ይድረስ ለተከበርከዉ የኤርትሪያ ሕዝብ!
Posted: 28 Oct 2025, 16:51
የተከበርከዉ የኤርትሪያ ሕዝብ ወይ፣ ይህን ምክር እንደ ወንድማዊ ምክር እንደምትሰማኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ዛሬ ላይ የተለየየ አገር ተብጅቶልን ብንለያይም፣ አብረን ብዙ ነገር ሆነናል፣ ብዙ ነገር አብረን ተቋድሰናል፣ አብረን ተምረናል፣ አብረን በልተን ጠጥተናል፣ አብረንም ወጉን አሳልፈናል፣ አብረን ገፈትም ቀምሰናል፣ እና ሌሎችም ጉዳዮች አብረን አሳልፈናል። ለዚህ ነዉ ወንድማዊ ምክር ያልኩት፣ እንዲሁ ከመሬት ተነስቼ አይደለም።
አንድ ነገር ግን ለስገነዝብህ ወደድኩኝ፤ እስከ መቼ ነዉ ከዉስጥህ ወጥቶ የአንተ የወደ ፊት ዕጣ ፋንታ ሳይሆን የላኪዉን ጉዳይ ለመስፈፀም አንተን አታሎ፣ በዉሸት ጋርዶብህ፣ የሌላዉንም ያለዉንም አስመስሎ እየሸጠልህ ያምትኖረዉ? መቼ ነዉ በቃኝ የምትለዉ? አሁንም የልበቃ ይመስለሃል? ወደህ አገር እሆናለሁ ብለህ ከኢትዮጵያ ራስህን መለየት ከፈልግክ ያ የአንተ ምርጫ ነዉ፣ ማንም አስገድዶህ የግድ ከኢትዮጵያ ጋር ኑር የምልህ መኖር የለበተም፣ የምል እምነት አለኝ። ጥያቄ ግን ሌላ አገር መሰርትክ እንጂ አሁን በወጉ ነፃ ነህ ወይ? ነፃንተ ፍላጋ አልነበረም እንዴ ከኢትዮጵያ መለየት አለብኝ ብለህ (ብሎህ አታሎህ) የሄድከዉ? እዉን አሁን ነፃነት ኤርትሪያ ዉስጥ አለን? መንግስት የለህም፣ ሕገ-መንግስት የለህም፣ ምርጫ አይካሄድም፣ ትምህርት እንደልብ የምከታተል ወጣት የለህም። ነፃ የተባለዉ ኤርትሪያ አሁን ላይ እኮ ወደ ምድረበዳነት እየተለወጠ ነዉ፣ አይደለም እንዴ? ይህ ከአንተ በላይ እኔን አሳስቦኝ ሳይሆን፣ እንዴት እንደዚህ ትሞኛለህ የምል ጥያቄ ማንሳት ፈልጌ ነዉ? አረ ቆም ብለህ አስብ እንጂ ወገን!
