Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15174
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?

Post by Abere » 22 Dec 2025, 12:45

ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ? ደራሲው ውሉደ አውሬ ነው (aka Deqi-Arawit)።

:lol: :lol:


Affable
Member
Posts: 742
Joined: 15 Jul 2023, 13:21

Re: ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?

Post by Affable » 22 Dec 2025, 12:54

Despite believing the author is an expert to write the book, I have no intention of buying it.

Dama
Member+
Posts: 7376
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Re: ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?

Post by Dama » 22 Dec 2025, 13:28

It just too obvious from title that there isn't anything new I will learn from it.
The author is advised to consult with a marketing or branding professional for his next book.


Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?

Post by Meleket » 23 Dec 2025, 08:43

ወዳጃችን ወንድም Abere ያልተጻፈ የምናብና የህልም መጸሓፍ ከማንበብ ይልቅ የተጻፈ መጸሓፍ ማንበብ መርጠናል።። የታሪክ ተመራማሪውን የዞባ ዓንሰባ ፍሬ ነጸረኣብ አዛዚን ስለ ጥልቅ የምርምር ስራው በሰፊው እያመሰገንን! "ኣገናዕ" ወዲ አዛዚ ብለናል።

ኣያይዘንም እነዚህ በኢሰብኣዊና ኣረመኒያዊ ግፍ ንጹሓን ኤርትራዉያንን መስጊድና ቤተክርስትያን ውስጥ ሳይቀር ይረሽኑ የነበሩ የጥፋት ሃይሎችን፡ ታጋይ ኢሳያስና የትግል ጓዶቹ፡ ግፈኞቹን ኣይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ረገድ፡ የበኩላቸውን ሚና በመጫወታቸው “ጎበዞች” ብለናቸዋል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።



https://shabait.com/2024/12/18/remember ... 0victims.



ከመገናኛ ብዙሃን እየሰማነው እንዳለው፡ ብልጥግኖች አሁንም በድሮን ይሁን እንጂ፡ ዖና በሰክዲራና ወዘተ ላይ ከዓመታት በፊት እንደተደረገው ተመሳሳይ ጥቃትና ግፍ፡ በመስጊድና በቤተስኪያን ውስጥ ጭምር በሰፊው ያማራ ህዝብ ላይ እያካሄዱ ነው ይባላል። ይህን ግፍ ለመታደግ ማን ይሆን እንደ ኤርትራዉያን ታጋዮች “ለህዝቤ እቆማለሁ” የሚል ኣካል? ማን ይሆን ግፈኞችን የሚጠራርግ አካል? ማንስ ይሆን እንደ ነጸረኣብ አዛዚ ይህን መሰሉን የግፍ ታሪክ በመጻፍ፡ ለመጪው ትውልድ ከበቀል ስሜት በመታቀብ ትምህርት ይሆነው ዘንድ የሚያቆየው! በሂደት ዬምናየው ጉዳይ ነው። ወዳጃችን ወንድም Abere መቼም ይህን ታሪክ በመጻፍ እንደ ኤርትራዊው ነጸረኣብ አዛዚ ለመጪው ትውልዳችሁ ሁነኛ ታሪክ ልታቆይ እንደምትችል ጠርጥረናል!

Abere wrote:
22 Dec 2025, 12:45
ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ? ደራሲው ውሉደ አውሬ ነው (aka Deqi-Arawit)።

:lol: :lol:
...

Abere
Senior Member
Posts: 15174
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?

Post by Abere » 23 Dec 2025, 10:38

ወንድም መለከት፤

የአጤውን ጡጫ ማን ያልቀምሰ ነበር - ጎጃም፤ባሌ፤ ጎንደር፤ ወሎ ወዘተ ቀምሰዋል። ኤርትራ ክ/ሀገር ብቻ አልነበረችም። ጡጫ የሚደገፍ አይደለም።
አንድ አባባል አለ
ከድሃ የግብዣ መአድ፤ የንጉስ ጉርሻ ያጠግባል የሚል። የዐጼ ሀይለስላሴ ዘመኗን ኤርትራ ከኢሳይያስ ዘመኗ ጋር ማነጻጸር በቂ ነው። አቶ ኢሳይያስ ጤፍ ሽጦ፤ ባቄላ ሸምቶ የኤርትራ ህዝብ በእጅ እያስፈጨ ያለ ይመስለኛል። ዝንጀሮ ትንሽ ቁስል ጭሮ ጭሮ ምን ያደርጋታል እንድሉ ነው የአፈር ወርቅ ልጅ የሰራው። በኤርትራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ባለው ሁኔታ እናዝናለን..

Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?

