Page 1 of 1

ግምታዊ መለኮታዊ ጎህ በፍጥረት በር፥ ቁጥር 5 (ጥያቄ ቁጥር 4)

Posted: 19 Oct 2025, 21:29
by Naga Tuma
መለኮት ስለመኖሩ እና ኣለመኖሩ ክርክር ብያስጀምር ምን ለማስተማር ነዉ?

Re: ግምታዊ መለኮታዊ ጎህ በፍጥረት በር፥ ቁጥር 5 (ጥያቄ ቁጥር 4)

Posted: 28 Mar 2026, 16:17
by Naga Tuma
ከብዙ ዓመታት በፊት ስለ ምስራቅ ኣፍርካ ታሪክ ኣንብቤ ያስተዋልኩኝ የአከባቢዉ ሃይማኖቶች መጽሓፎች ዉስጥ ተጽፎ የምያስተምሩት የስደት ታሪክ ዉስጥ ዘበት መኖሩን ነበር።

ታሪኩ በኣጭሩ የሚለዉ ከስደት በኋላ ፕሮፌት ሙሴ የተባለዉ ከስደት በፊት አክናተን ተብሎ ይታወቅ የነበረ ታላቅ ፈረዖ ነዉ።

የስሙ ትርጉምም አሙን ኢዝ ሳቲስፋይድ ማለት ነዉ ተብሎ ተጽፏል።

ያ ታላቅ ፈረዖ በምድር ላይ ለመጀመርያ ግዜ ኣንድ እግዝኣብሔር ማለትን ማስተማር የጀመረ መሆኑ ታሪክም ተጽፏል።

ሌሞ መቃ ዽባ ማለት ስሞቹ መቶ የሆኑ ኣንድ ሌሞ ማለት ነዉ።

ሌሞ ትክክለኛ ትርጉሙ ይሄ ነዉ ማለት ያስቸግረኛል። ስለዚህ ትርጉሙን ለምያዉቁት ልተዉ።

ከሃያ ዓመታት በፊት ታሪክ ኣጥንቼ ያስተዋልኩ በዚህ ግዜ ደግሞ ስለ መለኮታዊ አሰራር ተዓምራት የማስተዉል ሰዉ ነኝ እያልኩኝ ነዉ።

ሌሞ መቃ ዽባ ስለተባለዉ ሁሉንም የምያግባባ ስም ስፈልግ እና ቢፈለግ ብዬ ስመክር ቆየሁ።

በቅርቡ ከስደት በፊት ስሙ አሙን ኢዝ ሳቲስፋይድ ከተባለ ለስደት የተዳረገዉ ታላቅ ፈረዖ የአሙን ፕሮፌት ነበረ ማለት ነዉ ኣስብሎኛል።

ስለዚህ እግዝኣብሔር፣ እግዝያር፣ መለኮት፣ ዋቀ፣ ጦሳ፣ እና ሌሎች ስሞችን ፕሮፌት የነበረዉ እና ስሙ አሙን ኢዝ ሳቲስፋይድ የተባለ ከሆነ አሙን ማለት ትክክለኛ ስሙ ነበረ ማለት ይቻላል ኣስብሎኛል።

ይህ መለኮታዊ ጎህ ምናልባት አሙን ኢዝ ሳቲስፋይድ ከተባለ በኋላ የአሙን ፕሮፌት ለስደት መዳረግ የኢትዮጵያ አበሳ ሆኖ ኖሮ በመለኮታዊ አሰራር ተዓምራት በዚህ ዘመን አሙን ጎሁን የፈነጠቀ ይሆን?

ይህን ከእኔ በላይ ስለ ሃይማኖት እናዉቃለን የምትሉ ማወቅ ኣለባችሁ።

እኔ ዛሬ ያስተዋልኩኝን ኣስተዉዬ ወይም ያስተዋልኩ መስሎኝ የሚከተለዉን ኣስብሎኛል።

አሙን ህያዉ ነዉ።

መጋቢት ቀን 19፣ 2018፣ ዓም

Re: ግምታዊ መለኮታዊ ጎህ በፍጥረት በር፥ ቁጥር 5 (ጥያቄ ቁጥር 4)

Posted: 31 Mar 2026, 14:18
by Naga Tuma
ጤና ይስጥልን፣ እንደምን ናችሁ?
ከህያዉ ተላክን፣ ልንጠይቃችሁ።

የአሙን ፕሮፌት እና የፕሮፌት ማኒ መንፈሶች

መጋቢት ቀን 12፣ 2018፣ ዓም