Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Zmeselo
Senior Member+
Posts: 37096
Joined: 30 Jul 2010, 20:43

How to humiliate the fatso!

Post by Zmeselo » 07 Jan 2026, 12:56

"እነ ጌታቸው ረዳ ... ድሮ... ድሮ ድሮ... ልጅ እያሉ" 😂

(By Ethio Lead ) - በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ75ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት ተዘጋጅቶ በነበረው ሴሚናር ላይ: የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ንግግር በኢንተርኔት መንደር ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥናታዊ ጽሁፍ አቀራረብና በፖድካስት ዘይቤ በነበረው ቆይታ: የቀድሞውን የትግራይ ተዋጊዎች አመራርና የአሁኑን አማካሪያቸውን ጌታቸው ረዳን "ጎንተል" የሚያደርግ ንግግር አድርገዋል።

"ድሮ ድሮ እነጌታቸው ህፃን እያሉ አዲስ አበባ የሚሰራውን ስራ 'ብልጭልጭ' ነው ይሉ ነበር፤ አሁን ግን ስላደጉ እንዲህ የሚሉ አይመስለኝም" በማለት በግልጽ ተናግረዋል።

​ይህ ንግግር ከቀልድ ወይም ከቀላል ወግ ያለፈ ጥልቅ የፖለቲካ ስሌትና "የበላይነትን" የማሳየት ፍላጎት የታየበት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጌታቸው ረዳንና መሰሎቻቸውን "ህፃን ነበሩ" ማለታቸው፣ የቀድሞ ተቃውሟቸውንና ትችታቸውን እንደ "አለመብሰል" ወይም "እንደ አለማወቅ" በመቁጠር የራሳቸውን የፖለቲካ ስብዕና እና ራዕይ "ከፍተኛና የበሰለ" አድርገው ለማቅረብ የሞከሩበት ስልት ነው።

ይህ አይነቱ አገላለጽ የቀድሞ ተቀናቃኞችን አሁን ባለው የፖለቲካ አሰላለፍ ውስጥ "ተቀባይ" ወይም "ተማሪ" አድርጎ የመሳል ስነ-ልቦናዊ ጫና የመፍጠር አላማ አለው።

​በተጨማሪም፣ "አሁን ስላደጉ ሀሳባቸውን ቀይረዋል" የሚለው አገላለጽ፣ መንግስት እያከናወናቸው ያሉትን እንደ "ኮሪደር ልማት" ያሉ ስራዎችን ተቃዋሚ የነበሩ አካላት እንኳን ሳይወዱ በግድ እውቅና እንዲሰጡ የማድረግ የፖለቲካ የበላይነት (Political Dominance) ማሳያ ነው።

ጌታቸው ረዳን በአደባባይ እንዲህ ባለ መልኩ መጥቀሳቸው፣ በሁለቱ አካላት መካከል ያለውን "የአዛዥና ታዛዥ" ግንኙነት ለህዝብ ፍንጭ ለመስጠት የታለመ ይመስላል። በአጠቃላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን አጋጣሚ የተጠቀሙት የራሳቸውን የልማት ጉዞ ትክክለኛነት ለማረጋገጥና የቀድሞ ተቺዎቻቸውን ድምፅ ለማለዘብ እንደሆነ መረዳት ይቻላል። 😂





አቤት ውርደት ... ደግሞ ፊት ወንበር ላይ አስቀምጦ ነው እንዲህ የሚወርፈው ... 😆