Page 1 of 1

የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፍወርቂ የ79 ዓመት ኣዛዉንት ነዉ

Posted: 25 Dec 2025, 05:36
by Naga Tuma
ረዘም ላለ ግዜ እየገረመኝ ያለዉ የዚህ ያህል ዕድሜ ኣዛዉንት ጋላ የሚል ቃል ስህተት ነዉ ብሎ የማያምን ነዉ ወይስ ስህተት መሆኑን ኣዉቆ ቃሉን ሆነ ብለዉ የሚጠቀሙትን ደጋፊዎቹን ስህተት ነዉ ብሎ መምከር የማይችል ነዉ?

ይህ ቃል ለመጀመርያ ግዜ የተሰጠዉ ቦረና ዉስጥ ጥንታዊ ባህልን እንደ ቅርስ ይዘዉ ለሰነበቱ ኢትዮጵያዊያን ነዉ። ይህ ማህበረሰብ በዚህ ዘመን ካሉት የፖለትካ ድርጅቶች ሆኑ የፖለትካ መሪ ይለያል።

ባህላቸዉ ኣጥንቶ ለማሳደግ የሚደነቅ እንጂ የሚናቅ ኣይዴለም።

የፈረዖዎችን ዘመን የባህል ቅርሶችን እነዚህ የኢትዮጵያ ማህበተሰብ ያላቸዉ ሊሆን ይችላል።

ይህ ከተስተዋለ ፈረዖዎች ኢሳይያስ አፍወርቂን የበደሉት ኣለ ወይ ያስብላል።

ከሌለ ስህተት ስለሆነ ተዉ ብሎ መምከር ያቅተዋል ወይስ ደጋፊዎቹ ምክሩን የማይሰሙ ናቸዉ?