Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

ኤርትራዊው የባሕረ ሓሳብ ሊቅ ኣባ ሳሙኤል ኣስገዶም [ሓልሓለ 1915 - ኣሥመራ 2011]

Post by Meleket » 22 Dec 2025, 10:39

ኤርትራዊው የባሕረ ሓሳብ ሊቅ ኣባ ሳሙኤል ኣስገዶም [ሓልሓለ 1915 - ኣሥመራ 2011]

የባሕረ ሃሳብ ምርምርና ጥናት ሲነሳ፡ የኤርትራዊው ተመራማሪ የአባ ሳሙኤል ኣስገዶም [ሓልሓለ 1915 - ኣሥመራ 2011] የምርምር ውጤትን መመርመር ግሩም ነው። ኣባዉ ምርምራቸው የባሕረ-ሓሳብ መምህርም በነበሩት በብፁዕ ገብረሚካኤል ኣኪሎ ጽሑፍ ዙርያ ያጠነጠነ እንደሆነ ይታወቃል።

ኣባ ሳሙኤል ኣስገዶም ማን ናቸው?

ኣባ ሳሙኤል ኣስገዶም ሰኔ 1915 እ.ኤ.ኣ. ሓልሓለ (ጽልማ) በተባለው ኣካባቢ ከኣቶ ኣስገዶም ጋርዛና ወይዘሮ ሓና ቀሺ ኪዳኑ የተባሉ መልካምና በእምነት ጽኑ ክርስትያኖች ዘንድ የተወለዱ ናቸው። ኣባ ኃደራማርያም ወልደሥላሴ (ዘማይዔላ ሸሓግነ ትግራይ) ከተባሉ ኣጎታቸው በስጦታ የተበረከተላቸውን አንድ የባሕረ ሓሳብ መጽሓፍ ግሩም አድርገው መርመረው በማጥናት የደረሱበት ድምዳሜ፡ በባሕረ-ሃሳብ ጥናት መስክ የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዳበረከቱ ያረጋግጣል። በባሕረ ሓሳብ ጥናት መስክ ለመመራመር የምትሹ ተመራማሪዎች፡ ምርምሩን ፈልጋችሁ አግኝታችሁ ማዬትና ማጥናት ትችላላችሁ። በትግርኛም በግእዝም በአማርኛም አዘጋጅተውት አልፈዋል ኣባዉ። ላበረከቱልን ግሩም ምርምር እጅጉኑ እናመሰግናቸዋለን ሰማእቱ ብፁዕ ገብረሚካኤልንና ኣባ ሳሙኤል አስገዶም ዘማኅበረ ሲታዉያንን። ጥናቱ ኣርእስቱ “የባሕረ-ሓሳብ ትምህርት - ዘደረሶ ብፁዕ ኣባ ገብረሚካኤል ሰማዕት - ዘከመ ኣስተራትዖ፡ ኣባ ሳሙኤል ኣስገዶም ዘማኅበረ ሲታዉያን] ይላል። መቺም ይህ የምርምር ውጤት መንዲዳ ወይ ሾላ ወይም ደብረገነት (ፐራዲዞ) ወይም ከረን ወይም ጎንደር ወይም ሓላይ ኣሊያም ካዛማሪ (ጣልያን) በሚገኙ የማኅበሩ ላይብረሪዎች ውስጥ አይጠፋም ይሆናል ብለን እንገምታለን። ምርምሩ እንዲህ ብሎ ይጀምራል፦

“የባሕረ-ሓሳብ ትምህርት - ዘደረሶ ብፁዕ ኣባ ገብረሚካኤል ሰማዕት - ዘከመ ኣስተራትዖ፡ ኣባ ሳሙኤል ኣስገዶም ዘማኅበረ ሲታዉያን]

፩ - ባሕረ-ሓሳብ ምን እንደሆነ፣
በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ። ንጽሕፍ ባሕረ ሓሳብ በእንተ ካህናት ከመ ኢይትመሰሉ ይቡሳን፣ እስመ ካህን በዢያእመረ ባሕረ ሓሳብ፡ ይመስል ፈለገ ዘአልቦ ማይ።
ባሕረ-ሓሳብ ማለት ቍጥር ያለው ዘመን ማለት ነው። “ባሕርን” ዘመን ሲል፣ ዕዝራ እስመ በመዳልው ደለወ ዓለመ፥ ወበመስፈርት ሰፈሮ ለባሕር ይላል። (፬ ዕዝራ ፬፡37) ሓሳብንም ቍጥር ሲል መጽሓፈ ነገሥት፣ ወኢትትሓሰቦሙ ወርቆሙ ይላል። (፬ ነገሥት ፳፪፡ 7)
፪- ጥንትታትና ኣዕዋዳት
፫ - ባሕረ ሓሳብን የደነገጉ
፬ - ዓውደ ኣበቅቴ
፭ - የበዓላት ሠርቅና ቀመር
፭ - አበቅቴ ጨረቃና፣ አበቅቴ ፀሓይ
፮ - በሠርቅ የሚተባበሩና፣ የሚከታተሉ አውራኅ
፰ - ዐጽፈ ኣውራኅና ዓመተ ወንጌላውያን
፱ - ቀመራትና ኣበቅቴ
፲ - ልደተ አበቅቴና፡ ዕለተ መጥቅዕ
፲፩ - አልቦ አበቅቴ
፲፪ - የአውራኅ ኅፀፅ
፲፫ - ያለፈውና የሚመጣው አበቅቴ
፲፬ - መጥቅዕ፣ ዕለተ-ምርያና ጥንትዮን
፲፭ - የዕለታት የበዓላትና የአጽዋማት ተውሳክ
፲፮ - የበዓላትና የአጽዋማት ታሕታይ/ ላዕላይ ቀመር
፲፯ - ታሕታይና ላዕላይ ቀመር የሚውሉበት ዓመታት
፲፰ - የሠርቀ ወርኅ ምርመራ
፲፱ - የኦሪት በዓላትና አጽዋማት
፳ - የኦሪት በዓላት ላዕላይ/ ታሕታይ ቀመር
፳፩ - የበዓላትና የአጽዋማት መመላለሻ
ትራፋተ ዓውድ
፳፪ - የፀሐይና የጨረቃ መፈጠር
፳፫ - “ጨረቃ ከፀሐይ በፊት ተፈጠረ” የሚል ይነቀፋል
፳፬ - ኅዋኅው የሚባሉ ከዋክብት
፳፭ - የዐረብ አውራኅ የዕለት ክፍፍል
፳፮ - የዕለት ክፍፍል ኣቈጣጠር
፳፯ - የጨረቃ መፈጠርና፣ ከፀሓይ ግንኙነቱ
፳፰ - ላይ የተነገው ባህል ምርመራ
፳፱ - የጨረቃ መንገድና ኅፀፅ
፴ - ቀመረ ዐረብ
፴፩ - ዓመተ ፀሓይና ዓመተ ጨረቃ




የሰማዕቱ የብፁዕ ገብረሚካኤል አኪሎ(1790 ዲቦ - 1855 ወሎ) በረከታቸው የኣባ ሳሙኤል ኣስገዶምም [ሓልሓለ 1915 - ኣሥመራ 2011] ጸሎታቸው አይለየን!