አዳብና በአዲስ አበባ! ክስታኔን ስምኛ ሶዶን አገርኛ!
Posted: 16 Oct 2025, 11:15
ክስቶ ከእምዬ ምኒልክ ጎን ሃ ብሎ አዲስ አበባ ጫካ ውስጥ ጅብ እየበላው ይቺን ከተማ የገነባ ሕዝብ ነው! ዛሬ ምኒልክ እራሱ ላይ ዉፋ ቅቤ በሻሽ አስረውለት ቁጭ ብሎ ይህን ጨዋታ ቢያይ ምንኛ ይደሰት ነበር ። ምነው ብቻዬን ተዋችሁኝ ከተማውን ቤት ስሩበት ዛፍ ትክሉበት እንጂ ያላቸው ክስታኔዎችን ነበር! በኢትዮጵያ ባህር ዛፍን ከአዲስ አበባ ውጭ በመትከል የመጅመሪያው ሕዝብ ክስታኔ ነው! ጥይት መስራትን ከጣሊያን ተምሮ የኢትዮጵያ ጥይት ፋብሪካን የቆረቆረ ይህ ሕዝብ ነው! እድርን እቁብን ለኢትዮጵያ ያስተማረ ይህ ሕዝብ ነው! የንግድ ሙያን ከአረብ አውጥቶ መርካቶን ያቆረቆረ ይህ ሕዝብ ነው! ያለ ክስታኔ አዲስ አበባ ጎደሎ ነች!! አይደለም በምኒልክ በኃይለ ስላሴ ዘመን በራሱ ሕዝብ መዋጮ ከአለም ገና እስከ ወላይታ ሶዶ ድረስ በታላቁ አዋሽ ላይ ድልድይ ሰርቶ መንገድ የሰራ ይህ ሕዝብ ነው!