ህዳሴ ግድብ፡ የአለም ኃይሎች አሰላለፍ ስርዓት ሳሆን ቀውስ ነው! ኢትዮጵያ ምን ታድርግ?
Posted: 21 Jan 2026, 15:36
የወቅቱን የግብጽና አሜሪካ ድራማ በተመለከተ መታወቅ ያለበት ነገር አለ ። እሱም ትራምፕ ምንድን ነው የሚፈልገው? ኤል ሲሲ ምንድን ነው የሚፈልገው የሚሉት ናቸው ።
ትራም አሜሪካንን እንደ ገና ብቸኛው ያለም ሱፐር ፓወር ማድረግ የሚፈልግ ቅዠታም ነው። ለምን ቢባል አይችልም።
በተለይ ኢትዮጵያ ከቻይና ፣ ከሩሲያ ፣ ከህንድ ጋራ ያላት እስትራተጂያዊ አጋርነት በጣም የሚያበሳጨው ነገር ነው።
በዚህ ዘመን አሜሪካ አንዷ የኢትዮጵያ አጋር ኃያል አገር እንጂ በቸኛው ኢትዮጵያን የምትቆጣጠር ኃይል አይደለችም ለምሳሌ በኢኮኖሚው ዘርፍ ቻይና ፣ ሕንድ ፣ ቱርክ ፣ ኢሚራቲ ናቸው የኢትዮጵያ አጋሮች ። በሚሊታሪ ሩሲያ ቻይና እስራኤል እንጂ አሜሪካ አይደለችም።
አሁን ላይ የአሜሪካው ቦዪንግ፣ ጄኔራል ኤሌክትሪክ የጄት ሞተር ፣ የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ግምባታ ላይ ዋነኛ ጥቅም አላቸው ። በተረፈ ያለም ባንክ ብድርና ጥቂት ቢሊዮን እርዳታ ናቸው።
አለቀ፣ ዛሬ ብቻ በኢትዮጵያ 600 የህንድ ኩባኒያዎች አሉ ።
የትራምፕ ንዴት በተለይ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ፣ የአለም አየር ንብረት ንቅናቄ ውስጥ መግነኗ ፣ በአፍሪካ ሕብረት ውስጥ እጅግ ተደማጭ መሆኗና በተለይ በተለይ ከ4ኛው ያለም ኃያል ሕንድ ጋር ከፍተኛ ወዳጅነት መፈጸሟ ነው ። ህንድ አለ ምንም ጥርጥር ቅርብ ምስራቅና አፍሪካን የምትወጥ ኃያል እየሆነች ነው። በቅርብ ምስራቅ ከ10 ሚሊዮን የማያንሱ ሕንዶች አሉ ። የሕንድና አፍሪካ ሕዝብ ሲደመር 3 ቢሊዮን ሲሆን ይህም ያለም ሕዝብ 36% ማለት ነው። ሕንዶች ዘ ግሎባል ሳውዝ ሲሉ ዘ ግሎባል ሳውዝ ኢስት ማለታቸው ነው ።
ሌላው የትራምፕ ፍላጎት የኖቤል ሽልማት ማግኘት ነው ።
የኤል ሲሲ ፍላጎት ውስጣዊ ቅቡልነት ነው ። ለ14 አመት ባዶ ድንፋታ ሲነፋ ኢትዮጵያ ግድቧን ክሽን አድርጋ ስላጠናቀቀች የግብጽ ሕዝብ እጅግ ግዙፍ የስነ ልቡና ስብራት ደርሶበታል! የምር ኢትዮጵያን ይፈራሉ! እንደ ምንንቃቸው በውል ያውቃሉ ። በዚህ ሳቢያ አል ሲሲ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ አላቸው! ይንቁታል!
እናም አል ሲሲ አንዳች ኢትዮጵያን የሚያስገድድ ነገር በማሳየት ገጽታውን ማሻሻል ዋና አላማው ነው ። ስለ ሆነም ባብዛኛው አላማው የፖለቲካና የሕዝብ ግንኙነት እንጂ የግድቡ ቴክኒካዊና ኢኮኖሚያው አደጋ አይደለም ።
የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ይህን የሚያውቁ ይመስለኛል።
ኢትዮጵያ የዛሬ 140 አመት የውጫሌን ውል የፈረመችና የሰረዘች አገር ነች ። ስለዚህ ኢትዮጵያ ዘና ፈታ ብላ እየተናወጠ ያለውን አለም በጽሞና በማስተዋል፣ እዚም እዛም የሚፈነዱትሁኔታዎችና ጥምረቶችን በመለካት ስክን ያለ አቋም ነው መውሰድ ያለባት! ኢትዮጵያ በምንም ጥድፊያ ውስጥ አይደለችም! ግድቧን ሰርታለች! ሰው አውቋት ጸሃይ ሞቆዋታል።
የአለም ኃይል አሰላለፍ እርግጠኛ ሳይሆን ያልተረጋገጠ ፣ ያልጸደቀ ክስተት ነው
ያለም ኃይል አሰላለፍ የጸና የተረጋጋ ሳይሆን ተለዋዋጭ ተንሸራታች ፣ ሙልጭልጭ ነው
ያለም ኃይል አሰላለፍ ቀላልና ቀጥታ ሳይሆን ውስብስብ ጥልፍልፍ ስዋስው ነው
ያለም ኃይል አሰላለፍ ግልጽና ጥርት ብሎ የሚታይ ሳይሆን አሻሚ ደብዛዛና ውዥብር ነው
ስለዚህ ዋናው ወሳኙ የኢትዮጵያ መሪዎች ሥራ ኢትዮጵያን እንደ አገር በሚሊተሪ፣ በኢኮኖሚ፣ በቴክኖሎጂና በማህበራዊ መስኮች መገምባትና እንደ ብረት በማጠንከር በዚህ የአለም ቀውስ ውስጥ ያገራችንን ብሄራዊ ጥቅም ላይ ብቻ በማነጣጠር በቀውሱ ባህር ውስጥ መዋኘት ነው! ወጀቡን መቅዘፍ ነው ! በውስብስቡ ውስጥ መሹለክ ነው! በቀውሱ አለመጠለፍ ነው!
ኢትዮጵያ ያፍሪካ ቀንድ ኃያል አገር ነች! ይህን ታሪካዊ ሚናዋን በትክክል መወጣት አለባት!
ስለዚህ የትራምፕ ድራማ ምንም የሚያስፈራ ነገር አይደለም!