መሻሻል ሳያሳይ፣
ከእርጅናው ጋራ አባሰባት ስቃይ።
እንዲህ እንዲህም ሲል ያይኗን ብርሃን አጣች፣
ልጆቿ ሲያብቡ እሷ ግን ገረጣች።
ይህንን ታዝባ ባለ ትዳር ልጇ፣
እናቷን መርዳቷን አረገች ግዳጇ።
እናቷን ስትመራ በመንገዷ ሁሉ፣
ለመመረቅ ነበር እንዲያው በጥቅሉ።
እናትየዋ ግን የእናት ነገር ሆኖ፣
ልጆቿን ስትመግብ አንድ ልጇ ጨክኖ፣
አንድ ሃሳብ አመጣ አወላግዶ አጢኖ፣
ካወቅኩ ባይ ልጇ በቀረበ ‘መላ’፣
በሰላሙ ሰፈር ተንኮል እንዲያጠላ፣
እንዲህ እንዲህ አላት በነገር ፍተላ።
“ልጄ በመሆንሽ ራሴ የወለድኩሽ፣
የምልሽን ስሚ እንዲያው አትቅለስለሽ።
ይህ ያይኖችሽ ብርሃን ከኔ የወረስሽው፣
ባለቤቱ እኔ ነኝ ቁርጥሽን እወቂው።
ይህን ሃቅ አጢነሽ ተንግዲህ በኋላ፣
ማንኛውም ስራሽ እኔን ማያጉላላ፣
እንዲሆን አድርጊ እኛ እንዳንጣላ!
እንዲያውም ይህ ዓይንሽ ሁሉን ምታይበት፣
ባለቤቱ እኔ ነኝ እንዳሻኝ ምሆንበት፣”
ብላ እንድታስብ ያቺ ምስኪን እናት፣
አወቅኩ ባይ ልጇ በአንክሮ መከራት።
ባለትዳር ልጇ የመላች በትዕግስት፣
መረጠች ለናቷ እውነቱን ልትነግራት።
“እማማ እናታለም ወላጄ ውቢቱ፣
ይህን ሃቅ ስሚኝ እንዲያው ባዛኝቱ።
ድሮ ዓይኖች ነበሩሽ ምን ምን የመሰሉ፣
“በፌደሬሽን” ወቅት ላንቺ የተተከሉ፣
ያያቸውን ሁሉ እንዲያው ሚያማልሉ፣
እኛን በማሳደግ ውለታን የዋሉ።
የአምላክ ስራ ሆኖ ስለጠፉ አሁን፣
እንዴት ታልሚያለሽ ጌታን ለመኮነን?
ባለም አደባባይ ክሶችን መስርተሽ፣
እንዴት ልትዘልቂው ነው ፈጣሪን ሞግተሽ?
ያይንሽንስ ብርሃን እንዴት ልትመልሽ?
የተጠቃሚነት መብቱ ይገባኛል፣
የራስ ባልሆነ ዓይን እንዴትስ ይቻላል?
ይልቅ ጠባይ አርገሽ ከኔ ከልጅሽ ጋር፣
በብርሃኔ ልምራሽ እንኑር በፍቅር።
አንቺም ዋዛ አይደለሽ ብዙ ሃብቶች አሉሽ፣
ይህ የዓይኔ ብርሃን አይቀርም ሳይጠቅምሽ።
እንዲህ እንዲህ አርገን እየተጠቃቀምን፣
በፍቅር መኖር ነው ለኛ የሚበጀን።
ያለሽ አንድ አማራጭ ዓይንሽ እንዲበራ፣
እሱ ራሱ መጥቶ ተዓምር ካልሰራ፣
ሌላ መላ የለም ሚሆን በፉከራ፣
ጭቃውን አብኩቶ አይንሽን ነካክቶ፣
እሱ ካልዳበሰሽ ተሰማይ መጥቶ፣
የትም አያደርስሽ ሽለላ ቀረርቶ።
ተከባብሮ መኖር እያለ አንድ መላ፣
ተጋግዞ መኖርም እያለ አንድ መላ፣
እስቲ ዕድል አንስጠው ተንኮል ለሚያሰላ፣
አዋቂ ነኝ ለሚል ለማንም ቱልቱላ፣
ሌተቀን ለሚያልም እኛኑ ሊያባላ።
እኔና አንቺ ሁሌም ከልብ ስንፋቀር፣
እምንሰራው ሁሉ እንደሚሆን ተአምር፣
መሰሪ ዲያብሎስን እንደሚያደርግ ኩምትር፣
በምን አማርኛ ለመግለጽ ልሞክር!!!!!!!
ፍንጭ፦ ይህ ጽሑፍ ዓላማው፣ የሰው ገንዘብ ሚመኝን ክፉ መካሪ መሰሪን ለመገሰጽ ነው።
ያሌኛ ያኛ ያሌም!
Prisoners of war in Assab, Eritrea [Photo by Habtom Berhe, from the Greg Marinovich collection]
Meleket wrote: ↑06 May 2023, 04:20Meleket wrote: ↑03 Aug 2018, 05:09ከታሪክም እያጣቀስን እስቲ እንማማር!
