Page 1 of 1

✈️ ✈ ለማመን የሚያስቸግር አስደናቂ እውነተኛ ታሪክ ✈ ✈️

Posted: 07 Oct 2025, 08:24
by Fiyameta
በኤርትራ ምድር በተፈጸመ አንድ አስገራሚ ታሪክ ዙሪያ ነው የምንቆየው። ይህንን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንተርኔት ሳነበው ማመን ከብዶኝ ነበር። ምክንያቱም 18 ሰዎች እንዲያ ዓይነቱን በጀብድ የተመላ ኦፕሬሽን ይፈጽማሉ የሚል ሐሳብ ሊመጣልኝ ስላልቻለ ነው። የደርግ መንግሥት ባለስልጣን የነበሩት አቶ ገስጥ ተጫነ "የቀድሞው ጦር" በሚል ርእስ በጻፉት ዳጎስ ያለ መጽሐፍ ውስጥ ታሪኩን ከዳሰሱት በኋላ ግን እውነት መሆኑን አምኜ ተቀብዬዋለሁ። እናም ያንን ጀብድ በራሴ አቀራረብ ልተርክላችሁ።
-----



የህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ሻዕቢያ) ታጋዮች በትጥቅ ትግሉ ዘመን ከሰማይ ቦምብ እያዘነበ በእንቅስቃሴአቸው ላይ ችግር የፈጠረባቸውን የኢትዮጵያ አየር ሃይል አጥቅተው ከችግሩ ለመገላገል ወሰኑ። በዚህም መሠረት በአስመራ ከተማ ዳር በሚገኘው ሰምበል የተሰኘ የአየር ሃይል ሜዳ ላይ የሚያርፉትን አውሮፕላኖች የሚያወድም ቡድን ያዘጋጁ ጀመር።

ለኦፕሬሽኑ የተመረጡት 16 ታጋዮች ናቸው (ሁለት ታጋዮች በኋላ ላይ ከአስመራ ከተማ ተቀላቅለዋቸዋል)።

ኦፕሬሽኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልግ በመሆኑ ለማጥቃት ዘመቻው የተመረጡት ወጣቶች በሙሉ የአስመራ ከተማን መግቢያና መውጫ በደንብ የሚያውቁ እንዲሆኑ ነበር የተወሰነው።




አስራ ስድስቱ ታጋዮች ለኦፕሬሽኑ የሚያስፈልጋቸው የኮማንዶ ስልጠና በሰሜን ኤርትራ በሚገኘው የሳሕል በረሃ ይሰጣቸው ጀመር። ስልጠናውም ሆነ ስምሪቱ በከፍተኛ ጥንቃቄና ሚስጢር መካሄድ ስለነበረበት ከሰልጣኞቹ፣ ከአንዳንድ የሻዕቢያ ወታደራዊ ሃላፊዎች እና ከጥቂት የግንባሩ መሪዎች በቀር ሌሎች የግንባሩ ታጋዮች ስለጉዳዩ የሚያውቁት ነገር አልነበረም።



ኮማንዶዎቹ በዚህ መንገድ ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ከሳሕል ተነሱ። እጅግ ሚስጢር በተመላበት ሁኔታ 250 ኪሎ ሜትር ተጉዘው አስመራ ከተማ ዳርቻ ላይ ደረሱ። እዚያ ሲደርሱም በፊት የኮማንዶ ስልጠና የነበራቸውና መረጃ በማሰባሰብ ስራ ላይ የተሰማሩት ሁለት ኮማንዶዎች ተቀላቀሏቸው።

ኮማንዶዎቹ ያሰቡትን ጥቃት ለመፈጸም የያዟቸው መሳሪያዎች AK-47 ጠመንጃ (ክላሽኒኮቭ)፣ ቀላል ቦምብ ማስወንጨፊያ እና የእጅ ቦምቦዎች ብቻ ነበሩ።



እ.ኤ.አ. ግንቦት 21/1984..... May 21, 1984


ምሽቱ አልቆ ውድቅት ነገሷል። በሰምበል አየር ማረፊያ ያሉ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት አባላት ጥቂት ወታደሮችን በዘበኝነት ከውጪ አቁመው በቤትና በድንኳን ውስጥ ለጥ ብለው ተኝተዋል።

በወታደራዊ አቆጣጠር በ20:00 ሰዓት ላይ ኮማንዶዎቹ የሰንበል አየር ማረፊያን በማጥቃት በነበልባል እና በጭስ ማንደድ ጀመሩ። በአየር ማረፊያው ላይ ያሉ የጦር አውሮፕላኖች በጥይትና በRPG ሲመቱ የሚፈጠረው ፍንዳታ እንደ ብራቅ ጮኸ። የሰንበል ሜዳ በነፍስ ግቢ፣ ነፍስ ውጪ ስሜት በሚተራመሱ ወታደሮች ተመላ። የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ምን እየተካሄደ እንዳለ እና ማን እንደመጣባቸው ማወቅ ተሳናቸው። አውሮፕላኖቹ ወደ ሚቃጠሉበት ቦታ ለመጠጋት ሲሞክሩ ደግሞ በሻዕቢያ ኮማንዶዎች ተኩስ እየተቀነደቡ ይወድቁ ጀመር።

