Page 1 of 1
ኢሱ ሞት አማረው- ክድጡ ወደ ማጡ! በሆረስ ጥያቄ መሰረት!
Posted: 03 Dec 2025, 01:19
by Axumezana
የኢሳያስ ነገር ሁሌም ወደ ግራ
እድሜውን ልክ የክፋት ጎተራ
እንድ ቀን እድሜ ቢጨመርለት
ተጨማሩ ሴራ ኢትዮጵያን ለሞጉዳት
ለግብፅ ተቀጥሮ አግሬን ሲያውክ
ድፍን 60 አመቱ ይሰግዳል በእንብርክክ
ከድጥ ወደ ማጡ እንዲሉ
ከኢራን ገጠመ ሌባው ለአመሉ
እስራኤልን ሊጎዳ ከኢራን አብሮ
ኢትዮጵያን ሊጎዳ ከግብፅ ተደምሮ
መንግስቱ ፈረሰች እርሱም ተፈንግሎ
ፅባኦት ተሰማ የኤርትራውያን እንጉርጉሮ
Re: ኢሱ ሞት አማረው- ክድጡ ወደ ማጡ! በሆረስ ጥያቄ መሰረት!
Posted: 03 Dec 2025, 02:34
by Horus
Axumezana wrote: ↑03 Dec 2025, 01:19
የኢሳያስ ነገር ሁሌም ወደ ግራ
እድሜውን ልክ የክፋት ጎተራ
እንድ ቀን እድሜ ቢጨመርለት
ተጨማሩ ሴራ ኢትዮጵያን ለሞጉዳት
ለግብፅ ተቀጥሮ አግሬን ሲያውክ
ድፍን 60 አመቱ ይሰግዳል በእንብርክክ
ከድጥ ወደ ማጡ እንዲሉ
ከኢራን ገጠመ ሌባው ለአመሉ
እስራኤልን ሊጎዳ ከኢራን አብሮ
ኢትዮጵያን ሊጎዳ ከግብፅ ተደምሮ
መንግስቱ ፈረሰች እርሱም ተፈንግሎ
ፅባኦት ተሰማ የኤርትራውያን እንጉርጉሮ
አክሱም
እንዲህ አድርጌ አነበብኩልህ ..
የኢሳያስ ነገር ሁሌም ወደ ግራ
እድሜ ልኩን ተንኮል የክፋት ጎተራ
የአንድ ቀን እድሜ ብንጨምርለት
መልሶ አሴረ ያው እንደ ለመዳት
ለግብጽ ተቀጥሮ እኛኑ ለመጉዳት
ሲሄድ በብርክኩ ስልሳ ዓመት ሆነው
ከድጥ ወደ ማጡ እንደ ተባባልነው
ከኢራን ገጠመ እንዳመሉ ሌባው
እስራኤልን መጉዳት ከኢራን አብሮ
ኢትዮጵያን ማጥቃት ተግብጥ ተደምሮ
መንግስቱም ይፈርሳል እሱም ተሽቀንጥሮ
ያኔ ቀኑ ሲደርስ ሰዓቱ ተቆጥሮ
ፅባኦት ይሰማል በኤርትራ እሮሮ
Re: ኢሱ ሞት አማረው- ክድጡ ወደ ማጡ! በሆረስ ጥያቄ መሰረት!
Posted: 03 Dec 2025, 08:45
by Axumezana
መልካም!
Re: ኢሱ ሞት አማረው- ክድጡ ወደ ማጡ! በሆረስ ጥያቄ መሰረት!
Posted: 03 Dec 2025, 13:52
by Abere
ዐይጥ ስለ ድንቢጥ ምስክር ተጠርቶ፤
ዶሮ ተጨምሮ የእህል ስጥ ተበልቶ፤
ድንቢጥ ነጻ ሁኖ ዶሮ ግን ተቀጥቶ፤
አይጥ ህልሟ ነበር ብታየው ተሳክቶ።
የዐይጥ ከድንቢጥ ጋር ፍቅር የያዛት፤
ዶሮ ድመት መስሏት በድነገት ታይቷት፤
ስለሆነ እንጅ ነው ለዶሮውም ቢሆን አላት አድናቆት፤
ዶሮ ባይጭራላት፤ ባያፈስላት፤ በየቀዳዳው ስር ባይበትናላት፤
መች ትቀምስ ነበር ከስጡ በረከት - ሰርቃ እና ደብቃ በየንቃቃት።
ዶሮ - ሻዕብያ ነው፤ ወያኔ አይጠ-መጎጥ፤
ኦሮሙማ ደግሞ ተከታይ ድንቢጥ፤
ከእህሉ ባለቤት ቶሎ ለማምለጥ - ከዶሮ እና ድንቢጥ የሚልመጠመጥ።
እውነት ነው እውነት ነው አሉ አምሳ አለቃ ገብሩ፤
ኢሳያስ አውሬ ነው ፍጹም ለነገሩ፤
ቢሆንም ቢሆንም - እነ ዳውድ ኢብሳ፤ እነ ሌንጮ ለታ፤ -ኢትዮጵያ ብትኖ እንደት ተሰወሩ፤
እረ እነ ወይን ሂሳብ አወራራጅ እነ ደብረጢዎ፤ እነ ስባሃት ነጋ - ባለ ማኒፌስቶዎች ለምን አልተጠሩ?
ሁሬሳ ተከፋይ - ኦሮሙማ ጥገቱ፤
አክሱምዒዛና- ማስታወል የነሳው ወይን እስከሞቱ፤
ንጹህነን ያላሉ - በወንጀል ጠምብተው ክፉ እየሸተቱ፤
የሞላ ሽንት ቤት - የአደባባይ ክርፋት ሁነው ባለበቱ።