Post by Meleket » 24 Dec 2025, 05:03

ወዳጃችን ወንድም Abere የኤርትራ ህዝብን በጡጫቸው ለመደቆስ ያሰቡትና ያለሙት አጤ ሃይለስላሴ ብቻ መስለውሃል እንዴ? ደርጉም እኮ እድሜውን ሙሉ የኤርትራን ህዝብ ለማንበርከክና የህዝቡን መብትና ፍትሃዊ ጥያቄ ለማዳፈን ነበር የሰራው፡ በውይይት ሳይሆን በአዳፍኔ! ኢሕኣዴግም እንዲሁ መንበሩን በኤርትራዉያን ጥረትም ካጸና በኋላ፡ ተመልሶ ያጎረሰን እጅ መንከስ ነበር የመረጠው! ብልጥግናዉም እንዲሁ፡ የጦቢያ መሪዎች በሽታ ተመሳሳይ ነው።

የንጉስ ሆነ የደርግ ካድሬ ጉርሻ ምን እንደሚመስል በከፊል እዚህ ላይ ታዝበነዋል።



https://hdrimedia.com/product/gfei/

Abere
Senior Member
Posts: 15174
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?

Post by Abere » 24 Dec 2025, 10:28

ወንድም መለከት፤

ግፍ መቸ ከሰማይ ስር ጠፍቶ ያውቃል። ችግሩ ዘመን በጨመረ ቁጥር ግፉ የትዬ ለሌ እየደረሰ እንጅ። ዐይናችን በኤርትራ ክፍለ ሀገር የተሻለ እያየ ጆሯችን በጎ ነገር እየሰማ ሳይሆን በወላድ ማህጸን ያሉ እምቢ አልወለድም እያሉ ነው፡፡

እንኳን ወደ ኤርትራ መጣሁ ሳይሆን በእግዚአብሄር! ወደ እናቴ ሆድ መልሱኝ ብለው የሚማጸኑበት ክ/ሀገር እንጅ የተስፋዋ ምድር ባልሆነችበት ጉዳይ ላይ እሰጥ አገባ የሚያስፈልገው አይመስለኝም።

Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ወንድም Meleket በዚህ መጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ስርዓት ተጋብዘህ ነበር ወይ?

Post by Meleket » 26 Dec 2025, 11:41

ወዳጃችንና ወንድማችን Abere የተስፋይቱን ምድር እዚህችዉ ምድር ላይ ዬምንጠብቅ ቢሆን ኖሮ፡ ኣባባልህን ድንቅ ኣባባል ባልነው ነበር! ነገር ግን ኢትዮጵያም ሆነች ኤርትራ “የተስፋይቱን ምድር ለመውረስ” ግዜ ሳለን መልካም ተግባር እንድንተገብርባቸው የተሰጡን ጊዚያዊ መቆያ ስፍራዎች መሆናቸውን ጠንቅቀን እናውቃለን። አሁን ከቻልን ወደ ሕጻጽና ዳባት ኣካባቢ ያሉ በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎችን እምንረዳበት ግዜ ነው፡ ትሩፋት በማፈስ የተስፋይቱን ምድር የመውረሻ ሁነኛ ተግባር እንድንከውን የምንጠየቅበት ግዜ ነው።




ዋይ ዋይ ዋይ ሲሉ ተብሎ ባይዜምላቸውም፡ የህጻጽና የዳባት የወዘተም መጠለያ ጣቢያ ሰፋሪዎች ችግር ላይ ናቸውና ለነዚህ ሰብኣውያን ፍጡሮች ትደርሱላቸው ዘንድ ለመጠየቅ ያህል ነው። እኛም የበኩላችንን በጎ ተግባር እንደማንነፍጋቸው ለማሳወቅ ያህል ነው ወንድም Abere ።

Abere wrote:
24 Dec 2025, 10:28
ወንድም መለከት፤

ግፍ መቸ ከሰማይ ስር ጠፍቶ ያውቃል። ችግሩ ዘመን በጨመረ ቁጥር ግፉ የትዬ ለሌ እየደረሰ እንጅ። ዐይናችን በኤርትራ ክፍለ ሀገር የተሻለ እያየ ጆሯችን በጎ ነገር እየሰማ ሳይሆን በወላድ ማህጸን ያሉ እምቢ አልወለድም እያሉ ነው፡፡

እንኳን ወደ ኤርትራ መጣሁ ሳይሆን በእግዚአብሄር! ወደ እናቴ ሆድ መልሱኝ ብለው የሚማጸኑበት ክ/ሀገር እንጅ የተስፋዋ ምድር ባልሆነችበት ጉዳይ ላይ እሰጥ አገባ የሚያስፈልገው አይመስለኝም።

Post Reply