አበረ፥
እዚህ መድረክ ላይ ስለ ሳይንስ እና ሳይንሳዊ አስተሳሰብ ከተባለ በፈቃደኝነቴ ከሆረስ በላይ የለፋሁበት ያለ ኣይመስለኝም።
ካሉት ዉስጥ ኣንዱ ነዉ ብዬ ከ18 ዓመታት በፊት ሞከርኩት። ትልቁ ችግሩ እኔ ኣዉቃለሁ፣ ኣንተ ኣታዉቅም ማለት ነበር። እንደዚህ ዐይነት አስተሳሰብ ከምሁራዊ አስተሳሰብ የራቀ ነዉ።
ሰንብቶ ኣንድ ስለ ትንሳዔ ማለት እና ሬይነሳንስ ማለት የጸፈዉን ሳነብ ማመን ኣቅቶኝ እጆቼን በአፌ ላይ ጭኜ መልሼ መላልሼ ኣነበብኩት።
ከብዙዎች የተሻለ ዕዉቀት ያለዉ ነዉ ብዬ ብገምትም የማይጠበቅ ስህተትን ሲገልጽ እያስተዋልኩኝ በፈቃደኝነቴ ለማረም እለፋለሁ።
ትላንትና እንደ ፌዝ ሰዉ ቡዳ ሆኖ ሰዉ ይበላል ከተባለ ከ18 ዓመታት በፊት ነበር የበላሁህ ያልኩት ካልዘነጋሁ በከተማ ቋንቋ ስለ ምሁራዊ አስተሳሰብ ተረተህ ነበር፣ ተሸንፈህ ነበር ለማለት ነዉ።
ስለ ኢትዮጵያ የዉስጥ ፖለትካ ጉዳይ ደግሞ በፈቃደኝነቴ ከሰን በላይ የለፋሁበት ያለ ኣይመስለኝም።
የሰን መሠረታዊ ችግር ስለ ኢትዮጵያ ፖለትካ ሆነ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን ከእሱ በላይ ማን ኣዉቆ ብቻ ሳይሆን የምያዉቀዉንም የማያዉቀዉንም ድክቴት እያደረገ መቀበል ኣለባችሁ ማለት ነዉ።
የሰን በጡንቻ ሳይሆን በቃላት ሆነ እንጂ ከመንግስቱ ሀይለማርያም የበለጠ ድክቴተር ነዉ።
ካልተሳሳትኩ ደርግ የክፍለ ሃገሮች የራስ ገዝነት ጥያቄ ጥናት ይደረግ ያለ ሲሆን ሰን የክልሎች ጉዳይ ከተነሳ እንዴት ይነካ ብሎ የሚዘል ነበር።
ስለእሱም ሰንብቼ ይህን የቦረኙዋ ሰዉን በጣም ኣጭር ጥያቄ ብጠይቀዉ ተሰምቶት ዕዉነት የሆነ መልስ ሰጠ።
የመለሰዉ ትክክለኛ መልስ እሱን ከያዘዉ ኣዙሪት በሳይንሳዊ መንገድ ያላቀዋል ብዬ ባልፍም ዞሮ ዞሮ ኣዙሪቱ ዉስጥ ክርችም የሚል ሆኖ ኣገኘሁት።
ዛሬ ጠዋት ይህን መድረክ ሳልከፍት በፊት በቅርቡ እዚሁ ፎረም ላይ የጻፍኩትን ትዉስታ ኣስታዉሼ ይህ ሰዉ የሞከራቸዉ ተራ በተራ ፉርሽ ከሆኑበት መለኮታዊ ብይን እያገኘ ያለ ሰዉ ኣይደለም ወይ ኣስባለኝ።
እኔ ኢትዮጵያ ኮሌጅ ተማሪ ሆኜ ኣንድ ዜና ስሰማ ዜናዉ ዉስጥ መማር እንፈልጋለን፣ ነገር ግን ከዚህ የተማርነዉ ምንም ዬለም ማለትን ሰማሁኝ።
መማር እንፈልጋለን ማለትን ስሰማ እንዲህ መናገር ነዉ እንጂ ብዬ ዘና ኣልኩኝ። ዘና ብዬ ኣፍታም ሳልቆይ ከዚህ ምንም የተማርነዉ ዬለም ማለትን ስሰማ ኣስቆኝም፣ ኣሳዝኖኝም ኣለፍኩኝ።
ይህን የምጽፍ ሰዉ ኣብዛኛዉን ዕዉቀቴን ያገኘሁኝ በደርግ ዘመን ከሆነ ይህ የምያሳየዉ መለኮታዊ ምልክት ኣለ ወይ ያስብለኛል።
የደርግን ስህተቶች፣ በተለይም የሃገር መሪዎችን እና መኮንኖችን ተራ በተራ በኣንድ ምሽት መቅሰፍን መርሳት እንዴት እንደሚቻል ኣላዉቅም። ያም ሆኖ የደርግን የኢትዮጵያ ትቅደም ልባዊ ምኞትንም መርሳት እንዴት እንደሚቻል ኣላዉቅም።
የመለኮታዊ አሰራር ምልክቶችን ማጥናት ለሚፈልግ ሰዉ ከበቂ በላይ ያሉ ይመስለኛል።
