Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11161
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

ህዝብ ማወቅ ያለበት ራያ አካባቢ ያለው ነባራዊ ሁኔታና እውነታ!

Post by MINILIK SALSAWI » Today, 09:13

አላማጣ ከተማ ራያ አላማጣ እና ኮረም ዙሪያ የነበረው የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና መከላከያ ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ ያለ ምንም የጥይት ተኩስ ጥር 21/2018 ዓ.ም አካባቢውን ለቆ ወጥቷል::
ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ሚያዚያ 2016 ዓ.ም ራያ ላይ የነበረውን መዋቅር በሴራ አፍርሶ አካባቢውን አሳልፎ በመስጠት በኋላም የተወሰነ ሃይሉን የተለያዩ ቦታዎች ላይ በማስፈር አካባቢውን ከትግራይ ሃይሎች ጋር ይዞ መቆየቱ የሚታወቅ ነው::
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና በተጠቀሱት የራያ አካባቢዎች ከሚያዚያ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከትግራይ ሃይሎች ጋር በጋራ ሰፍሮ ይኖር የነበረውን ሰራዊቱን ጥር 21/2018 ዓ.ም ያለ ምንም የጥይት ተኩስ ለቆ እንዲወጣ አድርጎ ቦታውን ሙሉ ለሙሉ ለትግራይ ሃይሎች አስረክቧል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም አገዛዙ በዚህ መንገድ ለቆና አስረክቦ የወጣውን የራያ አካባቢዎች የሃሰት ፕሮፓጋንዳና ሴራ ሊሰራበት እንደተዘጋጀ መረጃው አለን:: ይህንን ካሁን በፊት እንዳደረገውና አሁንም እንደሚያደርግ ግን ለህዝብ የተደበቀ አይደለም::
ብልፅግና ይዞት የነበረውን የራያ መሬት በዚህ መንገድ ያስረከበ መሆኑ እየታወቀ ነገር ግን በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ህዝብ ላይ የተለመደ ፀረ ፋኖ የውሸት ፕሮፓጋንዳውን በመስራትና አዲስ የውጊያ አጀንዳ በመፍጠር ብሎም በፀረ-ህዝብና አገር አፍራሽ ሚዲያዎቹ በማስተጋባት ለአማራው ከእልቂት በስተቀር አንዳች መፍትሄ ወደሌለው ጦርነት በማስገባት እድሜውን ለማራዘም እየሰራ ይገኛል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም ከደቡብ ወሎ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በሚሊሻ ስም የሰበሰበውን የአማራ ገበሬ እና አድማ ብተና ቀድሞ ወልድያ እና ራያ ቆቦ ዙሪያ ያሰፈረ ሲሆን ከሰሜን ወሎ ሚሊሻ ጋር በማድረግ በቀጣይ ከትግራይ ሃይሎች ጋር ሊያደርገው ባሰበው ጦርነት ከፊት ሊማግዳቸው ዝግጅቱን ጨርሷል::
*ማስታወሻ፦ አገዛዙ ባሁኑ ሰዓት ሰሜን ወሎ ዞን ባሉ ወረዳዎች የግል ታጣቂዎችን ሳይቀር ለጥር 22/2018 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ እየጠራ ይገኛል::
እየሆነ ያለው እውነታ ይሄው ነው::
ጥር 21/2018 ዓ.ም