_______________
ኢትዮጵያ ውስጥ ቁንጫ ከመግደል ሰውን መግደል ይቀላል
የብልጽግና መንግስት ማንን እያስተዳደረ እንዳለ ግራ ይገባል። ሀገሪቱን አንድ አድርጎ ማስተዳደር አልቻለም። የአማራ ክልል አብዛኛው የገጠር አከባቢዎች በፋኖ ነው የሚተዳደሩት። በኦሮሚያም አብዛኛው የገጠር አከባቢ መንግሥት ሸኔ ብሎ በሚጠራው አካል ስር ነው የሚገኘው። የትግራይ ክልል መንግስት አግጄዋለሁ ባለው ህውሃት ነው ሙሉ በሙሉ የሚተዳደረው። በቤንሻንጉል እና ሌሎች የኢትዮጵያ አከባቢዎችም ለአንድ እና ሁለት አመት ጋብ ብሎ የነበረው ጭፍጨፋ ድጋሚ ያገረሸበት ሁኔታ ነው ያለው። በዚህ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ እኮ ቁንጫ ከመግደል ሰው መግደል ይቀላል:: ቁንጫ ልግደል ብትል እንኳን እየዘለለች ስለምታስቸግርህ በቀላሉ ይዘሀት አትገድላትም። ነገርግን ሰውን መግደል: የሞት ዜና በሀገራችን የተለመደ ነገር ሆኗል። የሞት ዜናን ከመላመዳችን የተነሳ: ሰው ሞተ ሲባል ምንም አይመስለንም። ምናልባት በሶስት መቶ እና በሺዎች ሲሞቱ ትንሽ ትኩረት ከሰጠነው ነው። እና መንግስት ማንን ነው እያስተዳደረ ያለው?
አቶ አበበ አካሉ
መምህር እና ፖለቲከኛ