Page 1 of 1

የክስታኔ ገብና ባሊቆች ውግግት፡ አቲ ክርስቲያን፣ አቲ ሙስሊም

Posted: 05 Nov 2025, 23:53
by Horus
ኢትዮጵያ ማለት ይቺ ናት! ኢትዮጵያዊ ማለት እነዚህ ናቸው! እዚህ የሚደረገው የፍልስፍና ፣ ሕግ፣ ስነ ምግባርና የስርዓት ካልቸር ሙሉ መጽሃፍ ይወጣዋል
(1) ጡር - generational moral burden. example moral guilt
(2) ማል - socially & culturally forbidden behavior (አጢያት ፣ ግፍ ፣ ወንጀል እነዚህ በነፍስ አባትና በጎርደና ደነ (ዳኛ) የሚፈጸሙ ናቸው። ማል ግን በህሊና ዳኝነትና በሞራ ስነምግባር ወይም ግብረ ገብና (ግብረ ገብነት) የሚጠበቁ ባህሪያት ናቸው ። ታላቅን አለማክበር ማል ነው ፣ ወዳጅን መክዳት ማል ነው ። መዋሸት ማል ነው።
(3) ፎን - The logic, form, shape or manner of things . ዚ ቃይ ፎን ዬለን ከተባለ ይህ ነገር ሎጂክ የለውም ማለት ነው
(4) ለፌ - integrity የሰብ ልከው ለፌዋንን! የሰው መለኪያው ቃሉ ነው!
(5) ሴራ - law, rule, order, custom, mores ሕጋዊና ባህላዊ ድንጋጌዎች ፣
(6) ስኛት - a process, system or way of doing things according to sera. ማንኛውንም ነገር እንደ ስርዓቱ በትክክል መፈጸም!
(7) ቅጥ፣ ቅጥነት - equality, equity. ቅጥ (ቅጫ በ7 ቤት) አንዱ የሴራ የፍትህና ዳኝነት አይነት
(8) ጭቡ - wrongful act, deception
(9) አቅ፣ አቀተኘ - truth, truthfulness, honesty, authenticity
(10) ኬር፣ ኬርታ - holiness, wellness, goodness, peace - a universal concept that is only second to Godliness. ይህ ቃል በክስታኔኛ "እዝጌር" ወይም እግዚአብሄር በሚለው ቃል ውስጥ ያለ ስለ ሆነ (እዝ +ኬር) በጥንት ዘመን እግዚአብሄር የሚል ትግሩም ነበረው ማለት ነው። እዝ ኬር (እዝጌር) የኬር ኃይል ማለት ነው። ይህም ፈጣሪ ኃይል ማለት ነው። ስለሆነም በክስታኔች ኮስሞሎጂ እግዚአብሄር ከሚለው ቃል ቀጥሎ ያለው ኬር ነው።



Re: የክስታኔ ገብና ባሊቆች ውግግት፡ አቲ ክርስቲያን፣ አቲ ሙስሊም

Posted: 08 Nov 2025, 22:41
by Horus