Page 1 of 1

ፋኖ ሊወስዳቸው የሚገባ ጥንቃቄዎች -- የእራሱ መገናኛ ብዙሃን በመመስረት በመጠቀም ከሻዕብያ እና ወያኔ ጋር ምንም ዓይነት አጋርነት እንደሌለው መግለጽ አለበት።

Posted: 24 Jan 2026, 11:38
by Abere
ፋኖ ሊወስዳቸው የሚገባ ጥንቃቄዎች -- የእራሱ መገናኛ ብዙሃን በመመስረት በመጠቀም ከሻዕብያ እና ወያኔ ጋር ምንም ዓይነት አጋርነት እንደሌለው መግለጽ አለበት። ሦስቱም የአማራ ጥላቶች (TPLF, Shabia, OLF-PP) ይህን ፕሮፓጋንዳ እየተጠቀሙበት ነው። በተለያዩ የፋኖ አባል ግለሰቦች የተጣረዘ መረጃ በሳንቲም ለቃሚ ዩቲዩበሮች በተለይም የዲያስፓራ ሌባዎች ስለሚናፈስ የፋኖን ትግል ሊጎዳ ይችላል። አንዱ የአማራ ጥላት ደግፎ ሌላውን የአማራ ጥላት መዋጋት የቱን ያህል እንደሚጎዳ በተደጋጋሚ ታይቷል። የፋኖ ግልጽ አቋም ከጓዳ ወደ አደባባይ በእራሱ መገናኛ ርዕሰ አንቀጽ በግልጽ እና በተደጋጋሚ መቅረብ አለበት። የተሸፋፈነ ነገር በቅርቡ ከወያኔ ጋር በነበረው ጦርነት ታይቷል - በፕሪቶሪያ ጸሀይ ሙቆታል።