Page 1 of 1

አንጋቻ በከፋ!

Posted: 12 Nov 2025, 17:45
by Horus
ዬኪት ቲነሶ!

የቃል ትርጉም፣
አንጋቻ = ድመት
ገቸ = ጅብ

የተረቱ ትርጉም፡
አንጋቻ በከፋ ዬኪት ቲነሶ = ድመት ካመረረ ሁለት ሰው አያነሳውም !!! ፋ ሲነበብ እንደ ከፋ ጠ/ግዛት ሳይሆን ክፉ በሚለው ጠንካራ ድምጹ ነው

በነገራችን ላይ የጎንቻ ተራራ ማለት የጅብ ተራራ ማለት ነው! ጎንቻ በጋፋትኛ ጅብ ማለት ነው




Re: አንጋቻ በከፋ!

Posted: 12 Nov 2025, 18:04
by Dama
Gonche is hayena in 7bet as well. I guess it would be the same in East Gurage dialects such as Welene, Gedebano/Gutazer, Ulbarag/Azernet, Silte and Zay.

Re: አንጋቻ በከፋ!

Posted: 12 Nov 2025, 18:46
by Horus
Dama wrote:
12 Nov 2025, 18:04
Gonche is hayena in 7bet as well. I guess it would be the same in East Gurage dialects such as Welene, Gedebano/Gutazer, Ulbarag/Azernet, Silte and Zay.
ትክክል ነው ። ጎንቸ ጅብ ማለት ነው ። ነ እና ወ ኔዛል አናባቢ ይባላሉ ። አንድ ቃል ለማለት ሲያስቸግር ወይም በጣም ሲያጥር ነ ወይም ወ ያስገቡበታል በተለምዶ ። ለምሳሌ የቃሉ ስር ገቸ ነው፣ አንዱ ጎሳ ነ ያስገባና ገንቸ ፣ ጎንቸ ይለዋል ። ሌላው ደሞ ገወቸ ፣ ጎወቸ ፣ ጎወንቸ ይለዋል ። ዲያሊክቶች ማለት ይህ ነው። በ7 ቤት ጎንቸ ጅብ ማለት እንደ ሆነ አውቃለሁ ። በምሁር አክሊል አንጋቻ ያው አንጋቻ ነው ድመት ማለት ነው።

ሆያ ሆዬ ስንዞር ስጦታ ለሰጠች ወንድ ልጅ ወለጂ ብለን ስንመርቅ ፣ ለከለከለች ደሞ አንጋቻ ውለጂ ብለን እንራገማለን ! ስለዚህ በጭራሽ የሆነ ነገር መስጠት አለባት ፣ እንዳትረገም :lol: :lol: :lol:

Re: አንጋቻ በከፋ!

Posted: 12 Nov 2025, 18:50
by Dama
Angacha in Chaha also is cat in English.