የሻዕቢያ ኮማንዶዎች በአየር ማረፊያው ላይ ቆመው የነበሩትን 33 አውሮፕላኖች በሙሉ አወደሙ። በአስራ ስምንት ደቂቃ ውስጥ ግባቸውን ፈጽመው ወደ መጡበት ማፈግፈግ ጀመሩ። ይሁንና በስተመጨረሻው ሰዓት "እምባዬ" የተባለው ኮማንዶ ከተቃራኒ ወገን በተተኮሰበት ጥይት ተመትቶ ወደቀ። አስራ ሰባቱ ኮማንዶዎች ግን በድል አድራጊነት ወደ ሳሕል ነጎዱ።




በሰንበል አየር ማረፊያ ላይ የተፈጸመው ጥቃት በደርግ መንግሥት መሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀሰቀሰ። በማግሥቱ ጓድ ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም እሳት ለብሰው፣ እሳት ጎርሰው ወደ ሰንበል አየር ማረፊያ ከች አሉ። ጥቃቱ ወደተፈጸመበት ስፍራ ሲደርሱ በዚያ ያሉት የጦር ሰራዊቱ አባላት በጥቃቱ የወደቀውን ብቸኛውን የህግሓኤ ኮማንዶ አስከሬን በዱላ እየወገሩ እና በሳንጃ እየወጉ ሲጫወቱበት አገኟቸው።

መንጌ ባዩት ነገር በጣም ተናደዱ። ወታደሮቹንም እንዲህ ሲሉ ተቆጧቸው።
"በቶሎ አቁሙ! ወራዳ ሁላ! ይህ ልጅ ላመነበት ዓላማ ተሰውቷል። እናንተ ግን የእርሱን ያህል ለዓላማ መዋጋትን የማታውቁ ውርጋጦችና ልፍስፍሶች ናችሁ። አሁን አስከሬኑን በቶሎ አንሱትና በክብር ቅበሩት"



ከዚያ ጥቃት በኋላ የኢትዮጵያ አየር ሃይል እስከ ናቅፋ እና ቃሮራ ድረስ እየሄደ የሚያደርሳቸው ጥቃቶች በእጅጉ ቀንሰዋል። ኤርትራም ከሰባት ዓመት በኋላ ነፃነቷን ተቀዳጅታለች።



Re: ✈️ ✈ ለማመን የሚያስቸግር አስደናቂ እውነተኛ ታሪክ ✈ ✈️

Posted: 07 Oct 2025, 09:00
by Fiyameta



Re: ✈️ ✈ ለማመን የሚያስቸግር አስደናቂ እውነተኛ ታሪክ ✈ ✈️

Posted: 07 Oct 2025, 10:11
by Fiyameta
:P :P :P :P


Re: ✈️ ✈ ለማመን የሚያስቸግር አስደናቂ እውነተኛ ታሪክ ✈ ✈️

Posted: 07 Oct 2025, 10:34
by ZEMEN
Fiyameta wrote:
07 Oct 2025, 10:11
:P :P :P :P

No, the reason that India rejected the fighter jets is because they were defected. The Indians asked for their Money back and Russia agreed to give India new upgraded once. In the Agreement, India agreed to return the fighter jets to Russia and Russia sold it to Ethiopia. For your information, Ethiopia has no qualified pilot to fly those modern fighter jets. Mig 29 is the main Ethiopian pilots good at. No that the Ethiopian pilots are bad, in fact they very good but due to race and Killil division, all the best pilots are excluded, dismissed and some left the country. Currently there five Ukrainian pilots who are employed by the GALA government. Even though, the only Airforce in the world to let its helicopter to be captured is the Ethiopian Airforce. Those diam Eritreans know how to take everything back.

Re: ✈️ ✈ ለማመን የሚያስቸግር አስደናቂ እውነተኛ ታሪክ ✈ ✈️

Posted: 07 Oct 2025, 12:43
by Fiyameta





Re: ✈️ ✈ ለማመን የሚያስቸግር አስደናቂ እውነተኛ ታሪክ ✈ ✈️

Posted: 07 Oct 2025, 19:07
by Fiyameta
33 MIG fighter planes worth $2 billion dollars turned to ashes in less 18 minutes.

The sad part is, 40 years later, Ethiopia is still struggling to pay the IMF loans it obtained to purchase the 33 planes, plus interest.

Please wait, video is loading...

Re: ✈️ ✈ ለማመን የሚያስቸግር አስደናቂ እውነተኛ ታሪክ ✈ ✈️

Posted: 08 Oct 2025, 01:31
by Fiyameta