በአጤ ኃይለሥላሴ ግዜ ኤርትራ ውስጥ የተፈጸመች አንዲት የምትነገር ጨዋታ አለች። ያኔ ያኔ ‘መደመር’ የሚባለው ፍስፍና ሳይመጣ፣ ፌደሬሽን ፈርሶ ኢትዮጵያና ኤርትራ እንኳን ተዋህደው በነበረበት ወቅት የተፈጸመች ክስተት ነች። ንጉሥ ኃይለሥላሴ ለማርያም ልዩ ፍቅር ስለነበራቸው ሁልግዜ በጥር ወር አስተርእዮ ማርያምን በምጽዋ ነበር የሚያሳልፉት ነበር አሉ። እናማ ከወቅቱ ቱባ ቱባ ባለሥልጣኖች ማለትም ከመሳፍንቶቻቸውና መኳንንቶቻቸው ጋር ሆነው በባህሩ ዳርቻ ሲንጎራደዱ፣ ነገር የጠማው በአሽሙርና ሸር የታወቀ አንድ ቀልደኛ-ቢጤ የመሀል አገር ሰው፣ በወቅቱ ከኤርትራ መኳንንት አንዱ የሆነውን፣ የቢትወደድ አስፍሃ ወልደሚካኤል ወንድምን በነገር ሊጎነትል ፈልጎ፣ ምጽዋ ባህሩ አጠገብ እየተንጎራደደ “ባህሩ የኛ ነው!” አላቸው። እኒያ ጨዋ ኤርትራዊም ሰምተው ያልሰሙ መሰሉ። ያ “ሸረኛ” ግን አሁንም በስማችው ጠርቶ እጁን ወደ ባህሩ ቀስሮ “ባህሩ የኛ ነው!” በማለት ደገመላቸው። ሰውየው አሁንም ሰምተው ያልሰሙ መስለው ችላ አሉት። ለሶስተኛ ግዜ እጁን ወደ ባህሩ እያመለከተ “ባህሩ የኛ ነው” ቢላቸው፣ ትግርኛን ብቻ ሳይሆን አማርኛንም ቅኔ የሚቀኙበት ብልሁ የቢትወደድ ወንድም ምን ቢሉት ሃሪፍ ነው። - - - “ወዳጄ፣ ያለኛ የኛ የለም!” ብለውት እርፍ። አዎን “ያለኛ የኛ የለም!”። ይህን ሁሉ በውል ይከታተሉ የነበሩት የቀልደኛውንም አጎነታተል በደንቡ ያጤኑት ንጉሡም ‘የመሀል አገሩን ሰውየ’፣ “ይህ ብልህ ልጄ እውነተኛ መልስ መለሰልህ አይደል!” አሉት ይባላል። - - - ምን ለማለት ነው። በፍቅር ሁሉ ይቻላል፣ በመከባበር ሁሉ ይቻላል፣ በወንድማማችነት ሁሉ ይቻላል፣ በመረዳዳት መንፈስ ሁሉ ይቻላል፣ ነገርግን በአሽሙር በጥላቻ በመናናቅና በቅናት መንፈስ ምንም ማድረግ አይቻልም።
ስለዚህ ኢትዮጵያውያን ሆይ የኤርትራን መሬት ስትረግጡ ጠንቀቅ በሉ፣ በስንትና ስንት ሰማዕታት ህይወት የተመሰረተች ቅድስት ሀገር ስለሆነች፣ አፋችሁ መልካም ነገር እንጂ ጉራ፣ ቀረርቶ፣ አሽሙር፣ ትዕቢት ወዘተ ወዘተ ባታስተናግዱበት ይበጃችኋል። እግራችሁ የኤርትራን መሬት ሲረግጥ፣ ይህችን ለሐቅ ሲሉ ስንትና ስንት ቅኑ ዜጎቿ የተሰውላት፣ እንደሻማ የቀለጡላት፣ የሰነከሉላት፣ የታሰሩላት፣ የተገረፉላት፣ የታረዙላት፣ የተሰደዱላትን ኤርትራንና ኤርትራውያንን አሰብ ማድረግ ይጠበቅባችኋል። ይህን ካደረጋችሁ የኤርትራንና ኤርትራውያንን ፍቅር ያለ ገደብ ታገኛላችሁ። እኛ ኤርትራውያን ጠቅላይ አብይን የምናከብራቸው፣ በዚች እጅግ አጭር የስልጣን ግዚያቸው፣ በርካታ እስረኞችን ሞትም የተፈረደባቸውን እንደ አቶ አንዳርጋቸው አይነቶችን ሰዎች ጭምር ስለፈቱ፣ ተፎካካሪ እንጂ ተቃዋሚ የሚባል ነገር የለም የሚል አመለካከትን ስላስተዋወቁ፣ በውጪ ሃገር የሚኖሩ ፖለቲከኞችንና የመገናኛ ብዙሓንን ወደ ሃገረ ውስጥ ገብተው ገንቢ ሚና እንዲያበረከቱ ጥሪ ስላደረጉ፣ በአካልም ሄደው የልብ ትርታቸውን ስላደመጡ፣ በቀጠናችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ይቅርታን በተግባር ስላስተማሩ፣ እንደመር እንፋቀር ስላሉ፣ የህዝባቸውን የልብ ትርታ ለማድመጥ ስለሚጥሩ፣ የተጣሉና የተኳረፉ የሃይማኖት አባቶችን ሳይቀር ስላግባቡና ስላስታረቁ፣ አንደበታቸው በሳልና ርቱዕ ስለሆነ፣ ትሑት ስለሆኑ፣ እውነትን ስለሚወዱ፣ የሰው ገንዘብ ስለማይመኙ ወዘተ ብቻ አይደለም፣ ሰማእታቶቻችንንም ስላከበሩ ነው። ኤርትራ፣ ሃገረ - ሰማእታት ናትና!
https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=17&t=162456&p
ፈጣሪ ኤርትራንና ኤርትራውያንን ይባርክ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ይባርክ!
"ያለኛ የኛ የለም!"![]()
![]()
![]()