Page 1 of 1

ዉሳኔ 96 እና ሆረስ

Posted: 06 Jan 2026, 14:55
by Naga Tuma
እኔ ስለ ኢትዮጵያ ፖለትካ ከባህር ማዶ ሆኖ አስተያየት የሚሰጥ ግለሰብ ነኝ።

ከልጅነቴ ጀምሮ የእኔ ዝንባሌ አካዳሚ፣ በተለይም ሂሳብ እና ሳይንስ፣ እንጂ ስለ ሕዝባዊ ፖለትካ ሆነ ማህበራዊ አኗኗር ጥናት ኣልነበረም።

ስለ ፖለትካ ጉዳይ ማንበብ ሆነ አስተያየት መስጠት ወደ እኔ መጥቶ እንጂ ፍለጋዉ ያልሄድኩኝ ነበርኩ።

ተምረናል የሚሉ አማርኛ ተናጋሪዎች ሆኑ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ኢትዮጵያዊያን አስተሳሰብ ካደኩበት ማህበረሰብ አስተሳሰብ ዝንፍ ሲል እያስተዋልኩኝ እንደዚህ ኣይዴለም የማለት ሂስ ኣልፎ ኣልፎ እገልጽ ነበር።

ያንን ኣልፎ ኣልፎ ሂስ መስጠት ሰልችቶኝ ያለኝን አስተያየት ኣካፍዬ ወደ ኣካዳሚ ለማተኮር ወሰንኩኝ።

በቅንነት ያካፈልኩኝ አስተያየት ንትርክ ኣስነስቶ አስተያየቴን ማካፈል ቀጠልኩኝ።

ዉሳኔ 96 የምለዉ እንደ እ ኢ አ በ1996 የኦሮምያ ክልል መቀመጫን ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ እንዲዛወር የተደረገዉን ዉሳኔ ነዉ።

በዚህ ግዜ ወደ ኋላ ተመልሼ ሳስብ እና የሆረስን ልፋት ሳጠና ዉሳኔ 96 ዉስጥ መለኮታዊ አሰራር ምልክትን ያስተዋልኩ ይመስለኛል።

ለዚህ ምልክት በጣም ቀላል ጥያቄ ሆረስ በዛ ዉሳኔ ሂደት ዉስጥ ምን ሚና እንደነበረዉ እራሱን ጠይቆ ለእራሱ መልስ ማግኘት ነዉ።

ይህን ግለሰብ መድረክ ላይ የሚጽፈዉን ከማንበብ ዉጪ በአካል ኣላዉቀዉም።

አስተያየቱን እያነበብኩ እንወያይ ያልኩት ከ18 ዓመታት በፊት ነበር።

የኢትዮጵያ ሆነ የኤርትራ ምሁራንን እየፈለኩ የነበረ ስለሆነ ካሉን ዉስጥ ኣንዱ ይህ ሰዉ ሊሆን ይችላል ብዬ ኣሰብኩኝ።

ብዙም ሳልቆይ ታዝቤዉ ኣለፍኩኝ።

ይህ ሰዉ ካለን ምሁር ዉስጥ ኣንዱ ነዉ ብልም እኔ ከምመኛቸዉ ልሂቅ ደረጃ የደረሰ ነዉ ብዬ ኣላምንም።

ምክንያቱም ቆም ብሎ ከማስተዋል ይልቅ በሃገር ፍቅር ምኞቱ ላይ ተንተርሶ የሚሯሯጥ ነዉ።

ለሃገር ብሎ መልፋት መልካም ነዉ። ያላስተዋልከዉ ኣለ ሲባል ቆም ብሎ የማስተዋል ችሎታ ማነስ ወይም ማጣት ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለተከበረች ሃገር ስምም መልካም ኣይሆንም።

ይህ ግለሰብ ኣብዮት ያሉት የኢትዮጵያ ተማሪዎች አካል ነበር።

ከሃምሳ ዓመታት በፊት በኣብዮት ንጉሠ ነገሥት ኣፄ ሀይለሥላሴ ይነሱ ያሉት የኢትዮጵያ ተማሪዎች ከሃምሳ ዓመታት በኋላ መለኮታዊ አሰራር ዬለም እና የእግዝኣብሔርን ስፍራ እንዉረስ ያሉ ሆነዉ ተገኙ።

