Page 1 of 1
ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?
Posted: 22 Dec 2025, 12:45
by Abere
ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ? ደራሲው ውሉደ አውሬ ነው (aka Deqi-Arawit)።

Re: ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?
Posted: 22 Dec 2025, 12:54
by Affable
Despite believing the author is an expert to write the book, I have no intention of buying it.
Re: ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?
Posted: 22 Dec 2025, 13:28
by Dama
It just too obvious from title that there isn't anything new I will learn from it.
The author is advised to consult with a marketing or branding professional for his next book.
Re: ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?
Posted: 22 Dec 2025, 14:03
by Abere
ሁሬሳ
Re: ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?
Posted: 23 Dec 2025, 08:43
by Meleket
Re: ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?
Posted: 23 Dec 2025, 10:38
by Abere
ወንድም መለከት፤
የአጤውን ጡጫ ማን ያልቀምሰ ነበር - ጎጃም፤ባሌ፤ ጎንደር፤ ወሎ ወዘተ ቀምሰዋል። ኤርትራ ክ/ሀገር ብቻ አልነበረችም። ጡጫ የሚደገፍ አይደለም።
አንድ አባባል አለ
ከድሃ የግብዣ መአድ፤ የንጉስ ጉርሻ ያጠግባል የሚል። የዐጼ ሀይለስላሴ ዘመኗን ኤርትራ ከኢሳይያስ ዘመኗ ጋር ማነጻጸር በቂ ነው። አቶ ኢሳይያስ ጤፍ ሽጦ፤ ባቄላ ሸምቶ የኤርትራ ህዝብ በእጅ እያስፈጨ ያለ ይመስለኛል። ዝንጀሮ ትንሽ ቁስል ጭሮ ጭሮ ምን ያደርጋታል እንድሉ ነው የአፈር ወርቅ ልጅ የሰራው። በኤርትራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ባለው ሁኔታ እናዝናለን..
Re: ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?
Posted: 24 Dec 2025, 05:03
by Meleket
ወዳጃችን ወንድም Abere የኤርትራ ህዝብን በጡጫቸው ለመደቆስ ያሰቡትና ያለሙት አጤ ሃይለስላሴ ብቻ መስለውሃል እንዴ? ደርጉም እኮ እድሜውን ሙሉ የኤርትራን ህዝብ ለማንበርከክና የህዝቡን መብትና ፍትሃዊ ጥያቄ ለማዳፈን ነበር የሰራው፡ በውይይት ሳይሆን በአዳፍኔ! ኢሕኣዴግም እንዲሁ መንበሩን በኤርትራዉያን ጥረትም ካጸና በኋላ፡ ተመልሶ ያጎረሰን እጅ መንከስ ነበር የመረጠው! ብልጥግናዉም እንዲሁ፡ የጦቢያ መሪዎች በሽታ ተመሳሳይ ነው።
የንጉስ ሆነ የደርግ ካድሬ ጉርሻ ምን እንደሚመስል በከፊል እዚህ ላይ ታዝበነዋል።

https://hdrimedia.com/product/gfei/
Re: ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?
Posted: 24 Dec 2025, 10:28
by Abere
ወንድም መለከት፤
ግፍ መቸ ከሰማይ ስር ጠፍቶ ያውቃል። ችግሩ ዘመን በጨመረ ቁጥር ግፉ የትዬ ለሌ እየደረሰ እንጅ። ዐይናችን በኤርትራ ክፍለ ሀገር የተሻለ እያየ ጆሯችን በጎ ነገር እየሰማ ሳይሆን በወላድ ማህጸን ያሉ እምቢ አልወለድም እያሉ ነው፡፡
እንኳን ወደ ኤርትራ መጣሁ ሳይሆን በእግዚአብሄር! ወደ እናቴ ሆድ መልሱኝ ብለው የሚማጸኑበት ክ/ሀገር እንጅ የተስፋዋ ምድር ባልሆነችበት ጉዳይ ላይ እሰጥ አገባ የሚያስፈልገው አይመስለኝም።
Re: ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?
Posted: 26 Dec 2025, 11:41
by Meleket
ወዳጃችንና ወንድማችን Abere የተስፋይቱን ምድር እዚህችዉ ምድር ላይ ዬምንጠብቅ ቢሆን ኖሮ፡ ኣባባልህን ድንቅ ኣባባል ባልነው ነበር! ነገር ግን ኢትዮጵያም ሆነች ኤርትራ “የተስፋይቱን ምድር ለመውረስ” ግዜ ሳለን መልካም ተግባር እንድንተገብርባቸው የተሰጡን ጊዚያዊ መቆያ ስፍራዎች መሆናቸውን ጠንቅቀን እናውቃለን። አሁን ከቻልን ወደ ሕጻጽና ዳባት ኣካባቢ ያሉ በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎችን እምንረዳበት ግዜ ነው፡ ትሩፋት በማፈስ የተስፋይቱን ምድር የመውረሻ ሁነኛ ተግባር እንድንከውን የምንጠየቅበት ግዜ ነው።
ዋይ ዋይ ዋይ ሲሉ ተብሎ ባይዜምላቸውም፡ የህጻጽና የዳባት የወዘተም መጠለያ ጣቢያ ሰፋሪዎች ችግር ላይ ናቸውና ለነዚህ ሰብኣውያን ፍጡሮች ትደርሱላቸው ዘንድ ለመጠየቅ ያህል ነው። እኛም የበኩላችንን በጎ ተግባር እንደማንነፍጋቸው ለማሳወቅ ያህል ነው ወንድም Abere ።
Abere wrote: ↑24 Dec 2025, 10:28