sesame wrote: ↑04 Jan 2026, 00:00
There is a branch of mathematics called Catastrophe Theory!
sesame:
I wonder if you are a mathematician.
Before I read your comment about the theory you write here, I was trying very hard to understand about what might be a probabilistic impossibility.
So, I invite you to think about it from a scientific viewpoint and imagine if it can be a probabilistic possibility.
እባክህ የሚከተለዉ ታሪካዊ ክስተት መከሰት የሚችልበትን ምድራዊ ፕሮባቢሊቲ ማብራራት የሚችል ሰዉ ካለ ፈልግ?
ታሪኩ የተከሰተዉ እ አ አ በ1987 ነዉ።
ሶስት ስፍራዎችን ያያዘ ነዉ፥ ስፍራ ሀ፣ ስፍራ ለ፣ እና ስፈራ ሐ።
ስፍራ ሀ የገጠር ቀበሌ ነዉ። ስፍራ ለ ከተማ ነዉ። ስፍራ ሐ አዲስ አበባ ነዉ።
የገጠር ቀበሌ ከከተማዉ በእግሮች የሁለት ሰዓታት መንገድ ነዉ።
ከተማዉ ከአዲስ አበባ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።
በተጠቀሰዉ ዓመተ ምህረት የማትሪክ ዉጤቱን ይጠባባቅ የነበረ ተማሪ ኣንድ መስከረም ቀን ከስፍራ ሀ ወደ ስፍራ ለ ሄደ።
አዲስ አበባ ዩኒቨርዚቲ ይማር የነበረ ታላቅ ወንድሙ የታናሽ ወንድሙን ዉጤት ቀድሞ ሰምቶ ተደስቶ ብቻ ሳይሆን ተሯሩጦ ጥቁር አንበሳ እንዲመደብ እሺ ተባለ።
እሺ ከተባለ በኋላ ለታናሽ ወንድሙ ደብዳቤ ጽፎ ተሯሩጦ አዲስ አበባ ዉስጥ አዲስ ከተማ ይባል የነበረ ስፍራ የነበረ አዉቶብስ ተራ ሄዶ ደብዳቤዉን ከአዲስ አበባ ወደ ስፍራ ለ ከተማ ለመሄድ የተዘጋጀ አዉቶብስ ዉስጥ ለነበረ ኣንድ መንገደኛ ሰዉ ይሰጥ እና በከተማዉ ዉስጥ እዚህ ስፍራ ስትደርስ ወይም ስትደርሺ ወርዉሪ ይላል።
ስፍራዉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ስለሆነ የማይሳት ነዉ።
ትምህርት ቤቱ ፊት ለፊት የዘመዶች ቤት ነዉ።
መንገደኛዉ በተባለዉ ወይም በተባለችዉ መሠረት በስፍራዉ ደርሶ ወይም ደርሳ ደብዳቤዉን ሲወረዉር ወይም ስትወረዉር ተማሪዉ የዘመዶቹ ቤት ፊት ለፊት ከሌሎች ሰዎች ጋር ቆሞ ስለነበረ ወረቀት ከአዉቶብስ ዉስጥ ሲወረወር ኣይቶ ተገረመ።
የተወረወረዉን ወረቀት ከመሬት ላይ ማን ቀድሞ እንዳነሳዉ ተማሪዉ ኣያስታዉስም።
የተወረወረዉ ወረቀት ሲታይ ለተማሪዉ የተላከ ደብዳቤ መሆኑ ታወቀ።
ስለዚህ ደብዳቤዉን ከፍቶት ኣነበበ። ማለፉን ይጠብቅ ስለነበረ ኣልተገረመም።
ጥቁር አንበሳ ተመደብ መባሉን ስያነብ በጣም ደነገጠ። በወጣትነቱ የሜዲካል ዶክተር ሆኖ መስራት ቀርቶ ሆስፒታል ሄዶ ሰዉ መጠየቅን የማይወድ ነበር።
ስለዚህ ጥቁር አንበሳ ሄዶ መማር ከማትሪክ ፈተና በኋላ ከመረጣቸዉ ሶስት ስፍራዎች ዉጪ ነበረ። ፍላጎቱ ስላልሆነ ብቻ ነዉ።
ለዚህም ያልመረጠዉ ቦታ ተመደብ መባልን ስያነብ በጣም ደንግጦ በሩጫ የከተማዉ ስልክ ቤት ደርሶ ወደ አዲስ አበባ ደዉሎ ለታላቅ ወንድሙ መልዕክት እንዲደርሰዉ ጣረ።
መልዕክቱ ለታላቅ ወንድሙ ደርሶ ሀሳቡን ኣነሳ።
ተማሪዉ በኣንደኛ ደረጃ የመረጠዉ ስፍራ ሄዶ ተማረ። ፍላጎት ሆኖ ሊሆን ይችላል የተማሪዉ የመጀመርያ ሰምስተር ዉጤት ከሁሉ የላቀ ሆነ።
ታሪካዊ ገጠመኙ በወቅቱ ግጥምጥሞሽ ወይም ኮይንሲደንስ መስሎ ታለፈ።
ከብዙ ዓመታት በኋላ እዚህ መድረክ ላይ መልስ ሲሆን ክስተት ይመስላል። ይህ ክስተት ኣንድ ምልክት ቢመስልም ብቸኛ ክስተት ኣይመስልም።
ስለዚህ ለእኔ ብለህ ሳይሆን ለጓዶችህ ብለህ ይህ ታሪካዊ ገጠመኝ ሊሆን የሚችል ምድራዊ ፕሮባቢሊቲ ነዉ ማለት ትችላለህ?