አዲስ አበባ ያለው ኦህዲድ ሰአት ቆጣሪ አስቀምጦ ሞቱን የሚጠብቅ ቡድን ሆኗል። በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ ከመንግስት እጅ መውጣቱን የሚያመላክቱ ብዙ ምልክቶች አሉ።
Posted: 12 Oct 2025, 08:22
በጦር ሜዳ ያጣውን ድል በዲፕሎማሲው መስክ ለማሳካት!
By Tigray Analytics FaceBook page
የነገሮች መቋጫ ፖለቲካና ዲፕሎማሲ ነው። ጦርነት በዲፕሎማሲም ጭምር ማሸነፍ ይጠይቃል። ነገሮችን በድርድር መፍታት ሲያቅት ፖለቲካውን ገፋ ለማድረግ ውሱን ጦርነት (limited) ማካሄድም የተለመደ ነው። የዚሁ ተቃራኒ ጠቅላላ ጦርነት ይባላል። ይህ አንድን ወገን በሃይል በማንበርከክ አላማህን ማስፈጸም ነው። ኦህዲድ/ብልጽግና በትግራይ የተከተለው ጦርነት ጠቅላላ ጦርነት ይባላል። ይህ ማለት የትግራይን ታጋዮች፤ ህዝብና ኢኮኖሚ በማውደም ቀሪውን በሃይል በመቆጣጠር ማስገበር ነው። ኦህዲድ/ብልጽግና በኤርትራ እየተከተለው ያለው አስመራን ጋዛ የማድረግ ወታደራዊ እቅድ የጠቅላላ ጦርነት እሳቤ ነው። የኢትዮጵያ ገዢዎች በኤርትራ ለዘመናት “ባህር እንጂ ህዝቡን አንፈልገውም” የሚለው መፈክር የጠቅላላ ጦርነት ባህርይ ነበረው። ዲፕሎማሲ በማንኛውም ሁኔታ የሚካሄድ ነው። ወታደሮች ጦር ሜዳ ላይ በሻሞላ እየተመሻለቁ ባለበት ወቅትም ቢሆን ዲፕሎማቶች ወይን ይዘው ቢወያዩ ሊገርመን አይገባም። ሁሉም የራሱ ህግ አለው። ዲፕሎማሲ በጦርነት ወቅትም ቢሆን አይቋረጥም። ይህ እውነታ እንዳለ ሆኖ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ የፖለቲካ ዲያሎግ፤ ድርድር የሚባል የተለመደ አይደለም። የፕሪቶርያ ስምምነት አደጋ የገተጠመውን በዚህ ምክንያት ነው። በኢትዮጵያ ከተቻለ ማሸነፍ ብቻ ነው። ስታሸንፍ ጠቅላይ ትሆናለህ።
ኦህዲድ እጅ የቀረችው የሉአላዊነት ሰርቲፌኬት በመሆኗ ለተመድ ደብዳቤ በሳምንት ልዩነት ሁለት ደብዳቤም መፃፍ ይችላል። የሆነውም ይህ ነው። አፍሪካ ህብረትም አዲስ አበባ በመሆኑ ከተፅእኖ ነፃ ነው ማለት አይቻልም። በዲፕሎማሲው ዘርፍ ያለው ብልጫም ከዚህ የሚመነጭ ነው። ይህም ሆኖ የዘመኑ ዲፕሎማሲ ለሁሉም እድል ሰጥቷል። መንግስት መክሰስ የሚቻልበት ዘመን ላይ ነን። ሉአላዊነት የገዳዮች ሽፋን መሆኑ አብቅቷል። ወደ ገደለው ስንገባ የሰሞኑ የኦህዲድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተመድ የፃፈው ደብዳቤ አንድምታው ምንድነው ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል።