ይህ ግለሰብ በጣም የሚገርመኝ ለዚህ ነዉ።

የተዋጣለት ምሁር ነዉ ልለዉ ኣልችልም። ምክንያቱም የተዋጣለት ምሁር ከሆነ ዉሳኔ 96 ዉስጥ ሚናዬ ምን ነበረ ብሎ የጠየቀ ኣይመስለኝም።

ዉሳኔዉ ዉስጥ መለኮታዊ አሰራር ከነበረ ለምንድነዉ የሚካሄደዉን ለዉጥ ከፊት ነኝ የምለዉ ማለት የማይችል ሰዉ ይመስለኛል። የፈርሃ እግዝኣብሔርነት ትህትና የሌለኝ ለምንድነዉ ብሎ እራሱን መጠየቅ የማይችል ሰዉ ይመስለኛል።

ይህ ብቻ ሳይሆን መለኮታዊ አሰራሩን ሲጋፋ እዚሁ ፎረም ላይ ምልክቱን ኣንብቦ ጆሮ ዳባ ልበስ ያለ ሰዉ ነዉ።

የሃይማኖት ሰዉ ነዉ እንዳልለዉም የሃይማኖት መጽሓፍ እራሱ የሚናገረዉን ቆም ብሎ ማስተዋል የማይችል ሰዉ ነዉ።

ኢትዮጵያ ሆነ በዐለም አቀፍ ደረጃ ከዚህ ዘመን ትግል የበለጠ የንጹሓን እንባ የፈሰሰበት ግዜ ያለ ኣይመስለኝም።

በእኔ አስተሳሰብ የሰዉ ልጅ ታግዬ ያመጣሁት ከሚለዉ ለዉጥ እጅግ የበለጠ መለኮታዊ አሰራር ዉስጡ መኖሩን ምልክቶችን የማስተዉል ይመስለኛል።

የማያቸዉ የሚመስሉኝ መለኮታዊ ምልክቶች ከዚህ ዘመን በኋላ በዚህ ምድር ላይ በመለኮታዊ አሰራር የማያምን ኣንድም ሰዉ እንዳይራመድ የምያደርግ ነዉ። ይህ ከሆነ ደግሞ በምንም ስም ይጠራ ስሞቹ መቶ የሆኑት ኣንድ እግዝኣብሔር የሰዉ ልጆችን ኣሸነፈ ይባላል ማለት ነዉ።

ይህን ኣስተዉዬ ሳሰላስል የተገለጠልኝ የሚመስለኝ አስተሳሰብ ገነት የተባለ ስፍራ ምን ይመስላል ቢሎ ፈርሃ እግዝኣብሔር ያልሆነ ሰዉ ፈጽሞ የማይረማመድባት ምድር ናት ማለት ነዉ ኣስባለኝ።ይህ ከሆነ ደግሞ ይህን መፈጸም የሚችል የሰዉ ልጅ ሳይሆን እግዝኣብሔር ብቻ ነዉ ኣስባለኝ።

ለዚህ አሰራሩም ሰዎችን እያለፋ እና እየፈተነ ለወደፊት ዘመናት ምሳሌዎችን እያዘጋጀ ያለ ይመስለኛል።

እስከ ኣሁን የሚታዩ የሚመስሉኝ ምሳሌዎች አደቡ፣ ዳያብሎሱ፣ ወራዳዉ፣ ቀጥሎ ወራዳዉ፣ ምናልባትም ዕዉሩ መባል የሚችሉ ናቸዉ።

እስቲ ኢትዮጵያዊያን ሆናችሁ ኤርትራዊያን፣ ምሁራን ሆናችሁ ኣማኞች፣ ይህ አስተያየት በጣም ጥልቅ ኣማኝ የሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተሳሰብ ለየት ወይም ዝንፍ የሚል ነዉ ማለት ትችላላችሁ?

በቅርቡ የተገለጠልኝ የዚህ አስተያየት ማሳረግያ ይሁን።

ኣፄ ምኒልክን የሰጣችሁ
እግዜር ዬለም ያላችሁ
ፈረዖዎችን ቀሰቀሰባችሁ
መሬት እንዴት ትዋጣችሁ?