Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6755
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

የምያስገርም የሰዉ ልጅ ቅዠት በኢትዮጵያ፥ ዮሓንስ ለታ፣ ፕሮፌሰር መረራ ጉድና፣ ቀመር ዩሱፍ፣ እና ታደለ ገመቹ የኣንድ ቋንቋ ጎሳ ናቸዉ?

Post by Naga Tuma » 14 Oct 2025, 00:29

በመጀመርያ ሁላቸዉም የሰዉ ልጆች ናቸዉ።

በሁለተኛ ደረጃ ሁላቸዉም ኢትዮጵያ ዉስጥ ተወልደዉ ያደጉ ዜጎች ናቸዉ።

በሶስተኛ ደረጃ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ባልሆንም ኦሮምኛ የሁላቸዉም አፍ መፍቻ ቋንቋቸዉ ነዉ።

በአረተኛ ደረጃ ምናልባትም አረቱም በተለያዩ ሃይማኖቶች ታቅፈዉ ያደጉ ሊሆን ይችላል። እነዚህም የፕሮቴስታንት ክርስትና፣ የኦርቶዶክስ ክርስትና፣ ሀመቺሳ፣ እና እስልምና ናቸዉ የሚል ግምት ኣለኝ።

በአምስተኛ ደረጃ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ባልሆንም ሁላቸዉም አማርኛ እና እንግሊዘኛን ተምረዉ በነዚህ ሁለቱም ቋንቋዎች ከሌሎች ቋንቋዎቹን ከሚችሉ ሰዎች ጋር በተለያየ ደረጃ መግባባት የሚችሉ ናቸዉ።

በስድስተኛ ደረጃ የኦሮምኛ ግንድ ቦረና ዉስጥ የኖሩት የኢትዮጵያ ጎሳ ቢሆንም በእኔ ስሌት የእነዚህ አረት የኢትዮጵያ ዜጎች የቦረናነት የጎሳ ክፋይ ከሃምሳ ከመቶ በታች ቢሆን እንጂ ከዛ በላይ የሚሆን ኣይመስለኝም።

ትክክለኛዉን ሁላቸዉም ይህን ያህል ነዉ ብለዉ ማሳወቅ ይችላሉ።

ይህ በጣም ቀላል የሆነ ምሳሌያዊ ጥናት ሌሎች ሳይሆኑ እነዚህ ግለሰቦች ብቻ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን የአከባቢዎችን ፍትሓዊ አስተዳደርን እንዲህ ይሁን የማለት ሀሳብን ማመንጨት ይችላሉ።

ይህን ማድረግ የሚችሉት የተቆጠሩም ሆነ ያልተቆጠሩ የራሳቸዉን ጎሳዎች በሃገር ዉስጥ ያላቸዉን ስብጥርን ሙሉ በሙሉ ማወቅ ከቻሉ ነዉ።

ሁላቸዉም ይህን መሠረታዊ ጥናት ካደረጉ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሉዓላዊነት ያላት ሃገር ዉስጥ በየአከባቢያቸዉ እራሳቸዉን ማስተዳደር ከቻሉ ምን ያንሰዋል ማለት ይችሉ ይሆናል።