ሲጀምር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተመድ የፃፈው ደብዳቤ ከቁም ነገሩ አነጋጋሪነቱ በልጧል። ደብዳቤው በጥድፊያ የተፃፈ ስለመሆኑ ግልፅ ነው። እምብዛም የተመከረበት አይመስልም። በአንድ ሳምንት ልዩነት ሁለት ደብዳቤዎች መፃፍ ደግሞ አስገራሚ ነው። የአሁኑ ዋነኛው ጥያቄ መንግስት ይህን ደብዳቤ ለመፃፍ ያስገደደው ሁኔታ ምንድነው? የሚል ነው። ይህን ጥያቄ ለመመለስ የግድ አሁን ካለው የፖለቲካ፤ የፀጥታና፤ ወታደራዊ ሁኔታ መነሳት ግድ ይለናል።
በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ ከመንግስት እጅ መውጣቱን የሚያመላክቱ ብዙ ምልክቶች አሉ። በአማራ ክልል ከሰባት ሚሊዮን ተማሪዎች አራት ሚሊዮን ከትምህርት ውጭ ናቸው። ሰማንያ እጅ የአማራ ክልል በፋኖ ስር ይገኛል። በወሎ ወይም ምስራቅ አማራ ያለው ወታደራዊ ሁኔታ የፋኖ ሃይሎች የበላይነት ያገኙበት ሁኔታ ተፈጥሯል። በወልድያ አካባቢ የሆነው ነገር የታሪክ መታጠፊያ እንደሆነ ይገመታል። የአብይ ወታደሮች በሁሉም አካባቢ እየተቀጠቀጡ አቅማቸው ወደ ቡቱቶ እየተቀየረ ነው። ወታደሩ በቅርብ ሊፈርስ እንደሚችል የብዙዎች ግምት ነው። አዲስ አበባ ያለው ኦህዲድ ሰአት ቆጣሪ አስቀምጦ ሞቱን የሚጠብቅ ቡድን ሆኗል። በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ መንግስት የለም የሚያሰኝ ነው።
የትግራይ ሁኔታም ሌላው አሳሳቢ ሁኔታ ነው። የደብዳቤው ትርጉም ኦህዲድ ከፕሪቶርያ ስምምነት ማፈግፈጉን ያሳያል። የሰላም ተዋዋይ ህወሃትን እውቅና እንደማይሰጠው በደብዳቤው ተመላክቷል። ወደ ተመድ ሲጽፍ ህወሓት ማለት አቅቶት የህወሓት አንጃ ብሎ መፃፍ አስገራሚ ነው። አንጃ የሚለው ለመንደር ፖለቲካ ፍጆታ ብቻ መስሎን ተሳስተን ነበር። የፌዴራል ተቋማት በመጠቀም የሰላም ስምምነቱን በመጣስ ህወሓትን እውቅና ቢነሳውም በትግራይ ያለው ህዝባዊነት ሊነጥቀው አይችልም። በመሆኑም ትግራይ የራሷ የፖለቲካ ተቋማት ማጠናከር አለባት። የፖለቲካ ፓርቲዎች መተዳደርያ ህግም ማውጣት ግድ ይላታል። ትግራይ የአብርሃም በግ መሆን መፍቀድ የለባትም።
ሌላው በደብዳቤው የተጠቀሰው የጽምዶ ፖለቲካ ነው። ጽምዶ በመሰረቱ የህዝብ ለህዝብ ዕርቅና ሰላም መፍጠር ነው። ይህም የጋራ ድንበሩ የመድፍ ድምጽ የሚሰማበት ሳይሆን የሰርግ እምብልታ ድምጽ የሚሰማበት መሆን አለበት። ኦህዲድ በትግራይና በኤርትራ ህዝቦች ላይ የጋራ የህልውና ስጋት የፈጠረ በመሆኑ በጋር መመከት ተገቢ ኣይደለም የሚል ሰው ካለ ለማዳመጥ መዘጋጀት ነው። በየተራ በጅብ ለመበላት ፍቅደኛ መሆን የለባቸውም። የአብይ አህመድ መንግስት በኤርትራ፤ በትግራይና በአማራ ህዝቦች ላይ የህልውና አደጋ ስለፈጠረ የፖለቲካና ወታደራዊ ትብብር ማድረጋቸው መዘግየቱ ካልሆነ በስተቀር ተገቢ ነው። የጄኖሳይድ መንግስት በጋራ መታገል ተገቢ ነው። ይህ ሲባል ልዩነቶች የሉም ማለት ሳይሆን ቢኖሩም መተባበርን የሚያደናቅፍ አይደሉም።
