Page 1 of 1

ቀንጡ!

Posted: 14 Dec 2025, 22:20
by Horus
የቃል ትርጉም፤
ቀንጡ = ቀልጣፋ፣ ባለሙያ
አፈሉፍ = ወረተኘ፣ ወረኛ ፣ ወሬ አቀባባይ
ኧቡት = ክምር

ፈሊጥ፡
ጓራ ለቀባን (ጓሮ እርጉዝ ነው)
የሚያዳምጥ ሰው ስላለ በምስጢር ማውራት

እንዝንደ ጠብቅ (ጆሮህን ጠብቅ)
ስምህን (ዝናህን ጠብቅ)
እንዝን ያለቦ ጌ ማለት ጆሮ ያለው ቤት ፣ የዝነኞች ቤት ማለት ነው። መልካም ስም ያለው ቤተሰብ እንዝን ያላላቸው ሰዎች ናቸው ይባላል

አያገራ ቂጣ በምጣድ ያሺሉ
የማያጠግብ እንጀራ በምጣድ ያስታውቃል