ስለ ጉዳዩ እያሰላሰልኩኝ ቆይቼ ይህን መድረክ ስከፍት የኣንተን ርዕስ ኣይቼ ኣነበብኩኝ።
ስለ መለኮታዊ ነገር ደግሞ እዚህ መድረክ ላይ በፈቃደኝነቴ ከኣንተ በላይ የለፋሁበት ያለ ኣይመስለኝም።
ምክንያቱም ኣልፎ ኣልፎ ስለ መለኮታዊ ነገር ስትጽፍ የኣንተ ግንዛቤ መሠረታዊ ወይም ኦርጋኒክ የሆነ ይመስለኛል።
ከኣሁን በፊት መለኮታዊ ስምርት የሚገለጠዉ መቼ ነዉ ብዬ ጠቃሚ ጥያቄ ጠይቄህ ነበር። በተልይም ስምሪት ሳይጀመር በፊት ነዉ፣ በስምሪት ሂደት ዉስጥ ነዉ፣ ወይስ ስምሪቱ ከተፈጸመ በኋላ ነዉ ብዬ ጠይቄህ ነበር።
ምልክቶችን የምገነዘብ ስለሚመስለኝ ነዉ።
ለምሳሌ የሰን ነገርን ብቻ ማጥናት ከበቂ በላይ ነዉ ያስብለኛል። ሞክሮ ፉርሽ የሆኑበትን መቁጠር መለኮታዊ አሰራር እና መለኮታዊ ብይን ዉስጡ ዬሉም ወይ ያስብላል።
የኣንተ ደግሞ ትልቁ ችግር መለኮታዊ ነገርን እና ፖለትካዊ ነገርን መቀላቀል ነዉ።
መለኮታዊ ነገር ከፈረዖዎች ጋር የነበረ ነዉ ወይ ብያለሁ።
ስለ መለኮታዊ ነገር ደጋግመህ ስለምታነሳ ከእኔ በላይ ለኣንተ መገለጥ ነበረበት ብዬ ኣስባለሁ።
መለኮታዊ ነገር ከፈረዖዎች ጋር የነበረ ከሆነ ከታላቁ ፈረዖ አክናተን ጋር ከኢትዮጵያ እና ኣፍርካ ምድር የተሰደደ ሳይሆን ኢትዮጵያ ዉስጥ ከኖሩት ፈረዖዎች ጋር የሰነበተ እና የጠበቃት ሊሆን ይችላል?
ለዚህም ጥያቄ መልስ ከእኔ በላይ ኣንተ ማወቅ ኣለብህ ባይ ነኝ። ምክንያቱም ከእኔ በላይ ኣንተ ስለ መለኮታዊ ነገር ስለምታወራ ነዉ።
ምናልባት ቦረና ዉስጥ የኖሩት ኢትዮጵያዊያን በፈረዖዎች ዘመን መለኮታዊ ነገርን እና ፖለትካዊ ነገርን ለየብቻ ያደረጉት ለምን ነበረ ብለህ ብታጠና ይጠቅምህ ይሆናል።
መለኮታዊ አሰራር ኣንተንም ለሆነ ምሳሌ ያዘጋጀህ ካልሆነ ማለት ነዉ።
Abere wrote: ↑30 Dec 2025, 10:10
እግዜር ሲቆጣ ልምጭ አይቆርጥም----> Axumezana አፍቃሪ ወያኔን እግዜር ሲቀጣው አለንጋ/ ልምጭ/ ይዞ ውርዶ ሳይሆን ኦሮሙማ አባገዳ በላዩ ላይ አስቀምጦ ገረፈው። የአገር እና የእናት ትርጉሙ ሳይገባው ጡት ሲነክስ ፤ሃይማኖት ሲያረክስ የኖረ ወፈ-ሰማያት ወያኔ በኦሮሙማን ጥርስ አስገብቶ አስነከሰው፤ አጀንዳየ አስጨፈረው። መነኩሴ ቁብ ሲል የነበረ ወያኔ ኦሮሙማ ላዩ ላይ ቁብ አለበት - እንደ ባቢሎን ከፋፍሎ አፈረሰው። ለኃጣን የወረደ ለጻድቃን ይተርፋል እንድሉ ለመናፍቃን ወያኔዎች የወረደው ማዕበል ለሌሎች ተርፏል።
Axumezana wrote: ↑30 Dec 2025, 11:56
አበረ
ዙቋላ ላይ ሆኖ ይታያል አዋሽ
የAxumezana ግዛት እልፍ ብሎ ትንሽ
የህይወት ውሃ ምንጭ ከኦሮምያ የሚፈስ
በእግሩ ረገጠው የገዳውን መንፈስ
ከአርያም ተቀብቶ በዳዊት፥ በሙሴ፥ በፓውሎስ መንፈስ
አጋንንቱን ይገዛል አንበርክኮ በሰልፍ
ከትግራይ ተነስቶ ታዬ ኦሮምያ
ድብረ ሊባናስ ገዳም የሰይጣን መናሃርያ
ድንገት ደረሰና አደረቀው ቋያ
የነ አበረ PHD ይኸን አይመረምር
አይገባውምና መንፈሳዊ ሚስጥር