Page 1 of 1

ቡሾፍቱ ከተማ በዲሞክራስያዊ ምርጫ የተመረጠ የከተማ አስተዳደር ቢኖራት ስሟ ቡሾፍቱ ሆኖ ይሰነብት ነበር?

Posted: 19 Jan 2026, 00:55
by Naga Tuma
ቡሾፍቱ ማለት ጎምዛዛ ማለት ነዉ።

ካልዘነጋሁ ስሟን ያገኘችዉ በዙርያዋ ካሉ ኣንዱ ሀይቅ ነዉ ይባል ነበር። ዉሃዉን ሰዉ ቀምሶት ስለ ጎመዘዘ ጎምዛዛ ተባለች ኣሉ። እቴጌ ጣይቱ ይህን ስም እንዳላወጡ መገመት ይቻላል።

ስለዚህ ችግሩ ስሙ ሳይሆን ትርጉሙ ነዉ።

ትልቅ ኣይሮፕላን ማረፍያ ልታገኝ ነዉ ማለት ብዙ ስዎችን ከአለም ዙርያ የምታስተናግድ ትሆናለች ማለት ነዉ።

መንገደኞቹ ኣዲስ ቦታ ሲደርሱ የቦታዉ ስም ትርጉም ምን እንደሆነ ለማወቅ የሚጓጉ በብዛት ይኖራሉ።

እያንዳንዱ ተርጓሚ ጎምዛዛ ማለት ነዉ ብሎ መተርጎም እና የትርጉሙን ለመጀመርያ ግዜ ሰሚ በትርጉሙ መደናገርን ከወዲሁ መገመት ይቻላል።

የከተማዋ አስተዳደር ካለ ይሁን ምንም ኣይዴለም ብሎ ኣለፈዉ?