Page 1 of 1

THE NEW ETHIOPIA - WHERE VISION MEETS DISCIPLINE!

Posted: 26 Jan 2026, 02:03
by Horus

Re: THE NEW ETHIOPIA - WHERE VISION MEETS DISCIPLINE!

Posted: 26 Jan 2026, 05:52
by sesame


TOSA MEDIA ጦሳ ሚዲያ

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል፣ በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ የኢኮኖሚ እና የሰብዓዊ ሁኔታ የሚያሳዩ መረጃዎችን በኤክስ ገጻቸው ላይ አጋርተዋል።

ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ከለጋሽ ሀገራት እና ድርጅቶች በድምሩ 84 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ ብታገኝም፣ ሀገሪቱ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ ጠቁመዋል። አቶ የማነ ለዚህ ማሳያ ይሆናሉ ያሏቸውንና ለ2025 (እ.ኤ.አ) የወጡ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እና የሰብዓዊ ቀውስ የሚያሳዩ ዝርዝር መረጃዎችን አያይዘው አቅርበዋል።

ሚኒስትሩ ያጋሩት የኢኮኖሚ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፡-
▪️በፌዴራል ደረጃ ከተመዘገቡ የንግድ ተቋማት ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት በ2025 (እ.ኤ.አ) ከስራ ውጪሆነዋል።
▪️ 470,000 የሚሆኑ የንግድ ተቋማት ከምዝገባ መዝገብ ላይ ጠፍተዋል።
▪️ በግምት 4.7 ሚሊዮን የሚሆኑ የስራ እድሎች ተቀጥፈዋል።
▪️ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (NBE) 2.6 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ኪሳራ አስመዝግቧል።
▪️ ብሔራዊ ባንኩ በውጭ ምንዛሬ ለውጥ ምክንያት 407.1 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ሲያጋጥመው፣ አጠቃላይ የስራ ማስኬጃ ኪሳራው ደግሞ 428.56 ቢሊዮን ብር ደርሷል።
▪️ ባንኩ ከወርቅ ሽያጭ እና ከንብረት ዋጋ ቅነሳ (Inventory write-downs) ጋር በተያያዘ 57.2 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ሪፖርት አድርጓል።

በሰብዓዊ ሁኔታ ላይ የቀረቡት መረጃዎች፡-
▪️ በግምት 21.4 ሚሊዮን ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።
▪️ 4.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች በሀገር ውስጥ ተፈናቃይ (IDPs) ናቸው።
▪️ 12 ሚሊዮን ህጻናት የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፣ 8.32 ሚሊዮን ህጻናት ደግሞ ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው።
▪️ ወደ 9,178 የሚጠጉ ትምህርት ቤቶች መውደማቸው ወይም ጉዳት እንደደረሰባቸው ተጠቅሷል።
▪️ 68.7 በመቶ የሚሆነው ህዝብ በብዝሃ-ዘርፍ ድህነት ውስጥ እንደሚገኝ ሪፖርቱ አመልክቷል።

አቶ የማነ ገብረ መስቀል በመልዕክታቸው ማጠቃለያ ላይ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ቀጣናዊ ግጭቶችን ከመቀስቀስ ይልቅ፣ እነዚህን ውስጣዊ "አሳዛኝ እውነታዎች" ለመፍታት ትኩረት መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል።