ልማድ የያዘው እምነት አለ።
የሰው ልጅ የሰዎች ማህበረሰብ ነጻ ምርጫ አለው የሚለው ስሁት እመነት ነው።
የሰው ልጅ አለም በሚባለው ውስብስብ የገደብና የውሱንነት ጫካ ውስጥ ያለምርጫው የተወረወረ ፍጡር ነው።
የሰው ልጅ የሰዎች ማህበረሰብ ከገደብና ከውሱንነት ነጻ የሆነ ምርጫም ሆነ ነጻነት የለውም ሊኖረው አይችልም ።
ሌላው ቀርቶ ሰላም ከሌለ ልማት የለም የሚባለው ያልታኘከ አባባል እራሱ ስህተት ነው።
አንድ ሰው አንድ የሰዎች ማህበረሰብ አንጻራዊ ሰላም የሚያገኘው ነጻ ምርጫና ከገድብ ውጭ ነጻ ምርጫ የለም የሚለውን የተፈጥሮ ሕግ ሲቀበል ነው።
ይህን መሰል የእምነትና ህሳቤ ደረጃ ያልደረሰ ሕዝብ ሰላም ሊኖረው አይችልም።
ሰላም የሌለው ሕዝብ ደሞ የሚኖረው በሁከት፣ በአመጽ በጦርነት ውስጥ ነው ።
በጦርነት ውስጥ የሚኖር ፣ ጦርነት ኖርማል በሆነበት አለም ደሞ ኑሮውን ፣ ልማቱን እድገቱን በጦርነት መሃል ፣ ከጦርነት ጋር አያይዞ ማከናወን አለበት ።
ስለዚህ አቢይ አህመድ እየተዋጋን እናለማለን እያለማን እንዋጋለን ማለቱ እጅግ እጅግ ትክክለኛ ግንዛቤ ነው።
ኢትዮጵያን በአመጽና ጦርነት ወጥረን ከዝመናና ልማንት እንገታታለን ብለው የሚለፉትን ግብጽ፣ ኤርትራ፣ ወያኔ፣ ፋኖና ሸኔን ማሳፈር የሚቻለው ይህን በመሰለ እስትራተጂና ፍልስፍና ነው ።
ጦርነትና አመጽ የኢትዮጵያ ኖርማል ለ100 አመት የኖረ ወደፊትም የሚቀጥል እውነታ ስለሆነ ሕዝባችን ባንድ እጁ እየተዋጋ በሌላ እጁ ልማቱን ማጧጧፍ ነው ያለበት!