የተላከው ደብዳቤ የወልድያ የፋኖ ዘመቻን ድል ተከትሎ መሆኑ ግልጽ ነው። መስከረም 25 አንድ ደብዳቤ የተላከ ስለመሆኑ ይጠቁማል። እዚህ ላይ ሁለት መላምት ማስቀመጥ ይቻላል። በአንድ በኩል ያለው የሃይል አሰላለፍ ስጋት የፈጠረበት መሆኑን ያሳያል። እውነትም አሁን ያለው ኦህዲድ እንደሚለው እየተባበሩ ከሆነ አብይ ሻንጣውን ሸክፎ ሊሆን እንደሚችል ነው። ይህ መንግስት በአንድ ሳምንት ልዩነት ሁለት ደብዳቤ ለተመድ የፃፈበት ምክንያት የደም ብዛት ስለበረታበት ይሆናል። ይህ አንዱ ሲሆን ሌላው መላምት ደግሞ አብይ አህመድ በራሱ አንደበት እንደሚነግረን የወረራ ዝግጅት አጠናቆ ትግራይንና ኤርትራን ለመውረር የዲፕሎማሲ ንጣፍ እያነጠፈ ሊሆን ይችላል። አብይ አይጥ ለመያዝ ሰላማዊ ለመምሰል እንደምታነከስ ድመት አለም አቀፍ ማህበረሰብ በተጠቃሁ መንፈስ ለመቅረብ እየሞከረ ነው። አገር ቤት “ከግድብ ወደ ወደብ” እያለ ሲፎክር በውጭ ደግሞ “ከደሙ ንፁህ ነኝ” እያለን ነው።
በዚህ ፀሃፊ እይታ የአሁኑ የአብይ (ኦህዲድ) ብልጽግና በኤርትራና በትግራይ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ የማድረግ አቅም የለውም የሚል ግምት አለው። አሁን ያለው ስጋት የአብይ ጦር ተቦጫጭቆ በያለበት እንዳይፈርስ ነው። አሁን ያለው ምልክት ይህ ነው። በነሃሴ ወር መጨረሻ መከላከያ ራሱ ያደረገው ግምገማ ወታደሩ በጦርነት የተሰላቸ መሆኑን፤ የመዋጋት ፍላጎት እንደሌለው፤ በዘር የተቧደነ ስለመሆኑ፤ ኩብለላ ባህል እየሆነ መሄዱን፤ የበላይ አለቆች ተቀባይነት እንደሌላቸው፤ ሰራዊቱ በተለይም አዲስ ሰልጣኝ ከአንድ ብሄር መሆኑን በዝርዝር ገምግመዋል። ይህ የሚያሳየው አብይ አህመድ የሚጮኸው በባዶ እንደሆነ ነው።
ከዚህ አንፃር የወልድያው የፋኖ ድል አስደንጋጭ ነገር አለበት። ፋኖ አንድ ክፍለ ጦር ፊት ለፊት ገጥሞ ሲያሸንፍ የመጀመሪያው ሳይሆን አይቀርም። በጥሩ ወታደራዊ እቅድ የተመራ ነው። መንግስት ይህን ከፋኖ አልጠበቀም። በዚሁ ድርጊት በመደናገጡ፤ ድሉን ለትግራይና ለኤርትራ ለመስጠት እንደወሰነ ያሳያል። የዚሁ ሽንፈትም በአለም አቀፍ ደረጃ ለተመድ “ተባበሩብኝ” የሚል የተለመደ ነጠላ ዜማ አሰራጭቷል።
የኦህዲድ/ብልጽግና የጫጉላ ዘመን አብቅቶል። የአብይ አህመድ የቀረው አማራጭ የሰላም ጥሪ ተቀብሎ ስልጣን ማስረክብ ብቻ ነው። የጦር ሜዳው ሁኔታ የተቀየረ ስለሆነ ከእንግዲህ የሚደረጉ ጦሩነቶች የፖለቲካ ትርጉም አይኖራቸውም። የአብይ አሁናዊ ጥረት በወታደራዊና በፖለቲካ መስክ ያጣውን በዲፕሎማሲ የማሳካት ሙኮራ ነው። ዲፕሎማሲ ደግሞ የሁለቱም ውጤት ነው። ሲያልቅ አያምርም እንዲሉ!

Please wait, video is loading...