ኤርትርያነትን ፈልገህ ከሄድክ ያ የራስህ ምርጫ ነዉ። አንድ ነገር ግን ልጠይቅህ እፈልጋለሁ። ለራስህ ነፃነትን ፈልገህ ከኢትዮጵያ ስትለይ፣ እንዴት ብሆን ነዉ፣ ወይም ብትጨክን ነዉ የዚህን መጠነ ሰፊ ሕዝብ ጉሮሮ ዘግቼበት እሄዳለሁ ብለህ የምትወስንባት፣ ኢትዮጵያ ላይ? የገዘ ወንደም ሕዝብ አይደለም እንዴ፣ የተለያየ አገር ይኑራችዉ ብንባልም እኮ ብዙ ነገር እንጋራለን፣ ባህልን፣ እምነትን፣ ደምን፣ ታርክን እና ሌሎችም የምያቆራኙን ብዙ ነገሮች አሉን እኮ፣ እንዴት እንደዚህ በገዛ ወገንህ ላይ ትጨክናለህ? በገዛ ወገን ብቻ ሳይሆን፣ በማንኛዉም የሰዉ ልጅ ላይ ግሮሮዉን ዘግቼበት እለየወለዉ ማለት፣ ብልግና ብቻ ሳይሆን፣ አረመኔነትም ጭምር ነዉ፤ አይደለም እንዴ? አንተ እንደዚህ መጨከን ፈልገህ ሳይሆን፣ ከራስህ ወጥቶ ለባዳ ጉዳይ አስፈፃሚ የሆኑት በተረኩልህ የማያልቅ ትርክት ና ደባ ተነሳስተህ የፈፀምከዉ ታሪካዊ ስህተት ይመስለኛል። ያኔ ያሳሰቱህ አሁንም የጥፋት መንገድ እየመረጡልህ ነዉ፣ በጊዜ ከልነቀህበት። ለዚህ ነዉ ይህን ወንድማዊ ምክር መለገስ የፈልግኩት። መቀበል ና አለመቀበል ያአንተ ፋንታ መሆኑን እገነዘባለሁ።
ጥፋቱ በቃኝ ከአለልክ፣ ትልቅ የጥፋት ድግስ እየተደገሰልህ ነዉ፣ ከወገንህ ና ወንድም የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አሁንም መልሶ ደም ልያቃቡህ ዝግጅት ላይ ናቸዉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ በተደጋጋሚ እንደገለፀልህ፣ አንተን ለማጥፋት ወይም ለማዳከም ፍላጎት የለዉም፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ አብረን እንደግ ነበር ያለዉ። ለባዳ ተላላኪ የሆነዉ ና አንተን አገር ያሳጥህ ቡድን አሁንም አልሰማም ብሎ አሻፈረኝ አለ። ዳም አቃብቼ ተላላኪነቴን አሳካለሁ ብሎ አሁንም ወስኖዋል።
ኢትዮጵያ አንዲት ጥያቄ ነዉ ያለት፤ ጉሮሮዬ ተዘግቶብኝ አልኖርም፣ አልዘልቅም ነዉ ያለችዉ፤ ታዲያ የኤርትሪያ ሕዝብ የባሕር በርን ለኢትዮጵያ ከፍቶ ብሰጠዉ ምን ይጎልበታል? በጠኔ ልጨርሰው ወይም ደግሞ እንደፈለግኩኝ ጉሮሮዉን አንቄ ከላይ ሆኜ እዘዉራዋለሁ፣ ለላኪያ ጉዳይ ማስፈፀሚያ አደርገዋለሁ ብሎ ካለሰብ በስተቀር። ይህን ደግሞ ኩሩዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ጊዜም እንደማይቀበል አንተም እንደ ወንድም ሕዝብ የጠፋህ አይመስለኝም። ይህ የጥፋት መንገድ ነዉ፣ ራሳችንን ከዚህ የጥፋት መንገድ መቆጠብ ይገበናል፣ ለሁለታችንም አዋጪ መንገድ መፈለጉ ነዉ ያምያዋጣን የምል ነዉ የዛሬው ወንድማዊ ምክሬ። ጆሮ ዳባ ልበስ እንደማትለኝ ተስፋ አደርጋለሁ፣ አደጋዉ አስፈሪ ይመስለኛል፣ እኔን አስፈርቶኛል። ተላላኪዎችን ከመሓልህ አስወግደህ፣ የተገረጠብህን አደጋ ለሁላችንም ደንነት ስትል አስቆመዉ የምል ልባዊ ጥሬዬንም አስተላልፋለሁ።
ሰላም፣ ለኤርትሪያ ሕዝብ፣ ሰላም ለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ሰላም ለአፍሪካ ቀንድ ሕዝቦች ሁሉ፣ ሰላም ለአለም ሕዝብ ሁሉ ይሁን! በጋራ ሆነን ለሰላም ዘብ እንቁም፣ አደራህን ብዬ መልዕክቴን እቋጫለሁ፣ እንደማታሰፍረኝ ተስፋ አደርጋለሁ!
ከኢትዮጵያዊ ወንድምህ !