Page 1 of 1

እግዝኣብሔር ከሌለ ተዓምራትን የምያሳይ ምንድነዉ?

Posted: 12 Jan 2026, 17:20
by Naga Tuma
የኣንድ ትዉልድ የኢትዮጵያ ተማሪዎች መባዘን እጅግ በጣም ይገርማል።

ንጉሠ ነገሥት ኣፄ ሀይለሥላሴ በኣብዮት ዙፋን ይልቀቁ ተብሎ ሃገር ተናወጠች።

ኢትዮጵያ ዉስጥ ጭቆና ተሽሮ ፍትህ እና እኩልነት ይስፈን ማለት ተገቢ ቢሆንም በቀልበቢስነት ኣብዮት ብሎ መባዘን እግዝኣብሔርን ማስከፋት ማለት ምልክት ሊሆን ይችላል። ኣይችልም?

የዛዉ ትዉልድ አባላት እግዝኣብሔር ዐይኖች ስለሌሉት ኣያይም በማለት የእግዝኣብሔርን ስፍራ እንዉረስ ያሉ ሆነዋል። ኣልሆኑም?

ከጥቂት ዓመታት በፊት እዚሁ መድረክ ላይ ሆረስ እና ምስራቅ የእርስ በእርስ ግብግብ ሲገጥሙ እያነበብኩኝ ኣስተዉዬ ሃገር ገና በርካታ ምሁራን የሚባሉ ስለሌላት ሁለታችሁ የእርስ በእርስ ግብግብ ትታችሁ ለሃገር በኣንድነት እንድትለፉ እኔ የእናንተ ታናሽ እናንተን መምከር ኣለብኝ ብዬ ጠየኳቸዉ። ይህ ጥያቄ መጠየቁ መካድ የማይቻል ነዉ።

ሰንብተዉ ሁለቱ ከዱላ ቀረሽ ግብግብ በኋላ ተስማማን ብሎ ምስራቅ እዚሁ መድረክ ላይ ምስክርነቱን ሰጠን።

ግፍ ኣይፈሬዎቹ ሆረስ እና ምስራቅ እግዝኣብሔር የማያይ ስለሆነ ኣንተ እግዛኣብሔር በአሰራሩ ኣለ የምትለዉ ኣታዉቅም ብለዉ ተባብረዉ ይወቅሱኛል።

እኔ እ አ አ ከ1992 ወዲህ የሃይማኖት ቤት ሄጄ የማላዉቅ የእግዝኣብሔር አሰራር መኖሩን ስከራከር እነሱ እግዝኣብሔር ማለት የሰዉ ልጅ ምናብ ስለሆነ ማየት የማይችል ነዉ ብለዉ ተነስተዋል።

በዚህ ዘመን ከተከሰቱት ተዓምሮች ዉስጥ ኣንዱ እግዝኣብሔር የሰዉ ልጅ ምናብ እንጂ ዐይኖች የሌሉት ማየት የማይችል ነዉ የሚለዉን ሆረስ የኣንድ ሰዉ የአባት ኣምላክ ወይም አያነ አባ ለዘላለሙ ያጠፈረዉ መሆኑ ነዉ።

እሱ ኣላስተዋለም ይሆናል። እኔ ኣስተዉዬ እጅግ እየደነቀኝ እንዴት ሊሆን እንደቻለ መፍታት ተስኖኛል።

የአባት ኣምላክ ወይም አያነ አባ ህሊና ዬለሽ ህሊና ያለዉ ኣዕምሮ ዉስጥ መግባት ሲሞክር ቀልቦ የምያፈርጥ ይሆን?

የንጹሓንን እምባ ኣፍሳሽን የሚቆጥርበት ይሆን? ስለዚህ ጉዳይ የሃይማኖት መጽሓፎች የሚሰጡት ምስክርነት ምንድነዉ? ሃይማኖተኞች እስቲ ኣስተምሩን።

ድሮ ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥ ለመላላጥ ነዉ ይባል ነበር።

በዚህ ዘመን እግዝኣብሔር በአሰራሩ ካፈረጠ በኋላ መንፈራገጥ ለምንድነዉ እንበል?

የዚህ ዘመን ዳያብሎስ ሲወስድ እያሳሳቀ መሆን ኣለባት። መፈክሩ ከነን ጉንጉማ ዴመ የሆነ ምንድነዉ?

እግዝኣብሔር ዬለም ከሚሉት እና እግዝኣብሔር በአሰራሩ ተዓምራትን የምያሳይ ነዉ ከሚሉት የምያሸንፉት ዬትኞቹ ናቸዉ?