Page 1 of 1
የገንየ (በሰባት ቤት)፣ የጥፍር (በክስታኔ)
Posted: 06 Dec 2025, 01:54
by Horus
አንዲት ሴት ልጅ ከሰርጓ በፊት ለአንድ ወር ከወንድም ወደ ታች ያሉ ዘመዶቿ ተራ በተራ ሚዜዎቿ ጋር በየቤቱ እየተጋበዘች የሚሞሸሩበት ባህል ነው! ችሎታ ያለው ዘመዷ ሁሉ የገንየ የጥፍር ይደግስላታል!
Re: የገንየ (በሰባት ቤት)፣ የጥፍር (በክስታኔ)
Posted: 06 Dec 2025, 02:36
by Horus
የገንየ የሚለው ቃል ቀጥታ ትርጉሙን አላውቀውም ። በክስታኔዎች ዘንድ ድሮ አንዲት ልጅ በአሮጌ ጥፍሯ ወይም በስራ በተበላሸ ጥፍሯ ስለማታገባ የእጆቿ ጥፍሮች ሙሉ በሙሉ ተልጠው ከ2 ወይም 3 ወሮች በፊት ከዚያ ግዜ ጀምሮ ሥራ የሚባል ነገር በፍጹም የማትነካበትና የጥፍር ድግሶቿን በየዘመዷ ቤት ተራ በተራ ከሚዜዎቿ ጋር የምታምርበት ግዜ ነው ። ለዚህ ይህ ባህል የጥፍር የሚባለው ።
ጥፍር መቁረጥ በጎርደና ሴራ ከተከለከለ በጣም ቆይቷል ፣ ወደ 70 ወይም 75 አመት ይሆነዋል።
የጉራጌ ሴት ልጅ በትክክለኛው ባህል ሙሽራነቷ የሚጀርምረው የወንድ ቤት ሽማግሌ ልኮ እሺታ ከገኘበት ቀን ጀምሮ ነበር ።
ይህ የሽምግልና ወይም የፍጥምጥም ቀን በክስታኔ ቸግ (ዬቸግ ማይ) ይባላል ። ይህ ባህል አሁን በጣም ተስፋፍቷል ፤ እንዲያም አሁን ሰዉ ሁሉ ቸግ (ፍጥምጥም) ሰርግ (ሸባል) በአንድ ቀን አድርገውታል ፤ የድግስ ወጪን ለመቀነስ ነው ይባላል!
ቸግ የሚለው ቃልና ያማርኛ ጫጉላ የሚለው ቃል አንድ ናቸው ። ድሮ ጫጉላ የሙሽራነት ግዜን ሁሉ የሚያጠቃልል ቃል ነበር።
በክስታኔኛው ቸግ ግን አንዲት ሴት ልጅ ለጮኛ ተሰጥታ ሙሽራነቷ የሚጀምርበት ቀን ነው ።
ባማርኛ የጫጉላ ቤት የሚባለው የሙሽሮቹ ክፍል በክስታኔኛ ጎለት ይባላል ። ጎለት የሙሽራ ቤት ወይም ክፍል ማለት ነው። የሙሽራዋ መጎለቻ ማለት ነው ።
በቱባው ባህል አንዲት ሙሽራ ለ1 አመት በጎለት ውስጥ ኖራ በአመቱ ያ ክፍል ይፈርሳል (ለብቻው በሸምበቆ ውብ ሆኖ የሚሰራላት ክፍል ነው በወንዱ አባት ቤት ማለት ነው)
Re: የገንየ (በሰባት ቤት)፣ የጥፍር (በክስታኔ)
Posted: 06 Dec 2025, 02:50
by Horus
Re: የገንየ (በሰባት ቤት)፣ የጥፍር (በክስታኔ)
Posted: 06 Dec 2025, 02:55
by Horus