Page 1 of 1

THE 12TH ETHIOPIAN NATIONAL QUALITY AWARD @ NATIONAL PALACE!

Posted: 30 Nov 2025, 17:31
by Horus

Re: THE 12TH ETHIOPIAN NATIONAL QUALITY AWARD @ NATIONAL PALACE!

Posted: 30 Nov 2025, 17:52
by Horus

Re: THE 12TH ETHIOPIAN NATIONAL QUALITY AWARD @ NATIONAL PALACE!

Posted: 30 Nov 2025, 22:28
by sesame
Horsey,

What quality are you talking about! Ethiopia is a lawless jungle. Everywhere, PP goons are bleeding the people by open highway robbery. Here are a few samples of this!


ለአማራ ልማት ማኅበር (አልማ)
ገመድ ተዘርግቶ የጫነ መኪና እንዲቆም ተደርጎ የአልማ ካልከፈልክ አታልፍም የሚባልበት ሁኔታ እናያለን ሶሮቃ ሳንጃ አብርሀጂራ በሌሎችም በዚህ መስመር ባሉ ከተሞች እያስከፈሉ ይገኛል በየጭነቱ በየጊዜው
ሌላው ሳንጃ ላይ አመታዊ የአልማ ካልከፈላችሁ አታልፉም በማለት እያሳልፉም ለምን ?
አልማ በግዳጂ ካልከፈልክ አታልፍም የሚባልበት ሂደት ለምንድን ነው ? በፍላጎት እንጂ በምን ስሌት ነው የምንገደድ Amhara Revenue Bureau እንዴት ያየዋል አልማስ???



ይህ ደግሞ ሳንጃ ከተማ ሶረቃ ከተማ አብራጅራ ከተማ ላይ ኬላ ዘርግተው የሚቆርጡት ደረሰኝ የቀይ መስቀል የአባልነት ገቢ መሰብሰቢያ የሚል ደረሰኝ ነው:: አባል መሆን በውዴታ ነው ምክንያቱም አላማው መጉዳት ሳይሆን መርዳት ስለሆነ ስለዚህ

Ethiopian Red Cross Society ከቆማችሁለት አላማ በተቃራኒ ህዝብ በስማችሁ እየተመዘበረ ስለሆነ አስፈላጊውን እርምጃ እንድትወስዱ እናሳስባለን::



ተመልከቱ ጋይንት ከተማ የተላለፈ መመሪያን ጥሰው ዛሬ ሲቀርጡ ውለዋል የሚገርመው የሚቀርጡበት ደረሰኝ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ይላል ምን አገናኘው በቆሎ የጫነ መኪና እና የይዞታ ካርታ?

ተሽከርካሪ ላይ የሚሰበሰቡ ቀረጦች ለምዝበራ ተገላጭ የሆኑ ናቸው የምንል በምክንያት ነው ጋይንት ከተማ ህ ሊያከብር ይገባል።

መንገዱ የዘራፊ የአጋች መፈንጫ አድርጎ ከተማ ቁጭ ብሎ ገንዘብ መሰብሰብ አይከብድም ?



ለትራፊክ ሞተር መግዢያ ብር በግድ አምጡ ጂማ ዞን ሰቃ ከተማ።

በጅማ ዞን ሰቃ ላይ ትራፊኮች መኪና እያስቆሙ የሞተር መግዣ እያሉ 1000 እያስቆረጡ ነዉ የለኝም በሞባይል ባንክ ስትላቸዉ ደግሞ አይቻልም ታርጋ እንፈታለን ይሉሐል በየትኛዉ የሕግ አግባብ ነዉ ሹፌር ለነሱ ሞተር የሚገዛዉ ?
መንግስት ይህንን ለከት የለሽ የፋይናንስ ህግን የጣሰ እንደ ሽፍታ በግድ ገንዘብ አምጡ የሚሉ አባሎቹን መስመር ሊያስይዝ ይገባል።

እንዴት ነው ለትራፊክ ሞተር መግዢያ ተሽከርካሪ በግዴታ ብር እንዲከፍል ካልከፈለ ታርጋ ተፈቶ ክስ እንዲከሰስ የሚደረገው ?

ይህ አይነት ሂደት የህግ አልባነት ምልክት ነው መንግስት ይህንን ድርጊት ሊያስቆም ይገባል።